Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጓንዡ የሚያደርገውን ሣምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቻይና ጓንዡ የሚያደርገውን ሣምንታዊ በረራ ወደ 10 ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

ከዚህ በፊት ወደ ከተማዋ የሚያደርገው ሣምንታዊ የበረራ መጠን ሰባት መሆኑን አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

መስከረም 10 ቀን 2017 ዓም
ከበዓላት ጋር የተያያዙ የጉብኝት ጥቅሎች መዘጋጀታቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አሳወቀ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በመስከረም ወር የሚከበሩ የአደባባይ በዓላትን መሠረት ያደረጉ የጉብኝት ጥቅሎች (ፓኬጆች) መዘጋጀታቸውን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በመስከረም ወር ቀጣይ ቀናት መስቀል፣ ኢሬቻና የዓለም ቱሪዝም ቀን እንዲሁም የተለያዩ አካባቢዎች የዘመን መለወጫ በዓላት ይከበራሉ።

በመስከረም ወር የሚከናወኑ የተለያዩ በዓላት ለቱሪዝም ገቢ ዕድገት ያላቸውን ሰፊ ጠቀሜታ በመረዳትና ከክልሎች ጋር በመነጋገር የተለያዩ የጉብኝት ጥቅሎችን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=136968
በመዲናዋ ከቱሪዝም ዘርፍ ከ119 ቢሊዮን ብር በላይ ወደኢኮኖሚው ፈሰስ ለማድረግ እየተሠራ ነው
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በ2017 በጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ119 ቢሊዮን በላይ ብር ወደ ከተማው ኢኮኖሚ ፈሰስ ለማድረግ መታቀዱን የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ሳምሶም አይናቸው ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2017 ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ በማድረግ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ቱሪስቶች 119 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደከተማው ኢኮኖሚ ፈሰስ ለማድረግ ታቅዷል፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለፈው ዓመት የነበሩ ጥንካሬ እና ድክመቶችን....
https://press.et/?p=136961
በምርኩዝ መራመድ መቄዶንያን ከመርዳት ያልገታቸው አርበኞች
***************
(ኢ ፕ ድ)
......... እኛ አቅማችን ቢደክምም በምርኩዝ ብንራመድም ሞራላችን ግን መቄዶንያ የሚገኙ አቅመ ደካሞች ወገኖቻችን ለመርዳት በቂ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በውስጣችን ፍቅርና ሠላም ካለ ተካፍለን እንበላለን ብንታመምም የሚያሳክመን አናጣም ይላሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን ለእምነታቸው እና ለባሕላቸው ቦታ የሚሰጡ በመሆናቸው ይህን የመሰለ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል እና ኃላፊነት ተሰምቶት በርህራሄ የሚያገለግል የክብር ዶክተር ቢኒያምን ማግኘት ትልቅ ስጦታ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም እርስ በርስ በተገኘው አቅም በመረዳዳት......
https://press.et/?p=136950
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል
****
(ኢ ፕ ድ)

በ2017 ዓ.ም በሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል የሚታደሙ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ዘንድሮ ለሚከበረው የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ለ2017 ዓ.ም በከተማዋ በድምቀት ለሚከበሩት ኢሬቻና የመስቀል በዓል ከሦስት ወራት በፊት ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ያሉት አቶ ገዛኸኝ፤ በከተማው እንግዶችን የመቀበል ልምድና ተሞክሮዎች መሠረት በሆራ አርሰዲ በዓል......

https://press.et/?p=136963
ንግድ ባንክ ቪዛ ካርድን በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ ካርዶችን በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችላቸዉን ስምምነት ከቪዛ ኢንተርናሽናል ጋር ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳት አቤ ሳኖ እንደገለጹት ፤ባንኩ ከቪዛ ኢንተርናሽናል ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ አጋርነት ያለዉ ሲሆን የሚጠቀምባቸዉ ካርዶችም የቪዛ ኢንተርናሽናል ናቸው።

በዛሬዉ ዕለት ባንኩ ያደረገው ስምምነት ወደ ዉጭ የሚጓዙ ደንበኞች በውጭ ምንዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።

ስምምነቱ ለአምስት አመት የሚቆይ ሲሆን ቪዛ ለባንኩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

በመስከረም ሰይፉ
መስከረም 10 ቀን 2017 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️

በሰፊው የታረሰ የስንዴ ማሳችን። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለን ቁርጠኝነት ውጤት።

መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም
"ያሆዴ" ሠላምና አብሮነትን የሚያጸና በዓል ነው
- የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
"ያሆዴ" ሠላምና አብሮነት የሚያጸና በዓል መሆኑን የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ ገለጹ።

የ2017 ዓ.ም የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓልን ለማክበር የኦሮሞ ብሔረሰብን ወክለው የተገኙት የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት የያሆዴ በዓልን ለበርካታ ጊዜ ከብሔሩ ተዋላጆች ጋር ማክበራቸውን በመገልጽ በዓሉ የህዝቦችን ሠላምና አብሮነት ለማጽናት ከፍተኛ ሚና አለው።

በዓሉ የሀድያ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግበት ቂምና ጥላቻን የሚያርቅበት በመሆኑ ልዩ ስሜት ይፈጥራል ብለዋል።

የአርሲ አባ ገዳ ገሪባ ገልገሎ በበኩላቸው፦ በዓሉን ለማከበር በመገኘታቸው መደሠታቸውን ገልጸው የብሔሩ ተዋላጆች የኢሬቻ በዓል ከኦሮሞ ብሔረሰብ ጋር እንዲያከብሩ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ መከበር ይጀምራል።

በአማን ረሺድ (ከሆሳዕና)