የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል
******************
( ኢ ፕ ድ)
የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን የምሰረታ ይፋ ማድረጊያ መረሐግብር ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ደራራ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ ፋውንዴሽኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ከተመሠረተ ዓመት ቢሆነውም የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል።
አርትስቱ በህይወት እያለ ባህልንና ማህበራዊ ጉዳዮችን በዜማና በጥበብ ለህዝብ ሲያደርስ መቆየቱን አስታውሰው ፋውንዴሽኑ የአርቲስቱን ስራዎች ለማስቀጠል እንደምሰራ ገልፀዋል።ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የፋውንዴሽኑ ዳይሬክተር አቶ አሳድ ፋህሚ በበኩላቸው የፋውንዴሽኑ ዋና አላማ የአርትስት አሊ ቢራን ሥራዎችና ራዕዎችን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ነው ብለዋል።
በዚህም መሠረት ኪነጥበብን ማጎልበት፣ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ማስፋፋት፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ በጎ ሥራዎችን ማከናወን ላይ በትኩረት መሥራት የፋውንዴሽኑ አላማ መሆኑ ተናግረዋል።
የአርትስቱ ባለቤትና የፋውንዴሽኑ መስራች ወ/ሮ ኢሊሊ ማርቆስ ቢራ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ አልሞ የተነሳው አርትስቱ በህይወት እያለ መሥራት የሚፈልጋቸውን ስራዎች እውን ማድረግ ነው።
ይህ እንድሳካ ሀገር ውስጥ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።
በወይንሸት ካሳ
ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ከብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን በብሪክስ ማዕቀፍ ስር ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማስፋት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ሰኔ 2016 ዓም

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከሀምሌ 3 ጀምሮ በወረቀትና በኦንላይን ይሰጣል
******
(ኢ ፕ ድ)
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ በወረቀትና በኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሰታወቀ።
የአገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ፣ በሰጡት መግለጫ፤ ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከሀምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረሰ ፈተናውን እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡
የዘንድሮው ፈተና በወረቀትና በኦንላይን ጭምር እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡
የትግራይ ክልልን ጨምሮ 701ሺህ 489 የሚሆኑ ተማሪዎች የሚፈተኑ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሳይንስ 369 ሺህ 60፣ በተፈጥሮ ሳይንስ 332ሺህ 429 ተማሪዎች ለፈተናው እንደሚቀመጡ ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህ ውስጥም 99 በመቶ ያህሉ ተፈታኞች በመጀመሪው ዙር የሚፈተኑ ሲሆን፤ ወደ አንድ በመቶ የሚጠጉ ተማሪዎች በተለይ በጸጥታ ችግር ትምህርት ቀድመው ባለመጀመራቸው ምክንያት በሁለተኛው ዙር እንዲፈተኑ የሚያስችሉ ዝግጅቶች ማደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የዘንድሮው ፈተና እንደ ቀድሞው በወረቀት ብቻ ሳይሆን በኦንላይንም እንደሚሰጥ ጠቅሰዋው ከኦንላይን የፈተና አሰጣጥ አኳያ በፌዴራልና በክልል ደረጃ በተቋቋመ ኮሚቴ አማካኝነት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በአዲሱ ገረመው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።
በተመሳሳይ ሶስት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።
ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር ሲመለከቱ የነበሩት የጤና፣ ማህበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች እና የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በጋራ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡት የጤና፣ ማህበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቀስሙ ማሞ፤ አዋጁ ላይ የተካተቱ ዋና ዋና ሀሳቦችን በዝርዝር አቅርበዋል።
የሕዝብ በዓላት ለዜጎች ሥነ-ምግባርና ስነ-ልቦና ግንባታ እንዲሁም ለሀገርና ለህዝብ ያላቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ ስለመሆኑ በውሳኔ ሀሳቡ ተብራርቷል።
የሕዝብ በዓላት ኃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴታቸውን ጠብቀው በሰላም በድምቀት እና የዜጎችን የእርስ በእርስ መልካም ግንኙነትና መተሳሰብ በሚያጎለብት ሁኔታ እንዲከበሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።
የህዝብ በዓላት አከባበርና ሥርዓት ኃይማኖታዊና ባህላዊ ይዘታቸውን ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ያለው አስተዋፅዎና ለሀገራዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና ያላቸው በመሆኑ ከመንግስት የሚጠበቀውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ እንዲሁም በቂ የሚዲያ ሽፋን የሚሰጥ እንደሆነም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተብራርቷል።
ነባሩ የሕዝብ በዓላትና የዕረፍት ቀን መወሰኛ አዋጅ የሕዝብ በዓላት ሲከበሩ ጥቅም ሊያስገኙ በሚችሉ መልኩ በድምቀት የሚከበሩበትን ዝርዝር የአከባበር ሥነ-ሥርዓት አለማስቀመጡም ተመላክቷል፡፡
ይህ አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላትና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን፤ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩት መወሰን እንደሚችሉ ገልፀዋል።
በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመስልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ከምክር ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሦስተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆናለች
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ማሻሻል በመቻሉ በ2016 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሦስተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆን መቻሏን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሐና አርዓያሥላሴ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ለማሻሻል ብዙ የአሠራር ማሻሻያዎችና ለውጦች አድርጓል፡፡
የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ማሻሻል በመቻሉ እየተገባደደ ባለው የ2016 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሦስተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለመሆን በቅታለች፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በምሥራቅ አፍሪካ ቁጥር አንድ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆን መቻሏን አውስተው፤ በቀጣይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ጠንካራ ሥራ እየተሠራ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡
እንደ ኮሚሽነር ሐና ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ለማሻሻል ብዙ የአሠራር ማሻሻያዎችና ለውጦች ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዋናነት መሠረተ ልማት ላይ የተደረጉ ኢንቨስትመንቶች.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን https://press.et/?p=129735

