Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተማሪዎች የተሰሩ የስዕል ጉብኝት‼️

#የብልፅግና_ፓርቲ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍31👏1
“ከቃል እስከ ባህል”

የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ጀምረናል፤ የኢትዮጵያም ብልጽግና ጉዞ አይቀሬ ነው"

- የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍3👏1
"የደረጃ ሀሳብ የሌለው ፖለቲካ ፓርቲ የፈለገውን ማፍረስ ቢችልም ለውጥን ለመምራት ይቸገራል"
- የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******
(ኢ ፕ ድ)

የአንድ ፓርቲ አስኳሉ ሀሳብ ነው፤ የደረጃ ሀሳብ የሌለው ፖለቲካ ፓርቲ የፈለገውን ማፍረስ ቢችልም ለውጥን ለመምራት ይቸገራል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባዔው መክፈቻ ስስርዓት ላይ እንደገለጹት፤ ብልጽግና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ለመጀመሪያ አገር በቀል የሆነ እሳቤ ነድፎ የመጣ ፓርቲ ነው፡፡

ሀሳብ የለሽ ፖለቲከኞች፣ፓርቲዎች ለአጭር ጊዜ ድል የረጅም ጊዜን መከራን ያመጡብናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የአንድ ፓርቲ አስኳሉ ሀሳብ ነው፤ የደረጃ ሀሳብ የሌለው ፖለቲካ ፓርቲ የፈለገውን ማፍረስ ቢችልም ለውጥን ለመምራት ይቸገራል ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብልጽግና ሊያፈርስ የሚፈልገው ኋላቀር አስተሳሰቦችና ልምምዶች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡

ሊያፈርስ የሚያስበውን አልቆ መገንባትንም አስቀድሞ የሚያስብ ነው። ፒያሳን ማፍረስ ሳይሆን ፒያሳን አልቆ መገንባ የብልጽግና መለያው ነው ብለዋል፡፡

ለውጥ መፍጠር ብቻውን ለውጥ ለመምራት የሚያስችል ብቃት እስካልፈጠረ ድረስ የተሟላ የፓርቲ ህልውና አይኖረውም።

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶችና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከመላ ሀገራችን የተውጣጡ ጉባኤተኞች ተገኝተዋል።

ከአስራ አምስት ሀገራት እህት ፓርቲዎች የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

"ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች የሚተላለፍበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በማርቆስ በላይ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
3👍2👏1
#አምስቱ_አንኳር_ጉዳዮች‼️

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብልጽግና ባህል መሆን አለባቸው የሚላቸውን አምስት አንኳር ጉዳዮች ጠቅሰዋል።

አምስቱ አንኳር ጉዳዮችም‼️

✍️ ማወቅ - ሀገርን፣ ባህልን፣ ቋንቋን፣ ስነምግባርን፣ ህዝብን፣ ሀብትና ተፈጥሮን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

✍️ ማላቅ - ያለንን ጸጋ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ማሻሻል ፡፡

✍️ መፍጠር - በተለምዶ የምናየው መነጽር ባለፈ በአዲስ መነጽር መመልከት መቻልና በጭንቅላት ጨርሶ መጀመር ነው፣

መፍጠር ማለት ለግል ጥቅም ሳይሆን ለወል ወይም ለብሄራዊ ጥቅም መጀገን ነው፣

✍️ መፍጠን - በፍጥነት ስራዎችን መከወን ካልተቻለ ኢትዮጵያ በተለመደው መንገድ ልትጓዝ ትችላለች፤ በልጽጋ ግን ለዓለም መታየት አትችልም፣

✍️ ማስተሳሰር -ህዝብን ፣ሃሳብን ፣ውጤትን ማስተሳሰር ያስፈልጋል፣

በዳግማዊት አበበ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍53
በተወረወሩብን የዕንቅፋት ድንጋዮች ኢትዮጵያን ገንብተንበታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
******
(ኢ ፕ ድ)

በተወረወሩብን የዕንቅፋት ድንጋዮች ኢትዮጵያን ገንብተንበታል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ዐቅሟ ትልቅ፤ ጸጋዋ ብዙ፤ ዕድሏ ሰፊ፤ መሆኑን ዐውቀናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን ነው፤ ትውልድ ሲጠይቀው የኖረውን የኢትዮጵያ ብልጽግና እውን እናደርገዋለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍72