Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግብጽ በነበሩበት ወቅት አዲሱን ካይሮ ጎብኝተዋል‼️
ኮሚሽኑ በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተሳታፊ ልየታ ሥራ በዚህ ወር ይጀምራል

👉 ከአራት ክልሎች ሁለት ሺህ 603 ተሳታፊዎች ተለይተዋል
*******************
(ኢ ፕ ድ)

አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተሳታፊ ልየታ ሥራ በተያዘው የሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ገለጸ።

የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ አስተባባሪ ወይዘሮ ቤተልሔም ኪሮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተባባሪ አካላት ....
https://www.facebook.com/100069403920568/posts/pfbid02A6fkzmgHVefB8i6sdHx7yFoZ2U1dygcDJvmXwhMkWuguJXwwTDby5vJpmiGfQHHgl/?mibextid=Nif5oz
አቶ ደመቀ መኮንን ከጋምቢያና ማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጋምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማመዱ ታንጋራ (ዶ/ር) እና ከማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ቴምቦ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በኬንያ እየተካሄደ ከሚገኘው 43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሔደ ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ከጋምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማመዱ ታንጋራ (ዶ/ር) እንዲሁም ከማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ቴምቦ ጋር ባደረጉት ውይይት በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በሀገራቱ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም
በመጪዎቹ ቀናት ቅጽበታዊ ጎርፍና የወንዞች ከገደብ በላይ መሙላት ሊከሰት ይችላል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
አዲስ አበባ፦ በአገሪቱ ዋና ዋና ተፋሰሶች ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ስለሚኖር በተፋሰሶቹ ውስጥ በሚገኙ ለጎርፍ ተጋላጭ ቦታዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ እና የወንዞች ከገደብ በላይ መሙላት ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ።

ሰሞኑን በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ .....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0tebm5t5UE2GvgPQRKkSXCo4UL382qX5HshVAKrXLu7YmgsM6Vb1zGZFWiMESqeZ7l&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz
የሸገር ዳቦን ዳግም ወደምርት ለማስገባት ጥረት እያደረገ መሆኑን ሚድሮክ ገለጸ
👉ቢሮው በበኩሉ ጥራት ያለው ስንዴ ለፋብሪካው እንዲቀርብ እየሠራ መሆኑን አሳውቋል
*****************
(ኢ ፕ ድ )

ዳቦ ማምረት ያቆመው የሸገር ዳቦን መልሶ ለማስጀመር ጥረት እያደረገ መሆኑን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበኩሉ ለሸገር ዳቦ ፋብሪካ በግብዓትነት ተገዝቶ የነበረው ስንዴ የጥራት ችግር ስላጋጠመው ችግሩን በመፍታት ጥራት ያለው ስንዴ እንዲቀርብ እየተሠራ መሆኑን ገልጿል።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሰይድ ሞሐመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ከተቋረጠ ከሁለት ሳምንት በላይ የሆነውን የሸገር ዳቦ አቅርቦት .....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0X3rJw5WityKnm8rcYfQwLAH8CEd3e2YC4Cz4yV7rFkmvuiwHSkGkzAoXXVUEFT9al&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz