በታይላንድ በእስር ላይ የነበሩ 38 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በሥራ ቅጥር ሽፋን በሕገ ወጥ ዓለም አቀፍ የሰው አዘዋዋሪዎች ወደ ማይናማር ተወስደው ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ መንግሥት ጥረቱን መቀጠሉን ገልጿል፡፡
ከሰሞኑ በሕንድ ኒውዴልሂ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሲዮንም ወደ ታይላንድ ልዑክ በመላክ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንዲለቀቁ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ማይናማር ውስጥ ከነበሩት መካከልም ከስቸጋሪ ሁኔታ አምልጠው ወደ ታይላንድ የሚገቡ ስደኞች ሕጋዊ ሠነድ ባለመያዛቸው ለእስር ተዳርገው ነበር መባሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ይህን ተከትሎም ሚስዮኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ባደረገው ጥረት 38 ኢትዮጵያዊን ከእስር ተለቅቀው ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡
ጥር 16 ቀን 2017 ዓም

👍11👏3🙏2❤1
❤6👎2👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ያየነውን ለማሳየት እንተጋለን"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ሀገር ናት፤ ቢሰራባቸው በዓለም እያየን ከምንደነቅባቸው ስፍራዎች በዕጅጉን የላቁ ውበት ያላቸው ስፍራዎች በሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
#ጅማ_አባ_ጅፋር_ቤተመንግስት_ዕድሳት #ገበታለትውልድ
ጥር 17 ቀን 2017 ዓም

👍9👏3
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍4
አትሌት ማርታ የ3000 ሜትር ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች
***
(ኢ ፕ ድ)
በካዛኪስታን ዋና ከተማ አስታን በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች።
አትሌት ጉሚ ሽቶ እና አክሱማዊት አምባዬ ውድድሩን ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡
አትሌት ማርታ ርቀቱን ለመጨረስ 8 ደቂቃ ከ39 ሰኮንድ የወሰደባት ሲሆን ውጤቱም ከ18 ዓመት በታች ባሉ አትሌቶች ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ በክብረ ወሰንነት መያዙን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመለክታል።

❤11👍4👏1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ከህጻንነታቸዉ ጀምሮ በኮልፌ የወንዶች ልጆች ማሳደጊያ እና በቀጨኔ የሴቶች ማሳደጊያ ማዕከል ካሳደግናቸው ልጆቻችን መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ አብቅተን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ለመፈጸም ያበቃን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን። ሙሽሮች እንኳን ደስ ያላችሁ!
እንኳን ፈጣሪ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ረድቷችሁ ለዚህ ለተባረከ እና ለተቀደሰ የህይወታችሁ ምዕራፍ ቀን አደረሳችሁ። መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ!
የከተማ አስተዳደራችን ወላጅ ለሌላቸዉ ወላጅ እና ቤተሰብ በመሆን አሳድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁ ከማድረግ በተጨማሪ በቀጣይ የህይወታቸው ምዕራፍ የስራ እድል በመፍጠር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ዉጤታማ ህይወት እንዲኖራቸው እየተመኘን በዚህ በተቀደሰ ስራ የተሳተፉትን ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
በድጋሚ መልካም ጋብቻ፤ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ።
ጥር 18 ቀን 2017 ዓም

👍5👏1
ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ ልንከተላቸው የሚገቡ ዐሥር አቅጣጫዎች
******
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች አስቀመጡ።
በዚህም፤
1. ቡናን በጥራትና በስፋት ማምረት፤ በተለይ የጥሪኝ ቡና ስፔሻሊቲን ማስፋፋት፣
2. ልዩ ልዩ ኦርጋኒክ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን በልዩ ብራንድ ጂማ ላይ ማቀነባበር፣
3. የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረትና በመጠቀም፣ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን ማምረት፣ ማሸግና መላክ፣
4. የከብት ወተትና ሥጋ፤ እንዲሁም የዶሮ ዕንቁላል እና ሥጋን በጥራትና በብዛት በማምረት አሽጎ መላክ፣
5. ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ በሚመጥን መልኩ ማቀነባበር፣ ማሸግና መላክ፣
6. ልዩ ልዩ የእንጨት ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በፋብሪካዎች በጥራት ማምረት፣
7. የሸክላ ፋብሪዎችን በማስፋፋት፤ ለወለል፣ ለግርግዳ እና ለጣራ የሚያገለግሉ የግንባታ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ፣
8. የጂማንና የአካባቢዋን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ጸጋዎችን በማልማትና በማስተሣሠር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፣
9. የጂማ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅበትን ሰላሙን እና እንግዳ ተቀባይነቱን ማጽናት፣
10. ጎጂ ማኅበራዊ ልማዶችን እና ደካማ የሥራ ባህልን ማሻሻል፣
ጥር 2017 ዓም

👍8❤6👏1