በቀጣይ ሶስት አመታት ለማጠናቀቅ እየተሰራ የሚገኘው የአሶሳ ስታዲየም የግንባታ ሂደት አሁናዊ ገጽታ በፕሬስ ዐይን‼️
ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓም
ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️
ያለ ህዝብ ብቁ ተሳትፎ የሚከናወን ስራ ሙሉ ሊሆን አይችልም!
ሰላማችንን ዘላቂ እና ህዝባዊ መሰረት ያለው ለማድረግ ዛሬ አሰልጥነን ያስመረቅናቸው 11 ሺሕ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላትን ጨምሮ 341 ሺሕ የሠላም ሠራዊት አባላትን የከተማችን የሰላም ዘብ አድርገን አሰማርተናል።
ከ2013 ጀምሮ ሕዝባችንን በተደራጀ መልኩ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ማቀናጀት እና የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት ማድረግ መቻላችን እስካሁን ጋስገኙን ውጤታማ እና ስኬታማ ስራዎች በተጨማሪ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ሰላማዊ ማድረግ ችለናል።
ዛሬ የተመረቃችሁ የሰላም ሰራዊት አባላት ሕዝባችን የሰላሙ እና የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ባለቤትና ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆኑን በመረዳት በየአካባቢያችሁ የሰላምና የመሰረተ ልማቱ ዘብ በመሆን ህዝባችሁን በፍፁም ትህትና እና ፍቅር እንድታገለግሉ አደራ ማለት እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

የናይል ውኃን በፍትሀዊነት ለመጠቀም በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል
- አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የናይል ውሃን በፍትሀዊነት ለመጠቀም በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ትብብርን ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለፁ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በመተባበር የአፍሪካ ድንበር ተሸጋሪ የውሃ ሀብትን በፍታዊነት መጠቀም ላይ ትኩረት ያደረገው 3ኛው አፍሪ ራን የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በጉባኤ ላይ እንደገለጹት፣ የናይል ተፋሰስ ሀገራት በመተባበር በጋራ መልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቆጣጠር ያስፈልጋል። በተፋሰሱ ሀገራት መካከል የልምድ ልውውጥና በጋራ መመካከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የምትገነባው የዓባይ ግድብ ቀጣናዊ ውህደትንና በጋራ መልማትን እንደሚያጠናግር ገልጸዋል።
የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን ለማቋቋም አባል ሀገራት የናይል የትብብር ማእቀፍን ማጽደቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በቅርቡ ቡሩንዲ ማጽደቁን በመግለጽ በቀጣይ አንድ አባል ሀገር ካጸደቀ ኮሚሽኑ እንደሚቋቋም ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በበኩላቸው፣ ጉባኤው በናይል ተፋሰስ ሀገራትና ማህበረሰብ መካከል ፍትሃዊ የውሃ ተጠቃሚነት እንዲኖር ያደርጋል።
ኢትዮጵያ የናይል ትብብር ማእቀፍን በመፈረም አህጉራዊ ውህደትና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲኖር ቁርጠኝነቷን አሳይታለች ብለዋል።
በጉባኤው ላይ የተፋሰሰ ሀገራት ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶችና ምሁራን ተገኝተዋል። በውሃ አስተዳደር ዙሪያ፣ የአየር ንረት ለውጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት ለዘላቂ ልማት በፍትሃዊነትና በምክንያታዊነት መጠቀም በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይቶች ይደረጋሉ።
በሞገስ ጸጋዬ
ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓም

በኦሮሚያ ከ1 ሺህ 180 በላይ ኢንተርፕራይዞች ወደ ኢንቨስትመንት ተሸጋግረዋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሉ ባለፉት 10 ወራት ከአንድ ሺህ 180 በላይ ኢንተርፕራይዞች ወደተሻለ ኢንቨስትመንት መሸጋገራቸውን የኦሮሚያ ሥራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ኤባ ገርባ (ኢ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ቢሮው ኢንተርፕራይዞች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲሸጋገሩና ምርቶቻቸውን በስፋት እንዲያቀርቡ እየሠራ ነው፤ ባለፉት 10 ወራት አንድ ሺህ 182 ኢንተርፕራይዞች ወደ ኢንቨስትመንት ዘርፉ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
ኢንተርፕራይዞች አቅማቸውን በማሳደግ የተለያዩ ምርቶችን ወደማዘጋጀት መሸጋገራቸውን ጠቁመው፤ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና ማቀነባበሪያዎች፣ በአገልግሎትና በተለያዩ ዘርፎች እራሳቸውን በማሳደግ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በክልሉ በሚገኙ ወጣቶችና ኢንተርፕራይዞች አማካኝነት ከውጭ የሚገቡ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በሀገር ውስጥ ማዘጋጀት ተችሏል ብለዋል።
ቢሮው በየጊዜው ለሚሠሩ ቴክኖሎጂዎች የሙከራ መድረክ በማዘጋጀት ውጤታማነታቸው የሚለካ ሲሆን፤ በቀን እስከ ሰባት ኩንታል የሻይ ቅጠል ቆርጦ አድርቆ የሚያዘጋጅ ማሽን፣ የሩዝ ምርትን ሰብስቦ የሚያዘጋጅ ማሽን......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129948

የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች‼️
የ1445ኛው የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ አሽከርካሪዎች የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል፡፡
በዓሉን አስመልክቱ በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሶላት ስነ-ስርዓት ይካሄዳል፡፡
በዚህም፤
👉 ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
👉 ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ
👉 ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
👉 ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ፡፡
👉 ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
👉 ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
👉 ከ ጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ
👉 ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ
👉 ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
👉 ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ
👉 ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ
👉 ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ
👉 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ
👉 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ
👉 ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ
ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ/ም ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጠቁሟል።
ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