Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በዓለም መንግሥታት ጉባኤ እየተሳተፉ ነው
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቆይታቸው ወቅት በከተማ ፕላን እንዲሁም የወደፊት ከተሞችን በተመለከተ ከሚኖራቸው ውይይት በተጨማሪ በሌሎች መድረኮች እና የፓናል ውይይቶች ላይ በመታደም የወደፊት የአስተዳደር ዘርፎች ላይ የሚያተኩሩ የጎንዮሽ ውይይቶች ላይ የሚሳተፉ ይሆናል::

በውይይት መድረኩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሃመድ እንዲሁም የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ተሳታፊ ሆነዋል::

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
ቢሮው የሴቶች ቀን 'ማርች 8' ን በተለያዩ ኹነቶች እንደሚያከብር ገለጸ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዘንድሮው የአለም ሴቶች ቀን(ማርች 8)በተለያዩ ኹነቶች ሊያከብር ዝግጅት ላይ መሆኑን የኦሮሚያ ሴቶች እና ሕጻናት ቢሮ ገለጸ።

የዘንድሮው ማርች 8 በአለም ለ113ኛ፣በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ" በሴቶች ላይ መሥራት እድገት ያፋጥናል" በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ መብራት ባጫ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣ የክልሉን ሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴቶችን በተለያዩ ማሕበራት የማደራጀት ሥራ ተሰርቷል።

የሴቶች የቁጠባ ባህል ለማዳበር 3.1 ሚሊዮን ሴቶች በሲንቄ ባንክ ከ 5.3 ቢሊዮን ብር እንዲቆጥቡ ተደርጓል።

በኦሮሞ ባሕል መሰረት 541 ሕጻናት በጉዲፈቻ ሕጋዊ ወላጅ እንዲያገኙ መደረጉን የገለጹት ኃላፊዋ፤ 15ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉን አመላክተዋል።

ወይዘሮ መብራት፣ የዘንድሮው የሴቶች ቀን ሲከበር ሶስት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ቁጠባ ከሴቶች ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቁመው፤ ለችግር የጋለጡ ሴቶችና ሕጻናት ድጋፍ ማድረግ፣ የሴቶች ሰላም ኮንፈረንስ ማካሄድ፣ሴት ተማሪዎችና ሴት ፋብሪካ ሰራተኞች ጋር ውይይት ማድረግና ማስ ስፖርት የአከባበሩ ኹነቶች መሆናቸውን አብራርተዋል።

በዋቅሹም ፈቃዱ
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም