Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት የሚመጥን አመራር መስጠት ይገባል
- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት የሚመጥን ትጋትና ቁርጠኝነት የተላበሰ አመራር መስጠት እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤና የሥራ መመሪያ ተቀብለዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖ መሾም የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት ሃላፊነትና አደራ መጎናጸፍ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የረጅም ዘመን ግንኙነትን የሚያጠናክር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል።

በተጨማሪም አሜሪካ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባት ሀገር በመሆኗ በኢትዮጵያ ልማትና እድገት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አምባሳደሩ ጠንካራ ስራ ማከናወን እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

በመሆኑም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም አሜሪካ ትልቅ እሳቤን የሚጠይቅ ዲፕሎማሲ የሚከናወንባት መሆኑን ታሳቢ ያደረገ አመራር እንዲሰጡም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ወዳጅን ማብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ፣ በቀጣናው ሰላምና ትብብርን ለመፍጠር ጠንካራ ዲፕሎማሲ እና የውጭ ግንኙነት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ለጀመረችው የፖለቲካና ምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ውጤታማነት ከአሜሪካ ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በቀጣይ በሰላም፣ በጸጥታና በዳያስፖራ ጉዳዮች ዙሪያ ያቀደቻቸውን ግቦች ለማሳካት አምባሳደር ብናልፍ ሚናቸው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አማካኝነት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍51👏1
የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተማሪዎች የተሰሩ የስዕል ጉብኝት‼️

#የብልፅግና_ፓርቲ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍31👏1
“ከቃል እስከ ባህል”

የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ጀምረናል፤ የኢትዮጵያም ብልጽግና ጉዞ አይቀሬ ነው"

- የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍3👏1