Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ዲፕሎማሲያችን_ለብሔራዊ_ጥቅማችን

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት ጋር በመተባበር "ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደርዕይ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መጎብኘቱን ቀጥሏል።

በዛሬው ዕለት ከሆለታ ከተማ ሳደሞ ቀበሌ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ ተማሪዎች፣ ከከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የመጡ ተማሪዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስተባባሪነት ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተወከሉ ሰራተኞች አውደርዕዩን እየጎበኙ ይገኛሉ።

በተስፋ ፈሩ
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
የመሪዎችና የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔዎችን በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን ግብረ ኃይሉ አስታወቀ
*******
(ኢ.ፕ.ድ)

37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል እስከአሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ የፀጥታ ስራዎች ስኬታማ መሆናቸውን ገምግሞ፤ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔም በሰላም እንዲጠናቀቅ በርካታ የፀጥታ ኃይል አሰማርቶ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና ደኅንነት ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ገልጿል።

በተከታታይ እየተካሄደ ያለው የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተቀናጀ ኦፕሬሽን አዲስ አበባ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሆና እንድትቀጥል ያስቻለና አሁን ላይም የከተማዋ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ መቀጠሉን በግምገማ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል።

ግብረ-ኃይሉ ባካሄደው ግምገማ እስከአሁን ለተገኘው ሰላም እና በተካሄደው ኦፕሬሽን ለተገኘው ውጤት የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር ብሏል መግለጫው።

አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ሕብረት እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ ፀጥታዋ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ግብረ-ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጫው አንስቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ሀገር ሁሉም የፀጥታ መዋቅር የሚመለከተውን የሥራ ድርሻ ወስዶ አካባቢውን ፍፁም ሰላማዊ ለማድረግ በኃላፊነትና በተጠያቂነት የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ መግለጫው ጨምሮ ገልጿል።

በጉባዔው ላይ የሚታደሙ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ወግና ባህል በመቀበል እና በማስተናገድ በቆይታቸው ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ፤ ካረፉባቸው ሆቴሎች ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚሄዱበት ወቅት ሰላም ወዳዱ ሕዝባችን በባለቤትነት የሚጠበቅበትን የዜግነት ድርሻውን በኃላፊነት እንዲወጣና ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ቀና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል
የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኗል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር ) በይፋ የተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኗል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማችን ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መታሰቢያውን እንዲጎበኙ ባደረጉት ጥሪ መሰረት ነዋሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉ ነዋሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያ ድሉን በሚመጥን መልኩ መገንባቱን ገልፀው ሌሎችም ሙዚየሙን በአካል በመጎብኘት የጋራ ታሪካችን የሆነውን ዓድዋን በተጨባጭ እንዲገነዘቡ ጥሪ አቅርበዋል::

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም