Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ ግርማ የሺጥላ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።
ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ለውይይት በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላው ህዝባችንን በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ የሚመክር መሆኑን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከሶማሊያ ፖሊስ አዛዥና ከጅቡቲ ፖሊስ ምክትል አዛዥን ጋር ተወያዩ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከሶማሊያ ብሄራዊ ፖሊስ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሱሉብ አህመድ ፊን እና ከጅቡቲው ብሔራዊ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዑመር ሁሴን ሀሰን ጋር ተወያዩ ።
ውይይታቸውም ሽብርተኝነትና የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተቀናጀ የሦስትዮሽ ጥምረት ለመከላከል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የሦስቱን ሀገራት የፖሊስ መኮንኖችን አቅም ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በቀጣይም የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በጅቡቲ ለመፈራረም ተስማምተዋል፡፡
በመኸር እርሻው 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ይሸፈናል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም እርሻ እንደሚሸፈን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በግብርና ሚኒስቴር የብርዕና አገዳ ሰብሎች ዴስክ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ቢረዳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን በክላስተርና በመደበኛ ከሚሸፈነው 16 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታሩ መሬት በኩታ ገጠም እርሻ ይሸፈናል፡፡
በሚኒስቴር ደረጃ በተመረጡ አስራ ሁለት ሰብሎች ላይ የኩታ ገጠም ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100956