Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተደረገው ሁለተኛው የኢፍጣር ምሽት ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 200 የሚሆኑ ስደተኞች ተስተናግደዋል። ተሳታፊዎችም ብሔራዊ ቤተመንግሥት ጎብኝተዋል።
👏148👍5
ኢትዮጵያ ከምትገዛቸው ከ800 በላይ የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ የምታመርተው ከ100 በታች ነው

👉 በግዢ መዘርዝር ከተያዙ መድኃኒቶች ውስጥ 20 በመቶው አቅራቢ የላቸውም
****
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ከምትገዛው ከ800 በላይ የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ የምታመርተው ከ100 በታች መሆኑን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ለኢፕድ እንደገለጹት፣ የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት መሰረት ያደረጉ 800 መድኃኒቶች በመንግስት ጤና ተቋማት ቢመረጡም በኢትዮጵያ የሚመረተው ከመቶ በታች ነው፡፡

አገልግሎቱ መድኃኒቶችን ከሀገር ውስጥና ከውጪ አገራት ገዝቶ እንደሚያቀርብ ጠቅሰው፣ በግዢ መዘርዝር ከያዛቸው መድኃኒቶች 20 በመቶው አቅራቢ የሌላቸው፣ 30 በመቶው መድኃኒት አንድ አቅራቢ ብቻ እንዳላቸውና ቀሪዎቹ ቢሆኑ የተሻለ አቅራቢ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት መጠንን ማሳደግ ስትራቴጂካዊ መፍትሄ መሆኑን ጠቅሰው፣መድኃኒቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ኢንቨስትመንትን መሳብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱ ከሚገዛው መድኃኒት በገንዘብ መጠን ሲታይ የዛሬ አራት አመት የአገር ውስጥ መድኃኒት ድርሻ ከ20 በመቶ በላይ እንደነበረ በመግለጽ፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደ 8 በመቶ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን በተደረገው ማሻሻያ ወደ 36 በመቶ ከፍ ማለቱንና አሁን ደግሞ ወደ 41 እያደገ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዘርፉ ኢንቨስትመንት ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

በማርቆስ በላይ

መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓም
👎5👍4🤔1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👎21👍1
ኢትዮጵያ በታሪክም ይሁን አሁናዊ ሁኔታ የባሕር በር ጥያቄዋ ተቀባይነት እንዳለው ያሳያል
****
(ኢ ፕ ድ)
..... በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኤፍ ኤስ ኤስ በተባለች የጦር መርከብ ላይ ከ1977 እስከ 1983 ዓ.ም የመንግሥት ለውጥ ድረስ ሲያገለግሉ የቆዩት ፒቲ ኦፊሰር ሳሙኤል አረጋ ገብረማርያም የባሕር በር ጥያቄ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ደኅንነት የማስጠበቅ ጉዳይ ጭምር ነው ይላሉ።

ፒቲ ኦፊሰር ሳሙኤል ለኢብድ በሰጡት ማብራሪያ፤ የባሕር በር ባለቤትነት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት። ብዙ ጊዜ ሲነሳ የምንሰማው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ነው። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ብትሆን የደኅንነት ዋስትና ያላት ሀገር እንድትሆንም ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

አንድ ሀገር የትኛውም አይነት የወደብ አማራጭ ቢኖረው ልክ በራሱ እንደሚተዳደር የባሕር በር ወይም ወደብ ያህል ደኅንነቱና ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ሊያገኝ አይችልም። የራስ የባሕር በር ካለ የሚወጣውም የሚገባውም ነገር ደኅንነትም ሆነ ምስጢራዊነት ለሌላ ወገን ሊተላለፍ አይችልም።

በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ እቃዎችም ይሁኑ ወደ ውጭ የሚላኩት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሌሎች ሀገራት ይሁንታንና ፍተሻን የሚያልፉ መሆናቸውን ይናገራሉ።

ይህም ሊጠበቁ የሚገባቸውን ምስጢሮች በማውጣት ሕዝብንና ሀገርን ለአደጋ የሚያጋልጥ ይሆናል። እንደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያላትና የፍላጎት ማደግ ባለባት ሀገር የሚያስከትለው ጉዳት የከፋ ይሆናል። በመሆኑም ኢትዮጵያ ከ30 ዓመት በፊት እንደነበረችው ሁሉ አስፈላጊውንና ተገቢውን ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በመጠቀም የባሕር በር ባለቤት እንድትሆን መሥራት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

‹‹የባሕር በር ጥያቄ መነሳት አዲስ የሚሆንባቸው ዜጎች እንዳሉ እያየን ነው›› ያሉት ፒቲ ኦፊሰር ሳሙኤል፤ ይህ ሆን ተብሎ ትውልዱ ላይ ሲሠራበት የቆየ የማዘናጊያ አስተሳሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።

የአሁኑ ትውልዱ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጠቀምና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ፣ በሰጥቶ መቀበል መርሕ ኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤት ሊያደርግ የሚችልበት ዕድል........https://press.et/?p=147482
👍84
"የጣና ዳር ንግሥቷ፣ ባለዘንባባዋ ሙሽራ፣ የቱሪዝም አስኳሏ ባህር ዳር ስራ ላይ ነች"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሰገን ጥሩነህ
***

ፍፁም የሰላም አየር፣ የዓይንና የመንፈስ ማረፊያ ውብ ሥፍራ የታደለችው ባህር ዳር ከመዝናኛ እስከ ግዙፍ የንግድ ስፍራዎቿ በእንቅስቃሴ ተሞልተዋል፤ ሀገሬው ከጧት እስከ ማታ ሥራ ላይ ነው፡፡

የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ከልጅ እስከ አዋቂ በልዩ ልዩ ስፖርቶች ደምቀዋል፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ግዙፉ የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ከተማዋን የስፖርት ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጋት ይሆናል።

ሀገሬው በሥራ የደከመ አካሉንና አዕምሮውን ለማደስ ስፖርት ሲሠራ፣ በመዝናኛ ማዕከላት ሲዝናና፣ በዘንባባዋ ጥላ ስር አረፍ ሲል፣ በጣና ዳርቻ ሰብሰብ ብሎ ሲጫወት፣ በምሽት በእግር ሲንቀሳቀስ ማየት ልብን ሀሴት ያወርሳል።

ወቅቱ የዐቢይና የረመዳን አፅዋማት የሚፆሙበት ነው። የከተማዋ ምዕመን ሰርክ ወደ መስጂድና ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሲተምም ማየት መንፈሳዊ ኩራትን ይፈጥራል።

ውቧ ከተማ ልማቷን እያፋጠነች፣ ፍፁም የሰላም ድባብ፣ እረፍት አልባ የልማት ሥራ፣ ሞቅ ያለ የመዝናኛና የንግድ እንቅስቃሴ የሚታይባት ሆናለች።

ባየነው የሠላም ንፋስ የልማትና የሥራ ጥድፊያ እንዲሁም የቱሪዝም መነቃቃት ተደሰተናል። የተጀመሩ ስራዎችን ዓይናችንን ሳንነቅል በተገቢው ጥራት እንዲጠናቀቁ ክትትላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓም
👍7👏1
የባሕር በር ጥያቄ የመጪውን ትውልድ ሕልውና የሚወስን ነው
****
(ኢ ፕ ድ)
የባሕር በር ጉዳይ የመጪውን ትውልድ የመኖር እና ያለመኖር ሁኔታ የሚወስን ስለሆነ ከወዲሁ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ሲሉ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሃሳቡ ተስፋ ገለጹ፡፡

መምህር ሃሳቡ ተስፋ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሚያስተዳድራት በራሷ መንግሥት ድጋፍ አድራጊነት የነበራትን የባሕር በር እንድታጣ መደረጓ ሁሌም የሚያስቆጭ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ የባሕር በር ከሉዓላዊ ግዛትነቱም በላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጥቅሙ የሕልውና ጉዳይ ያደርገዋል፡፡

አንድ ሀገር የባሕር በር አለው ማለት ሌሎች የባሕር በር ካላቸው የዓለም ሀገራት ጋር ይዋሰናል ማለት ነው ያሉት መምህሩ፤ ይህ ደግሞ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የንግድ ልውውጥ እና ማኅበራዊ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እንደ መምህር ሃሳቡ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፤ በዚያው ልክ ፍላጎቱና የንግድ እንቅስቃሴውም አድጓል፤ ዓለም አቀፍ ግንኙነቱና ኢኮኖሚያዊ ትስስሩም ጨምሯል፡፡

እያደገ ከሚሄደው የሕዝብ ቁጥርና ፍላጎት አንጻር፤ የባሕር በር በተለይም የመጪውን ዘመን ትውልድ የመኖርና ያለመኖር ሁኔታ የሚወስን በመሆኑ ከወዲሁ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባዋል።
👍13👏2😢2