Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍71
"የአንጎላ ፕሬዝዳንት ማኑኤል ጎንካልቬስ ሎሬንቾን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ እላለሁ። ውይይታችን የሁለትዮሽ ጉዳዮችን ለመዳሰስ እንዲሁም ክቡር ፕሬዝደንቱ በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነታቸው ቁልፍ አኅጉራዊና ባለ ብዙወገን ጉዳዮችን ለመመልከት ችለናል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓም
👍1
ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ተፈራርመዋል።

የመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለረጅም ዓመታት ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል።

አሁን ላይ የነበረውን ሁለንተናዊ ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውም ተገልጿል።

በወታደራዊ አቅም ግንባታ ስልጠና፣ በተሞክሮ ልውውጥ፣ ሽብርተኝነትን በመከላከል እና በሌሎች ተያያዥ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

በሩዋንዳ መከላከያ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄነራል ብርጋዲየር ጄኔራል ፓትሪክ ካሪታዋ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ረጅም ጊዜያትን ያስቆጠረ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በችግራችን ጊዜ ፈጥና የደረሰችልን ሀገር ነች ያሉት ብርጋዲየር ጄኔራሉ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ ጉዳዮች ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓም
👍4👏1
"ዛሬ ከሰዓት ከኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡሩኖ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓም
👏1
ኢትዮጵያና ኩባ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረሙ
******
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያና ኩባ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መሥራት የሚያስችሏቸውን የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ሀገራት በባህል፣ በስፖርት፣ በቴክኖሎጂ፣ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፎች በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ከኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር የባህል ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዋል።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር መይሊን ሱዋሬዝ አልቫሬዝ ፈርመውታል።

የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ፤ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልጸዋል። የሁለቱ ሀገራት የረጅም ዘመናት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያና ኩባ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረው እ.አ.አ ከ1975 ጀምሮ  መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓም
👍32👏2🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአንጎላ ፕሬዝዳንት ጆኣኦ ማኑኤል ጎንካልቬስ ሎሬንቾን ጋር የነበራቸው ቆይታ‼️

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓም
👍62👏2
አዲስ ዘመን https://press.et/?p=147469
ዘኢትዮጵያ ሄራልድ https://press.et/herald/?p=111933
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✍️ ማንኛውም ጎረቤት በኃይማኖት አይለይም፣

✍️ እንዴት ለካህኑ አዛን ናፈቃቸው፣

✍️ ዓዛን ካልሰማን ዛሬ ዓዛን ያልተደረገበት ምክንያት ምንድነው የሚለው እኔን ይጨንቀኛል፣ ሙስሊሙ እንደዛው፣

✍️ ዛሬ ቅዳሴ የለም ብለው ይጠይቃሉ፣

👉 የአብሮነትና የሰላም ምድር ከተሰኘ ዘጋቢ ፊልም የተወሰደ https://youtu.be/EefsdA9mZvE?feature

#አብሮነት #ስለኢትዮጵያ #ዓዛን #ቅዳሴ
👍2👏1
ብልጽግና ፓርቲ የተከተለው አካሄድ የጸረ ሰላም ቡድኖችን ዓላማና ሕልውና ማክሸፍ አስችሏል

- አቶ ይርጋ ሲሳይ
****
(ኢ ፕ ድ)

ብልጽግና ፓርቲ የተከተለው በመርሕ ላይ የተመሰረተ አካሄድ የጸረ ሰላም ቡድኖችን ዓላማና ሕልውና ለማክሸፍ አስችሏል ሲሉ በፓርቲው የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ገለጹ፡፡

በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩና አካባቢውን  ለማተራመስ ሲጥሩ በነበሩ ፀረ-ሰላም ቡድኖች በርካታ ፈተናዎችን ሲያስተናግድ መቆየቱን ጠቁመዋል።

በሕዝቡ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክልሉ አስደናቂ ለውጦችን እውን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
👍7
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👏2👍1