Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ለሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል
****
(ኢ ፕ ድ)

በ2017 ዓ.ም በሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል የሚታደሙ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ዘንድሮ ለሚከበረው የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ለ2017 ዓ.ም በከተማዋ በድምቀት ለሚከበሩት ኢሬቻና የመስቀል በዓል ከሦስት ወራት በፊት ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ያሉት አቶ ገዛኸኝ፤ በከተማው እንግዶችን የመቀበል ልምድና ተሞክሮዎች መሠረት በሆራ አርሰዲ በዓል......

https://press.et/?p=136963
ንግድ ባንክ ቪዛ ካርድን በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ ካርዶችን በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችላቸዉን ስምምነት ከቪዛ ኢንተርናሽናል ጋር ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳት አቤ ሳኖ እንደገለጹት ፤ባንኩ ከቪዛ ኢንተርናሽናል ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ አጋርነት ያለዉ ሲሆን የሚጠቀምባቸዉ ካርዶችም የቪዛ ኢንተርናሽናል ናቸው።

በዛሬዉ ዕለት ባንኩ ያደረገው ስምምነት ወደ ዉጭ የሚጓዙ ደንበኞች በውጭ ምንዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።

ስምምነቱ ለአምስት አመት የሚቆይ ሲሆን ቪዛ ለባንኩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

በመስከረም ሰይፉ
መስከረም 10 ቀን 2017 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️

በሰፊው የታረሰ የስንዴ ማሳችን። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለን ቁርጠኝነት ውጤት።

መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም
"ያሆዴ" ሠላምና አብሮነትን የሚያጸና በዓል ነው
- የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
"ያሆዴ" ሠላምና አብሮነት የሚያጸና በዓል መሆኑን የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ ገለጹ።

የ2017 ዓ.ም የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓልን ለማክበር የኦሮሞ ብሔረሰብን ወክለው የተገኙት የሠላም አምባሳደር ቁፋ ጎቤ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት የያሆዴ በዓልን ለበርካታ ጊዜ ከብሔሩ ተዋላጆች ጋር ማክበራቸውን በመገልጽ በዓሉ የህዝቦችን ሠላምና አብሮነት ለማጽናት ከፍተኛ ሚና አለው።

በዓሉ የሀድያ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግበት ቂምና ጥላቻን የሚያርቅበት በመሆኑ ልዩ ስሜት ይፈጥራል ብለዋል።

የአርሲ አባ ገዳ ገሪባ ገልገሎ በበኩላቸው፦ በዓሉን ለማከበር በመገኘታቸው መደሠታቸውን ገልጸው የብሔሩ ተዋላጆች የኢሬቻ በዓል ከኦሮሞ ብሔረሰብ ጋር እንዲያከብሩ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ መከበር ይጀምራል።

በአማን ረሺድ (ከሆሳዕና)
ከሲዳማ ክልል ከ36 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ይቀርባል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በምርት ዘመኑ ከ36 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱን የሲዳማ ክልል ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማቅመም ባለሥልጣን አስታወቀ።

ዘንድሮ ወደ ውጭ ከሚላከው የቡና ምርት 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ይገኛልም ተብሏል።

የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በ170 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ቡና በስፋት ይለማል።

የቡና ምርታማነት የሚጨምሩ ፓኬጆችን በአግባቡ መጠቀም በተቻለበት በ1 ሄክታር 11 ኩንታል የቡና ምርት ይገኛል ያሉት አቶ መስፍን፤ በዘንድሮው የምርት ዘመንም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የቡና ምርት ለመሰብሰብ......

https://press.et/?p=137037