Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

የሉሲ(ድንቅነሽ) ግኝት የሳይንሱን ማኅበረሰብ ብሎም መላውን አለም ስለምድራችን እና ስላሳለፈችው የሕይወት መልክ ለማወቅ ያስቻለ መሥራች ሁነት ነበር። ግኝቱ ብዙ ጥያቄዎችን የመለሰ ብዙ አዳዲስ ጥያቄዎችን ያነሳሳ ሲሆን በጥያቄዎቹም ለብዙ ምርምሮች መነሻ መሆኑ እስከዛሬ እንደቀጠለ ነው።

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓም
“ቀደምት የሠው ልጆች መገኛ የሆነችውን ድንቅ ሀገር እንድትጎበኙ ጥሪ አቀርባለሁ”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******
(ኢ ፕ ድ)

በመላው ዓለም የምትገኙ ሁሉ ቀደምት የሠው ልጆች መገኛ የሆነችውን ድንቅ ሀገር ኢትዮጵያን ጎብኙ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

“የድንቅ ግኝት ግማሽ ምዕት ዓመት” በሚል መሪ ሃሳብ የድንቅነሽ ቅሪተ አካል የተገኘበት 50ኛ ዓመት በዓል በቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ተከብሯል።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንቅ ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ በርካታ የዓለም ቅርሶች አሉ፤ ይህንን መጎብኘት ያስፈልጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡና በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መስህቦች አሏት፤ ባለፉት 5 ዓመታት በቱሪዝም ዘርፍ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።

ድንቅነሽ የተገኘችበት 50 ዓመት ሲከበርም ኢትዮጵያ እንደ ፕሮፌሰር ዮሐንስ ያሉ በዓለም ምርጥ የተባሉ የቅሪተ አካላት ግኝት ያላቸው ተመራማሪዎችን የያዘች ሀገር በመሆኗ በቀጣይ በዘርፉ ብዙ ምርምር ይደረጋል ብለዋል።

በመድረኩ የሉሲ ቅሪተ አካልን ያገኙት ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆንሰንና ኢትዮጵያዊው የቅሪተ አካላትና የሰው ዘር አመጣጥ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዮሐንስ ኃይለሥላሴ እንዲሁም የዘርፉ ተመራማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓም
👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ7 ነጥብ 02 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

አየር መንገዱ 17 ነጥብ አንድ ሚሊዮን መንገደኞችን አጓጉዟል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ፣ አየር መንገዱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 7 ነጥብ 02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል። የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ አድጓል።

በጀት ዓመቱ 17 ነጥብ አንድ ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዙን ገልጸው፤ 13 ነጥብ 4 ዓለም አቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብለዋል።

በጭነት 754 ሺህ 681 ቶን ማጓጓዙን ገልጸው፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ስድስት በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ አምስት ዓለም አቀፍ የመንገደኛ መዳረሻ በመጨመር የአለም አቀፍ በረራ መዳረሻዎችን 139 ማድረስ መቻሉን አስታውቀዋል።

በሄለን ወንድምነው

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ዛሬ ሃያ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎቻችን የትምህርት ጥራትን አስመልክቶ ባካሄዱት የኦን ላይን ስልጠና መክፈቻ ወቅት የትውልድ ቅብብል የተሳካ የሚሆነው እንደነርሱ ያሉ መምህራን በሚወጡት እጅግ ጠቃሚ ሚና መሆኑን ገልጫለሁ።

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት ⁉️
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከታች በተጠቀሱ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዝዎታል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪው ረቡዕ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
***
(ኢ ፕ ድ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪው ረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 58 (4) እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ሥነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 15 (1 እና 2) መሰረት ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡

በዚሁ መሰረት የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ለረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡

ስለሆነም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በዕለቱ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ በአስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ መተላለፉን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በደረሰዉ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸዉ ላጡ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት በጎፋ ዞን ሳዉላ ከተማ ተካሄደ።

ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ብድር አጸደቀ
**-
(ኢ.ፕ.ድ)

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ ለአራት ዓመት የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጽድቋል፡፡

አይ ኤም ኤፍ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል...!!

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑም 2.556 ቢሊየን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን እና በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን አላማው ያደረገውን የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸም የሚደግፍ የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት(ECF) አጽድቋል።

የአስፈጻሚ ቦርዱ ውሳኔም ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ የሚረዳትን እንዲሁም በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊየን SDR ወይም 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል ይሆናል።

በአራት ዓመቱ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት የሚደገፈው የመንግሥት የኢኮኖሚ ፕሮግራም የግል ዘርፉን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ ሁለገብ የፖሊሲ ፓኬጅን እንዲሁም የላቀ እና በይበልጥ አካታች የሆነ እድገትን ማምጣትይቻል ዘንድ ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግን ኢላማው ያደረገ ነው።

ማሻሻያው ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች/አባዎራዎች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ለማለዘብ ይቻል ዘንድ የማህበራዊ ሴፍቲ ኔቶችን ማጠናከርም የመንግሥት የማሻሻያ ፕሮግራም አንድ ወሳኝ ክፍለአካል ነው። ቁልፍ የሚባሉት ፖሊሲዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡

1) ውጫዊ ኢሚዛናዊንትን ለመፍታት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማስታገስ በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ዋጋ መሄድ፤

2) የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ግሽበትን መዋጋት፤

3) የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን በማሰባብሰብ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሕዝባዊ ወጪዎች ማዋል፤

4) ከውጪአበዳሪዎች ጋር የሚደረጉ ወቅታዊ የእዳ ሪስትረክቸሪንግ ስምምነቶችን በመፈጸም ጭምር የእዳ አከፋፈል ዘላቂነትን መመለስ እንዲሁም

5) ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ፋይናንሺያል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ የመንግሥት ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ አቋም ማጠናከር።

ፕሮግራሙ ከልማት አጋሮች የሚገኝ ተጨማሪ የገንዘብ አቅርቦትን በማፋጠን እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው የእዳ ሪስትረክቸሪንግ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ማዕቀፍ በመስጠት ረገድ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ብሄራዊ መታወቂያ ለመውሰድ ተመዝግበዋል
******
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ለመውሰድ የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ። በ364 የምዝገባ ጣቢያዎች አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወ/ሪት ቃልኪዳን አብርሃም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን በመዘርጋት ዜጎች እና ሕጋዊ ነዋሪዎች የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጡ እና አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መንገድ ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ ነው። በአሁኑ ጊዜም አገልግሎቱን ለሕዝቡ ተደራሽ ለማድረግ በ364 ጣቢያዎች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።

ብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መንገድ ማግኘት ከማስቻል ባለፈ በአገልግሎት ሰጪና ተቀባይ መካከል በሚኖር ግንኙነት ላይ እምነት እንዲዳብር፣ በግል እና በመንግሥት ተቋማት የማንነት ማረጋገጥ ሂደት በተቀላጠፈ መንገድ እንዲከናወን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133254