Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ ግርማ የሺጥላ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።
ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ለውይይት በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላው ህዝባችንን በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ የሚመክር መሆኑን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከሶማሊያ ፖሊስ አዛዥና ከጅቡቲ ፖሊስ ምክትል አዛዥን ጋር ተወያዩ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከሶማሊያ ብሄራዊ ፖሊስ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሱሉብ አህመድ ፊን እና ከጅቡቲው ብሔራዊ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዑመር ሁሴን ሀሰን ጋር ተወያዩ ።
ውይይታቸውም ሽብርተኝነትና የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተቀናጀ የሦስትዮሽ ጥምረት ለመከላከል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የሦስቱን ሀገራት የፖሊስ መኮንኖችን አቅም ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በቀጣይም የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በጅቡቲ ለመፈራረም ተስማምተዋል፡፡