Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️

በሰፊው የታረሰ የስንዴ ማሳችን። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለን ቁርጠኝነት ውጤት።

መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም
"ያሆዴ" ሠላምና አብሮነትን የሚያጸና በዓል ነው
- የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
"ያሆዴ" ሠላምና አብሮነት የሚያጸና በዓል መሆኑን የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ ገለጹ።

የ2017 ዓ.ም የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓልን ለማክበር የኦሮሞ ብሔረሰብን ወክለው የተገኙት የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት የያሆዴ በዓልን ለበርካታ ጊዜ ከብሔሩ ተዋላጆች ጋር ማክበራቸውን በመገልጽ በዓሉ የህዝቦችን ሠላምና አብሮነት ለማጽናት ከፍተኛ ሚና አለው።

በዓሉ የሀድያ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግበት ቂምና ጥላቻን የሚያርቅበት በመሆኑ ልዩ ስሜት ይፈጥራል ብለዋል።

የአርሲ አባ ገዳ ገሪባ ገልገሎ በበኩላቸው፦ በዓሉን ለማከበር በመገኘታቸው መደሠታቸውን ገልጸው የብሔሩ ተዋላጆች የኢሬቻ በዓል ከኦሮሞ ብሔረሰብ ጋር እንዲያከብሩ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ መከበር ይጀምራል።

በአማን ረሺድ (ከሆሳዕና)
ከሲዳማ ክልል ከ36 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ይቀርባል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በምርት ዘመኑ ከ36 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱን የሲዳማ ክልል ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማቅመም ባለሥልጣን አስታወቀ።

ዘንድሮ ወደ ውጭ ከሚላከው የቡና ምርት 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ይገኛልም ተብሏል።

የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በ170 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ቡና በስፋት ይለማል።

የቡና ምርታማነት የሚጨምሩ ፓኬጆችን በአግባቡ መጠቀም በተቻለበት በ1 ሄክታር 11 ኩንታል የቡና ምርት ይገኛል ያሉት አቶ መስፍን፤ በዘንድሮው የምርት ዘመንም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የቡና ምርት ለመሰብሰብ......

https://press.et/?p=137037
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️