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት በጋራ ለማደግ የሚያስችል ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ከቀጣናው ሀገሮች ጋር በጋራ ለማደግ የሚያስችል መሆኑን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት በቀጣናው ሀገራት ብዙ ዕድሎችን ይፈጥራል፡፡
በተለይ ሀገሮቹ በጋራ ችግር ፈቺ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ምርምሮችን በመስራት በጋራ ለማደግ ያስችላቸዋል።
በምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ያለውን የረዥም ጊዜ ልምድ በመጠቀም የአካባቢውን አርሶ አደርና የማህበረሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ችግር ፈቺ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኘ ጀማል (ዶ/ር) ገልጸው፤ይሁንና ዩኒቨርሲቲው የሚሠራውን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129736

በመዲናዋ 35 በመቶ ሕፃናት በወቅቱ ትምህርት አያገኙም
**************
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሕፃናት መካከል 35 በመቶ በወቅቱ ትምህርት ቤት እንደማይገቡ የአዲስ አበባ ሴቶች ፣ ሕፃናት፣ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው “የሕፃናት ትምህርት ፣ተሳትፎና ጥራት ለማሳደግ ጊዜው አሁን ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ሰኔ ዘጠኝ ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለ33ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአፍሪካ የሕፃናት ቀን አስመልክቶ ከማስታወቂያና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በቢሮው የሕፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ አናኒያ ያቆብ እንደገለጹት፤ ቢሮው በቅርቡ ባደረገው ጥናት ሰባት ዓመት ሆኗቸው እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሕፃናት መካከል ወደ ትምህርት ቤት የሚገቡ ሕፃናት ቁጥር.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129751

በሚቀጥሉት ቀናት የሚጠበቀው ዕርጥበት የመኸር ሰብሎችን ለመዝራትና ማሳን ለማዘጋጀት አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በሚቀጥሉት ቀናት የሚጠበቀው እርጥበት አስቀድመው የሚዘሩ የመኸር ሰብሎችን ለመዝራትና ማሳን ለማዘጋጀት አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ ፡፡
ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ፤ በሚቀጥሉት ዘጠኝ ቀናት የሚጠበቀው እርጥበት አስቀድመው የሚዘሩ የመኸር ሰብሎችን በወቅቱ ለመዝራትና ማሳን ለማዘጋጀት አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው አስታውቋል።
በበልግ አብቃይ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዘግይተው ለተዘሩና ፍሬ በመሙላት ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎች፣ ለቋሚ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች የውሃ ፍላጎትን ከማሟላት አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው በመግለጫው ተመላክቷል።
በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚጠበቀው የእርጥበት ሁኔታ የረጅም ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት፣ ለቋሚ ተክሎች፣ በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ለተተከሉና ለሚተከሉ ችግኞች እድገት ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል በሚቀጥሉት ቀናት በዓባይ፣ በላይኛውና በመካከለኛው ባሮ አኮቦ፣ ኦሞ ጊቤ፣ ስምጥ ሸለቆ፣ አዋሽ፣ ተከዜና በጥቂት የአፋር ደናክል ተፋሰሶች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የእርጥበት ያገኛሉ። በተፋሰሶች ላይ የሚኖረውን የገፀ ምድርም ሆነ የከርሰ ምድር የውሃ ሀብትን ያሻሽላል፤ ለመስኖም ሆነ ለሀይል ማመንጫነት የሚያገለግሉ የግድቦችን የውሃ መጠን ያሻሽላል ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ በሚቀጥሉት ዘጠኝ ቀናት ለክረምት መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፉና እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ ተመላክቷል።
በሄለን ወንድምነው
ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓም

ኢትዮጵያ በማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማትን ሐዘን ገለጸች
*************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው የሐዘን መግለጫ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ለማላዊ መንግሥትና ሕዝብ የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
የማላዊ መከላከያ ኃይል አውሮፕላን የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍሮ ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) 100 ቀናት እና የሁለተኛው ሀገር በቀል ኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ባቀረቡት ሪፖርት‼️
👉 ባለፉት አሥር ወራት የ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል፣
👉 ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 ነጥብ 3 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፣
👉 መንግሥት 425 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧል፣ 271 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰበሰበ ነው፣
👉 ከሸቀጦች የወጪ ንግድ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር፤ ከሬሚታንስ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል፣
👉 የመንግሥት የበጀት ጉድለትም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ14 በመቶ ቀንሷል፣
👉 ለ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች በሀገር ውስጥ፤ ለ300 ሺህ ለሚሆኑት በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፣
👉 በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ኢትዮጵያ የ7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ታሰመዘግባለች፣
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129734