Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
በከተማችን ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ከሆኑ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ተወያይተናል።
የዛሬው መድረካችን እየተሻሻለ የመጣውን የገዢ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ የመስራት አዲስ የፖለቲካ ባህል መዳበር የበለጠ የሚያጠናክር ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ብቻ ስለከተማችን ሰላም፣ ልማት እና የፖለቲካ ባህል መዳበር ስንመክር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ምንም እንኳን የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረንም፣ የጀመርነውን ይህን የትብብር ባህል በማጠናከር የጋራ አጀንዳዎቻችን ላይ ለጋራ ሃገር በጋራ መስራታችንን አሁንም እንቀጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
በቀጣይ ሶስት አመታት ለማጠናቀቅ እየተሰራ የሚገኘው የአሶሳ ስታዲየም የግንባታ ሂደት አሁናዊ ገጽታ በፕሬስ ዐይን‼️

ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ያለ ህዝብ ብቁ ተሳትፎ የሚከናወን ስራ ሙሉ ሊሆን አይችልም!
ሰላማችንን ዘላቂ እና ህዝባዊ መሰረት ያለው ለማድረግ ዛሬ አሰልጥነን ያስመረቅናቸው 11 ሺሕ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላትን ጨምሮ 341 ሺሕ የሠላም ሠራዊት አባላትን የከተማችን የሰላም ዘብ አድርገን አሰማርተናል።

ከ2013 ጀምሮ ሕዝባችንን በተደራጀ መልኩ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ማቀናጀት እና የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት ማድረግ መቻላችን እስካሁን ጋስገኙን ውጤታማ እና ስኬታማ ስራዎች በተጨማሪ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ሰላማዊ ማድረግ ችለናል።

ዛሬ የተመረቃችሁ የሰላም ሰራዊት አባላት ሕዝባችን የሰላሙ እና የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ባለቤትና ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆኑን በመረዳት በየአካባቢያችሁ የሰላምና የመሰረተ ልማቱ ዘብ በመሆን ህዝባችሁን በፍፁም ትህትና እና ፍቅር እንድታገለግሉ አደራ ማለት እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
የናይል ውኃን በፍትሀዊነት ለመጠቀም በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል
- አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የናይል ውሃን በፍትሀዊነት ለመጠቀም በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለፁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በመተባበር የአፍሪካ ድንበር ተሸጋሪ የውሃ ሀብትን በፍታዊነት መጠቀም ላይ ትኩረት ያደረገው 3ኛው አፍሪ ራን የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በጉባኤ ላይ እንደገለጹት፣ የናይል ተፋሰስ ሀገራት በመተባበር በጋራ መልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቆጣጠር ያስፈልጋል። በተፋሰሱ ሀገራት መካከል የልምድ ልውውጥና በጋራ መመካከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የምትገነባው የዓባይ ግድብ ቀጣናዊ ውህደትንና በጋራ መልማትን እንደሚያጠናግር ገልጸዋል።
የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን ለማቋቋም አባል ሀገራት የናይል የትብብር ማእቀፍን ማጽደቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በቅርቡ ቡሩንዲ ማጽደቁን በመግለጽ በቀጣይ አንድ አባል ሀገር ካጸደቀ ኮሚሽኑ እንደሚቋቋም ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በበኩላቸው፣ ጉባኤው በናይል ተፋሰስ ሀገራትና ማህበረሰብ መካከል ፍትሃዊ የውሃ ተጠቃሚነት እንዲኖር ያደርጋል።

ኢትዮጵያ የናይል ትብብር ማእቀፍን በመፈረም አህጉራዊ ውህደትና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲኖር ቁርጠኝነቷን አሳይታለች ብለዋል።

በጉባኤው ላይ የተፋሰሰ ሀገራት ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶችና ምሁራን ተገኝተዋል። በውሃ አስተዳደር ዙሪያ፣ የአየር ንረት ለውጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት ለዘላቂ ልማት በፍትሃዊነትና በምክንያታዊነት መጠቀም በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይቶች ይደረጋሉ።

በሞገስ ጸጋዬ
ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓም