Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ዛሬ ጠዋት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ከፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጉሌ መልዕክት ይዘው መጥተዋል፤ በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ። እንዲህ ያሉት ግንኙነቶች በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ለንግግርና ትብብር አውታር በመሆን የጋራ መግባባትን ያሳድጋሉ።
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
ግብርና ሚኒስቴር ለአየር ላይ አስሳና ጸረ ለተባይ ኬሚካል ለመርጨት የሚያስችሉ አውሮፕላንኖችን ገዛ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የግብርና ሚኒስቴር የአንበጣ መንጋና የግሪሳ ወፍ በሰብል ምርት ላይ የሚያደረሱትን ጉዳት ለመከላከል፣ ለአየር ላይ አስሳና ጸረ ተባይ ኬሚካል ለመርጨት የሚያስችሉ አምሰት አውሮፕላንኖችን መግዛቱን አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የእጽዋት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ በላይነህ ንጉሴ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገዛቸው ኤርትራክተር 802 በመባል የሚታወቁ ዘመናዊ አውሮፕላኖች የበረሃ አንበጣና የግሪሳ ወፍን መከላከል ያስችላሉ።

ለአውሮፕላንኖቹ ግዢ 10 ሚሊየን ዶላር ወጪ እንደተደረገባቸው ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት በቂ የርጭት አውሮፕላንኖች ባለመኖራቸው የአንበጣ መንጋና የግሪሳ ወፍን መከላከል አዳጋች እንደነበር ጠቅሰው፣ በምርት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

የተገዙት አውሮፕላንኖች የምርት ብክነትን በመቀነስ ምርትና ምርታማነትንና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚደረገው እንቅስቃሴ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ አውሮፕላን የማስተዳደሩ ተግባር በብሔራዊ አየር መንገድ ኃ/የተ/የግል ማህበር የሚመራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አውሮፕላንኖቹ ከላቸው አቅም የተነሳ ፀረ- አረም ና ፀረ-ተባይ የመርጨትና የሰደድ እሳት የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር ላይ እንደሚሰማሩም ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ አየር መንገድ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ካፒቴን አበራ ለሚ በበኩላቸው፤ በግብርና ሚኒስቴር የተገዙት አውሮፕላንኖች በግብርናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ገልጸው ማህበሩ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የአየር ኦፕሬተር ፈቃድ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አግኝቶ በሥራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አውሮፕላኖቹን የማስተዳደር፣ የሚያበሩ ባለሞያዎችንና ቴክኒሻኖችን እንዲሁም አስፈላጊውን የሰው ሀይል የማሟላት ስራን እንደሚሰራ ካፒቴን አበራ ገልጸዋል፡፡
በአማን ረሺድ
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በጅቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ የገቢ-ወጪ ሂደቱን ጎበኙ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በጅቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ ተገኝተው አጠቃላይ የገቢ-ወጪ ሂደቱን ጎበኝተዋል።

የአፈር ማዳበሪያን አስመልክቶ ወደ ሃገር ቤት የሚደረገው ማጓጓዝ እንዲጠናከር ሁለት አዳዲስ የማዳበሪያ ከረጢት መስፊያ ማሽኖች ወደ ኦፕሬሽን እንዲገቡ ሚኒስትሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ይህ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡና የሚወጡ አጠቃላይ ምርቶች የሚስተናገዱበት ነው።
በጉብኝቱም ላይ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጨምሮ የወደብ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና በጅቡቲ የኢትዮጵያ ተቋማት አመራሮች መገኘታቸው ኤምባሲው አስታውቋል።
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
ባለፉት አስር ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጭ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል - ሙፈሪያት ካሚል
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 በጀት ዓመት ያለፉት አስር ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጭ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።

ሚኒስትሯ እንደተናገሩት፤ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ለሥራ የሚሰማሩ ዜጎች ተፈላጊውን ክህሎት እንዲጨብጡ የማብቃት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶታል።

በተለይም የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ውጭ ለማሰማራት አስፈላጊው ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው፥ ስልጠና ከመስጠት ባለፈ ብቁ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል።

እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት 314 ሺህ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ሆነዋል።

የሥራ ስምሪቱ ዜጎች ደህንነታቸው፣ የሚያገኙት ጥቅምና መብታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ በሚያስችል መልኩ መከናወኑንም አብራርተዋል።

በሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው በጥቅሉ ለ3 ሚሊዮን 77 ሺህ ዜጎች የሀገር ውስጥና የውጭ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ እንዳሉት የዲጂታል ሥርዓት በመዘርጋት ዜጎች ተመዝግበው ወደ ሥራ ገበያው እንዲገቡ ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ላይም በትኩረት እየተሰራ ነው።

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍም ወጣቶች ያላቸውን የፈጠራ ሀሳብ ወደ ቴክኖሎጂ ምርት መቀየር የሚችሉበት ስልጠና እና ምቹ ምህዳር መፈጠሩንም አክለዋል።

በዚህም የስራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶችን በማወዳደር ምርቶቻቸውን ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እንዲጠቀሙ በተጀመረው ሂደት 76 ቴክኖሎጂዎች ወደ ምርት መሸጋገራቸውን አብራርተዋል።

ስታርትአፖችና ኢንተርፕራይዞችን በማጎልበት ተጨማሪ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ በመንግስት ትኩረት መደረጉን አስረድተዋል።
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ የደህንነት ስጋት እንደሌለበት በኦዲት ተረጋግጧል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አስራት ቀጄላ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፍ ከ12 አመት በኋላ የመጀመሪያውን የአቪዬሽን ደህንነት ማረጋገጫ ኦዲት ሰርቷል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት አየር ማረፊያዎች ምንም አይነት የደህንነት ችግር እንደሌለባቸው አረጋግጧል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ያመለክታል። በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርፖርቶች በተደረገላቸው ዳሰሳ ጥሩ ውጤት አግኝተዋል።

ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ምንም አይነት የአቪዬሽን ስጋት የለባትም ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ይህም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ውጤት ነው። አየር መንገዱም የኢትዮጵያና የአፍሪካ ኩራት ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳዋል ብለዋል።

ውጤቱ አየር መንገዱ በቀላሉና ያለ ምንም የቅድመ ደህንነት ፍተሻ የበረራ አድማሱን ለማስፋት ይረዳዋል። ሌሎች አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለመስራት ትልቅ እድል ይከፍታ።

በኦዲት የተገኘው የአቪዬሽን ደህንነት ውጤት የቱሪዝም ፍሰቱን ያሳድገዋል። የኢትዮጵያን ገጽታም ለመገንባት ይረዳል።

የተሰጡ አስተያየቶች በቀላሉ የሚስተካከሉ ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ፣ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር በቅርቡ ማስተካከያ ይደረግባቸዋል ብለዋል።

በቀጣይም የአቪዬሽን ዘርፉን ተመራጭ ለማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ሞገስ ጸጋዬ
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ከ7 ቢሊዩን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል
********************
(ኢ ፕ ድ)

በዘንድሮው አመት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም 7 ነጥብ 5 ቢሊዩን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው አመት በአንድ ጀምበር በሚደረገው ችግኝ ተከላ መርሐግብርን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ዝግጀት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

ከሚተከሉ ችግኞች 43.9 በመቶ የደንና የውበት እንዲሁም 56.1 በመቶ የጥምር ደን መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

ከ800 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ችግኝ የሚተከልባቸው ቦታዎችን በጂኦሪፈራንስ እንዲለዩና ካርታ እንዲወጣላቸው ማድረግ እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡

በዘንድሮው አመት በአንድ ጀምበር በሚደረገው ችግኝ ተከላ መርሐግብር በርካታ ችግኞችን በመትከል በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ዝግጀት እየተደረገ መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የተፈጥሮ ሃብት መመናመንና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመከላከል የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ዘላቂነት ያለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የአረንጓዴ አሻራ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

በአንደኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በአጠቃላይ 20 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ መላውን ህብረተሰብ በተደራጀ ሁኔታ በማነቃነቅ 25 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል።

ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም
የሀረር ኢኮ ፓርክ ግንባታ ስራ 92 በመቶ ተጠናቋል- አቶ ተወለዳ አብዶሽ ባህል ፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በሀረር ከተማ ከመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ እየተገነባ የሚገኘው የሀረር ኢኮ ፓርክ ግንባታ 92 በመቶ መጠናቀቁን የሀረሪ ክልል ባህል ፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገለፁ፡፡

ፓርኩ በውስጡ ሀረር የምትታወቅበትን የጅብ ትርኢት ማሳያ አንፊ ቲያትር ጨምሮ የተለያዩ ባህላዊ የእደ ጥበብ ውጤቶች ለቱሪስቶች የሚሸጡበት ማእከላትና የመዝናኛ ስፍራዎችን በውስጡ የያዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፓርኩ እየተገነባበት የሚገኘው ስፍራ ሀረር የምትታወቅባቸው የተለያዩ እፅዋት የነበሩበት ስፍራ መሆኑን ጠቅሰው፣በስፍራው ይገኙ የነበሩ አትክልትና ቡናን ጨምሮ የተለያዩ መድሃኒትነት ያላቸው እፅዋቶችን መልሶ በማልማት ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ በተገኘ ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ገቢና በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ የመንግስት ሰራተኞችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እየተገነባ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ፓርኩን ለመገንባት ከሚያስፈልገው 162 ሚሊየን ብር ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሸፈነ መሆኑ ፕሮጀክቱን በክልሉ በመንግስት እየተገነቡ ከሚገኙ ሌሎች ፕሮጀክቶች የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የፓርኩ ግንባታ ሲጠናቀቅም ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር ለክልሉ የቱሪዝም እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
የአሜሪካን ኤምባሲ ለኤጀንሲው የሐሰተኛ ሰነድ መለያ ቴክኖሎጂ ግብዓት ድጋፍ አደረገ
***
(ኢ ፕ ድ)

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባገኘው ድጋፍ በሐሰተኛ ሰነድ አይነቶች፣ ዝግጅትና ልየታ ለአንድ ወር ሲሰጥ የነበረው የ8 ዙር ስልጠና አጠናቋል።

ኤምባሲው ከ2ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ድጋፍ በተጨማሪ ሃሰተኛ ሰነድ ለመለየት የሚያስችሉ በሃገር ውስጥ በቀላሉ የማይገኙ የአጉሊ መነፅርና የUV ጨረራ የቴክኖሌጂ መሳሪያዎችን ለተቋሙ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተረክበዋል። ለተደረገው የአቅም ግንባታና የቁሳቁስ ድጋፍ በኤጀንሲውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል።

ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም
በኦጋዴን ከ21 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ ተረጋገጠ
***
(ኢ ፕ ድ)

በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ ተረጋግጧል፡፡

በአካባቢው 19 ጉድጓዶችን በመቆፈር በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ጋዝ ተገኝቷል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በክልሉ ኦጋዴን አካባቢ ያለውን ሀብት በተገቢው መልኩ ለመጠቀም በስፋት ሥራዎች መሠራታቸውን አብራርተዋል፡፡

በአካባቢው ትልቅ ሀብት እንዳለ መረጋገጡን ያነሱት አቶ ሚሊዮን ፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ በስድስት ቦታዎች ላይ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መኖሩን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129874
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 46 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቅርቧል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት ዓመቱ ባለፉት 11 ወራት 46 ሺህ ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡ በመጪው ክረምት 71 ሚሊዮን የተለያየ ዝርያ ያላቸው የቡና ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ክልሉ ጨምሮ ገልጿል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በክልሉ 46 ሺህ ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡

እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ 67 ሺህ 348 ቶን የቡና ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለመላክ ታቅዶ ባለፉት 11 ወራት 46 ሺህ ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ተልኳል ያሉት አቶ አስራት፤ የተመረተው የቡና ምርትም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እንዲሁም ለውጭ ገበያ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129878
👍1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️