Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“ትርክት ከሚገነባባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ክህሎት ነው”
- ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

******

(ኢፕድ)

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ ዶ/ር በክህሎት የበቃ የሰው ሃይል ለአንድ ሀገር ምን አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ጹሁፍ አቅርበዋል፡፡

ትርክት ከሚገነባባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ክህሎት መሆኑን ገልጸው፤ ጥራት ያለው ክህሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ አቅረቦት መር ከሆነው ወደገበያ መር ለመቀየር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ለማሳካት የክህሎት ሚና ትልቅ ነው ያሉት ዶክተር ተሻለ፤ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ ስብራትን መጠገን የሚያስችል ክህሎት መር ሥራዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት።

ከኢንዱስትሪው እና ከግል ሴክተሩም ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በባህሪው ተግባር ተኮር መሆኑን አንስተው፤ ተግብር ተኮር ስልጠናን እውን ለማድረግ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡

እንደ ዶክተር ተሻለ ገለጻ፣ ብቁ የሰው ሃይል ማለት በእውቀት፣ በክህሎት እና በአስተሳሰቡ ዝግጁ የሆነ ነው። የመንግስትና የገል ተቋማት አጋርነታቸውን በማጠናከር እና ክህሎት ልማት ላይ በትኩረት በመስራት በሀገሪቱ ብቁ የሰው ሀይል ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

የስልጠናን ጥራት ለማምጣት ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን ትስስር አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በአጫጭር ስልጠና ከሶስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች በመደበኛው ደግሞ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች የሚያልፉ ቢሆንም፤ የክህሎት ልማቱን ከዚህ በላይ ለማሳደግ በትብብር መስራትን ይጠይቃል፡፡

በዘርፉ ያለን ሰዎችም የክህሎት ጥራትን ለማምጣት ያደረግነው ጥረት እና የማስተዋወቅ ስራው በቂ እንዳልሆነ ገልጸው፤ ለክህሎት ልማት ትኩረት መስጠት እና ለሙያና ሙያተኞች የምንሰጠውን ክብርም ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በሄለን ወንድምነው

መጋቢት 1/2017ዓ.ም
👍21
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍51👏1
ጊዜው የሚጠይቀው አርበኝነት ለሙያ እና ሙያተኛ ክብር መስጠት መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ገለጹ
- የትርክት መዛባት የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን ጎድቶታትል ብለዋል

****

(ኢፕድ)

ጊዜው የሚጠይቀው አርበኝነት ለሙያ እና ሙያተኛ ክብር መስጠት መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የትርክት መዛባት የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን እንደጎዳውም ተናግረዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር እንደገለጹት፤ ክህሎት በህብረት እና በአንድነት ሆነን ሀገር የምንሰራበት መንገድ ነው፡፡

ጊዜው የሚጠይቀው አርበኝነት ለሙያ እና ሙያተኛ ክብር መስጠት መሆኑን ገልጸው፤ ዜጎች ወርቃማ እጃቸውን ብሩህ አዕምሯቸውን ተጠቅመው የሚያደርጉት የችግር ፈቺነት ተግባር አርበኝነት ነው ብለዋል።

አሁን ያለንበት ወቅት የተዛቡ ትርክቶችን የምንጋፈጥበት ሲሆን፤ ከተዘቡ ትርክቶች አንዱ በሙያ እና ሙያተኞች ያለው ግንዛቤ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተዘባ ትርክትን ለማስተካከል በኮሚኒኬሽንና በተግባር አሰናስሎ በማስኬድ ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አይቻልም፣ አይሆንም አትንካ የሚሉት ጉዳዮች የፈጠራን በር የሚዘጉ በመሆናቸው፤ ልጆችን ከልጅነታቸው ጀምሮ ለፈጠራ ያላቸውን ሀሳብ በመደገፍና በማበረታት ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ምርታማነት ለማሳደግ እና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚ ለመገንባት ክህሎት መግቢያ በር መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ክህሎት ችግር ፈቺና መፍትሄ አመንጪ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ እያንዳንዱ አምራች ኢንዱስትሪ የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለመገንባት በትብብር መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡

ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጓቸው አዳዲስ የስልጠና መስኮች እንዳሉ ገልጸው፤ ትብብርን በማጠናከር ፍላጎት መር የሰው ሃይል ለማቅረብ ይሰራል ብለዋል፡፡

በልምድ እውቀትና ክህሎት ያገኙ ሰዎች እውቅና የሚያገኙበት ስርዓት በተያዘው ዓመት ይፋ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ልንከባከበውና ልንጠብቀው የሚገባ ሀገር በቀል እውቀቶች እንዳሉ ገልጸው፤ 26 የሚደርሱ ሀገር በቀል እውቀቶች ተለይተው ካሪኩለም ተቀርጾላቸዋል ሲሉ አንስተዋል፡፡

በቀጣይም በሀገር በቀል እውቀቶች የማሻሻያ ስራዎች የሚሰራ ሲሆን፤ ይህም ሙያና ሙያተኞችን ለማክበር ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አዲስና ነባር ቢዝነሶችን ማጣመር እና ስታርት አፖችን ማጠናከር የግድ እንደሚል ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ የሚቻለው ስራን በክህሎት ሲመራ በመሆኑ ያለንን እውቀት ያለምን ቁጠባ ሀገር ላይ ኢንቨስት እናድረግ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


በሄለን ወንድምነው
👍74🤮2
“የባሕር በር ጥያቄ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው”- ዕምሩ ገመቹ (ዶ/ር)
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን፤ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካና ዓለም አቀፍ ግኑኙነት መምህር እምሩ ገመቹ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የሌላ ሀገር ወደብ መጠቀም ከድንገተኛ ቀውሶች ጋር በተያያዘ ዋስትና እንደማይኖረውም አስታውቀዋል።

እምሩ ገመቹ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ ሀገሪቱ ያለችበት የቀይ ባሕርና የህንድ ውቂያኖስ አካባቢ ካለው ጂኦፖለቲካል ስትራቴጂክ አኳያ፤ በርካታ ሀገራት አካባቢውን የመቆጣጠር ፍላጎት አላቸው፤ ይህም እንደ ሀገር የደህንነት ስጋት ይዞ ሊመጣ የሚችል ነው።

ሀገሪቱ የባሕር በር ባለቤት ብትሆን ፤ ብሄራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ በተጓዳኝ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ የሚኖራት አበርክቶ ከፍ ያለ እንደሚሆን የጠቆሙት መምህሩ፤ በዓለም አቀፍ መድረክ የሚኖራት ተደማጭነትን ይጨምራል።

የኢንቨስትመንት ስበት በመፍጠር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እንዲያለሙ መደላድል ይፈጠራል፤ የተለያዩ ድጋፎችን እንድታገኝ ይረዳል፤ ይህም ብሄራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ አንጻር አስተዋጽኦ ይኖረዋል። https://press.et/?p=147260
👎2👏2
"ዛሬ በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን ተመልክተናል። መትጋት፥መሥራት፥ ማየት ከቻልን፣ ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች። ይህንን ስራ አጠናክረን እንድንቀጥል አደራ እላለሁ"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👏2👍1
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት እስከ አሁን ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር አምርቷል
****
(ኢ ፕ ድ)

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት እስከ አሁን ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር ማምረቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስታወቀ።

ፋብሪካው የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ(ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ እና የተቋሙ አመራሮች የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የተቋሙን አፈጻጸም መገምገምና የመሰረተ ልማት አቅሙን መፈተሽ እንደሆነ ተገልጿል።

ፋብሪካው በበጀት ዓመቱ ማብቂያ ለማምረት ያቀደውን የአንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር እቅድ ለማሳካት በትክክለኛ መስመር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። ፋብሪካው ከዋና ምርቱ በተጓዳኝ የግብርና ምርቶችን በማምረት ለሰራተኞቹና ለአካባቢው ማህበረሰብ እንቁላል፣ አሳና አትክልቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራሮች ኩባንያው በግብርናው መስክ እያሳየ ያለው ለውጥ፣ የሜካናይዜሽን አጠቃቀምን በማሳደግ፣ የእርሻ ስራዎችን በማስፋፋት፣ በአቅም ግንባታ እና ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመጠቀም እያስመዘገበ ያለው ውጤት መልካም እንደሆነ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ መረጃ ያመለክታል።

#ወንጂሸዋ

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓም
👍8👏1