Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ ‼️
#አህመድ_ቤን_ቤላ
“የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩት የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም መጥተው ግንቦት 1955 ዓ.ም. 32 የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ይህንን ድርጅት ከመሰረቱ የአፍሪካ አባቶች መካከል የቀድሞው የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ ቤን ቤላ አንዱ ናቸው።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።
አማርኛ የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጠይቃለች‼️

44ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በዚህ ጉባዔ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ አፍሪካ ህብረት የአማርኛ ቋንቋን የስራ ቋንቋው እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበዋል።

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ተመሥርቶ የድርጅቱ መመሪያ ውል በ32 መሥራች አገር መሪዎች ጸድቆ ተፈርሟል።

የምሥረታ ቻርተሩ ከተዘጋጀባቸው አራት ቋንቋዎች መካከል አማርኛ አንዱ ነበር።

የድርጅቱም ፅኅፈት ቤት በአዲስ አበባ እንዲሆን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ ላይ ይገኛል።

ይህ ድርጅት በ1994 ዓ/ም የአፍሪካ ኅብረት በሚባለው ስያሜ ተተክቷል።

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበትና በአማረኛ የተጻፈውን ቻርተር ከስር ይመልከቱ
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ ‼️

#ምዋሚ_ምዋምቡትሳ IV

“የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩት የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም መጥተው ግንቦት 1955 ዓ.ም. 32 የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ይህንን ድርጅት ከመሰረቱ የአፍሪካ አባቶች መካከል የቀድሞው የብሩንዲ ንጉሥ ምዋሚ ምዋምቡትሳ IV አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።

(ኢ.ፕ.ድ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም)
ነገ ለሚካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ድሬዳዋ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

ነገ በድሬዳዋ ከተማ ለሚካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።

በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና”በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የሚካሄደውን ሕዝባዊ ውይይት ለመምራትም የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጸጋዬ ማሞ ወደ ከተማዋ ገብተዋል፡፡

አመራሮቹ ድሬዳዋ ሲገቡ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የከተማዋ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከከተማ አስተዳደሩ ኮምንኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም
በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የ51 ሀገራት መሪዎች ይሳተፋሉ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

በመጪው ቅዳሜና እሁድ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የ51 ሀገራት መሪዎች እና የ14 ዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች እንደሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለአቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) የዛሬውን የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የ51 ሀገራት መሪዎች እና የ14 ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።

እየተካሄደ ከሚገኘው የ44 ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከቱኑዚያ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ውይይቱ ከሌሎች ሀገራት ጋርም በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል አቀባዩ አመላክተዋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው መደበኛ ስብሰባ ኢትዮጵያ በትምህርት እና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ስኬታማነት እየሰራችው ያለው ስራ ተንጸባርቋል ብለዋል።

በሄለን ወንድምነው እና ቃልኪዳን አሳዬ
የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና ፖርቱጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲልቪ ባይፖ- ተሞን ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ ከፖርቱጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ ከፖርቱጋል ጋር በቱሪዝም ፣ትምህርት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ተባብራ መስራት ትፈልጋለች ብለዋል።

የፖርቹጋሉ ሚኒስትር በበኩላቸው አገራቸው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራን እንደምትደግፍ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም
37ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚታደሙ እንግዶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
***************
(ኢ ፕ ድ)

በ37ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ የገቡ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ዲፕሎማቶችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጎብኝተዋል።

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች እንግዶችን በመቀበል ጉብኝቱን መርተዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በሳለፍነው እሑድ መመረቁ ይታወቃል።

የዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዚየም ኢትዮጵያውያን ከ128 ዓመታት በፊት ለቅኝ ግዛት የመጣውን የጣልያን ወራሪ ኃይል በአንድነት መክተውና አሸንፈው ነፃነታቸውን ያስከበሩበት እና ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነት ምልክት መሆን ያስቻሉ የድሉ መሪዎች፣ የጦርነቱ ተሳታፊዎችና ሌሎች ታሪካዊ እውነታዎች በአንድ ላይ የተገለጡበት ነው።

በአዲሱ ገረመው

የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮጵያውያን ኅብረ ብሔራዊነታቸውን በዓድዋ ድል አስመስክረዋል
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያውያን ኅብረ ብሔራዊነታ ቸውን ጠላትን በአንድነት ቆመው ተዋግተው ባሸነፉበት የዓድዋ ድል ማስመስከራቸውን ተባባሪ ፕሮፌሰር አየለ በከሪ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር አየለ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዓድዋ ድል ሕዝቦች ሀገራቸውን ለማዳን በመዘጋጀታቸው፣ በአንድነት በተከፈለ መስዋዕትነት የተመዘገበ የሚያስደንቅና በአርዓያነትም የሚጠቀስ ኅብረብሔራዊ ድል ነው፡፡

የየጁ፣ የወለጋና የሸዋ ፈረሰኞች እንዲሁም የጎንደር፣ የቤኒሻንጉልና የሸዋ ተዋጊዎች አንድም ሳይቀሩ ዓድዋ ላይ ተዋግተው ሲያሸንፉ ያስመሰከሩት ኅብረብሔራዊነታቸውን ነው ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ ዓድዋ ኅብረብሔራዊነት የኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ መሆን እንዳለበት ትምህርት የተሰጠበት...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120864
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
👉አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቶን ጭነት አጓጉዟል

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሰባት ወራት ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ።

አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቶን ገቢና ወጪ ጭነት እንዲሁም ከ115 ሺህ በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን ማኅበሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡

በማኅበሩ ከፍተኛ የእቅድና የፕሮግራም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ፍስሐ መብራህቶም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ሁለት ቢሊዮን 256 ሚሊዮን 459 ሺህ ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ሁለት ቢሊዮን 158 ሚሊዮን 333 ሺህ ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ያነሱት አቶ ፍስሐ፤ የእቅዱን 104 በመቶ በማሳካት ከሚጠበቀው በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን አስረድተዋል፡፡

አቶ ፍስሐ አክለውም፤ ባለፉት ሰባት ወራት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ቶን ጭነት ለማጓጓዝ ታቅዶ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120890
በአማራ ክልል በሩዝ ሰብል ከለማው መሬት ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኘ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአማራ ክልል በመኸር ወቅት በሩዝ ሰብል ከለማው መሬት ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ አግደው ሞላ እንደገለጹት፤ ምርቱ የተገኘው በ2015/2016 የምርት ዘመን በሩዝ ሰብል ከለማ ከ82 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ነው።

ምርቱ የተሰበሰበው ለሩዝ ሰብል ልማት ተስማሚ በሆኑት ደቡብ፣ ማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳ በሩዝ ሰብል ከለማ መሬት መሆኑን ተናግረዋል።

የተሰበሰበው ምርት በቀዳሚው ዓመት ከተገኘው ጋር ሲነጻጸር ከ900 ሺህ ኩንታል በላይ፤ በለማው መሬት ደግሞ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል።

በክልሉ የተሻሻሉ የሩዝ ምርጥ ዘሮችን ተደራሽ በማድረግ ልማቱ እንዲስፋፋ መደረጉ ከውጭ የሚገባን የሩዝ ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት የተያዘውን ግብ ለማሳካት እያገዘ መሆኑንም አቶ አግደው አስታውቀዋል።

ከእዚህ በተጨማሪ ልማቱ አርሶ አደሩ በምግብ ራሱን እንዲችል ከማድረግ ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱ በዘላቂነት እንዲያረጋገጥ የጎላ ሚና እንዳለው ነው ያስረዱት።

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ አርሶ አደር መልኬ መለሰ እንዳሉት፤ ባለፈው የመኸር ወቅት ''ሻጋ'' የተባለውን የሩዝ ምርጥ ዘር ተጠቅመው ካለሙት አንድ ሄክታር መሬት 60 ኩንታል ምርት አግኝተዋል።

የተሻሻሉና ምርታማ የሆኑ የሩዝ ዝርያዎች ተደራሽ መደረጋቸው የእሳቸውንና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ምርታማነት እያደገ እንዲመጣ ማገዙን ተናግረዋል።

በዚህም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን ነው የገለጹት።

ሌላው የወረዳው ነዋሪ አርሶ አደር ተዋቸው ፈጠነ በበኩላቸው፤ በምርት ዘመኑ የማዳበሪያ ዕጥረት ቢያጋጥምም በሩዝ ሰብል ካለሙት አንድ ሄክታር ተኩል መሬት 65 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

‘‘ምርታማነትን ለማሳደግ በምናደርገው ጥረት ዋነኛ ችግራችን የማዳበሪያ ግብዓት አቅርቦትና ጥራቱን የጠበቀ የሩዝ መፈልፈያ ማሽን አለመኖር ነው’’ ያሉት ደግሞ ሌላኛው የወረዳው አርሶ አደር ዘላለም አስፋው ናቸው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ አርሶ አደሩ በምርት ዘመኑ የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት ገጥሟቸው የነበረ ቢሆንም በአንድ ሄክታር መሬት ካለሙት የሩዝ ሰብል ከ50 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘታቸውን ተናገረዋል።

በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት በሩዝ ሰብል ከለማው 61 ሺህ ሄክታር መሬት 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
የጉጂ አባገዳዎች ህገ ደንቦችን አሳወቁ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የጉጂ አባገዳዎች ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት በሥርዓቱ መሠረት መተግበር ያለባቸውን የተለያዩ ድንጋጌዎችን አሳለፉ።

በጉጂ ዞን አዶላ ከተማ በተካሄደው ድንጋጌዎችን የማሳወቅ መርሐ ግብር ከተላለፉ ህገ ደንቦች መካከል፤ የሴቶች መብት የተከበረ ስለመሆኑና ምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት ሁሉ ክብር የሚገባቸው መሆኑ ይጠቀሳሉ።

በገዳ ሥርዓት ሰው መግደል፣ ሙስና መስጠትና መቀበል፣ ፍትህ ማዛባት፣ ሠላም ማደፍረስ፣ ነባር የገዳ ሥርዓትና ባህል መበረዝ፣ በማንኛውም ፍጥረት ላይ ወንጀል መፈፀምና ሌሎች ሀገራዊ እሴትን መፈፀም የተወገዘ ሆኑን በድንጋጌው ወቅት አስገንዝበል።

ከዚህም በተጨማሪ ለሠላምና ለአንድነት ሁሉም ሊታጋ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በአዶላ ከተማ አቅራቢያ አርዳ ጂላ በሚባለው ቦታ 75ኛ የጉጂ አባ ገዳዎች የ"ባሊ" ስልጣን ርክክብ መርሐ ግብር እየተከናወነ ሲሆን፤ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ክፍለዮሐንስ አንበርብር
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓም