Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍10👏1
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ እና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ተከታትለው በመግባት ወርቅ እና ብር ሜዳልያ አሸነፉ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ ባለው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ፍጻሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ እና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ተከታትለው በመግባት ወርቅ እና ብር ሜዳልያ አሸንፈዋል።

በሴቶች 800 ሜትር አትሌት ንግስት ጌታቸው ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።
👍247👏3
ኢትዮጵያ ታሪኳም ሆነ ሕልውናዋ ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)

ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ስጦታ በመሆኑ ታሪኳም ሆነ ሕልውናዋ በሙሉ ከቀይ ባሕር ጋር እንደሚያያዝ የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ሙሳ ሼኮ ገለጹ፡፡

የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ሙሳ ሼኮ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ስጦታ በመሆኑ የኢትዮጵያ ታሪክና ሕልውና በሙሉ ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ቀይ ባሕር እንደ ዓይንና እግር አንድ አካሏ ስለሆነም የኢትዮጵያ ታሪክ ከቀይ ባሕር ተነጥሎ ሊጻፍ አይችልም ብለዋል፡፡

ቀይ ባሕርን ማጣት ማለት ከኢትዮጵያ አካል አንዱን ማጣት ማለት መሆኑን ጠቁመው፤ ቀይ ባሕር ሲባል ባሕርነቱ ወይም መውጫ በር መሆኑ ብቻ አይደለም የተፈለገው፡፡ በቀይ ባሕር ላይ ከ 120 በላይ ሚሊተሪ ቤዞች ይገኛሉ፡፡ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ተርኪዬ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ፣ ጃፓንና ሌሎች ሀገራት ከሰባት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት አቆራርጠው መጥተው ቀይ ባሕር ላይ ሰፍረው ኢትዮጵያ አፍንጫዋ ስር የሚካሄደው ነገር አይመለከታትም ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡

አንድ ሰው ቡሬ ተራራ ላይ ቆሞ ቀይ ባሕርን መመልከት እንደሚችል የሚናገሩት አቶ ሙሳ፤ የባሕር በር ከኢትዮጵያ ድንበር 60 ኪሎ ሜትር ብቻ ነው የሚርቀው...https://press.et/?p=148192
👍13👎2👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
3👍2
ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን 213ሺህ 820 ኩንታል የሰሊጥ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል
****
(ኢ ፕ ድ)

ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን 213ሺህ 820 ኩንታል የሰሊጥ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በአካባቢው የሰፈነው ሰላም የግብርና ምርቶችን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

የመምሪያው ሃላፊ አቶ አይቻው ታረቀኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በዞኑ በ2016/17 ምርት ዘመን ከ300ሺህ ኩንታል በላይ የሲሊጥ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ በታህሳስ ወር ከተሰበሰበው የሰሊጥ ምርት 213ሺህ 820 ኩንታል ማቅረብ ተችሏል፡፡

በቀጣይ ወራትም የሰሊጥ ምርትን ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ እንዲቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ከምዕራብ ጎንደር ዞን የተመረተ 33ሺህ ኩንታል ሰሊጥ ለማዕከላዊ ገቢያ መላኩን ተናግረዋል፡፡

በምርት ዘመኑ ከሰሊጥ በተጨማሪ 250ሺህ ኩንታል አኩሪ አተር ለሀገር ውስጥ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ታቅዶ ከዚህ ውስጥ ከ103ሺህ ኩንታል በላይ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የማሾ ምርትም በተመሳሳይ ሁኔታ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ በተያዘው እቅድ መሰረት እስካሁን ሁለት ሺህ ኩንታል መቅረቡን አስረድተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በ2016/17 ምርት ዘመን በአምስት ወረዳዎች ከ40ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መልማቱ ታውቋል።

መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓም
👍71
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጎማ ሪሳይክል ማሽን የሰሩ

ይህ ማሽን ጥቅም ላይ የዋሉ ጎማዎችን በመጠቀም ለህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ ለrubberized አስፓልትና የእግረኞች መንገድ ታይልስ ለመስራት የሚውል ማቴሪያልን የሚያመርት ነው። ይህንን ማሽን እንዲሰራ መነሻ የሆነውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ”ክህሎት ኢትዮጵያ” ጉብኝት ባደረጉ ጊዜ የሰጡት አቅጣጫ ነው።

አስራ አምስት ማሽኖችን በውስጡ የያዘው ፕሮጀክቱ የማሽኑን ዋና ዋና አካላት ለማምረት 2 ወራት ብቻ ፈጅቷል። ማሽኑ 500 ኪሎ ግራም በሰዓት የማምረት አቅም አለው።

#ችግር_ፈቺ_እጆች
#PMOEthiopia
👏9👍52
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
Photo
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግርኛ ቋንቋ ያስተላለፉት መልዕክት

ጻውዒት ጥቆማ ፕረዚደንት ጊዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ
ንመላእ ህዝቢ ትግራይ

ከምዝፍለጥ በመሰረት ሕገ መንግስቲ ፈዴሪኢ 62(9)፣ ከምኡውን በመሰረት ስምምዕነት ፕሪቶሪያን ኣብ ክልላት ምእታው ጣልቃ መንግስቲ ፈዴራል ንምድንጋግ ብዝወጸ አዋጅ ቁጽሪ 359/1995 መሠረት፣ ከምኡውን ምምስራት ኣሳታፊ ግዚያዊ ምምሕዳር መንግስቲ ትግራይ ብዝምልከት ዝተደንገገ ናይ ቤት ምኽሪ ሚንስተራት ደንቢ ቁጥር 533/2015 መሠረት ዝቆመ ጊዚያዊ ምምሕዳር ትግራይ ንክልተ ዓመታት ኣብ ስራሕ ምጽንሑ ይፍለጥ።

በመሰረት ኣወጅ 359/1995 ኣንቀጽ 15(3) ጊዚያዊ ምምሕዳር ንክልተ ዓመት ጥራይ እዩ ክጸንሕ ዝኽእል። ጭቡጥ ምክንያት እንተሃልዩ ግና ዕድመ እቲ ጊዚያዊ ምምሕዳር ምንዋሕ ይከኣል። በቶም ቅድም ክብል ዝተገለጹ ሕግታትን ውዕሊ ፕሪቶሪያ ዝቆመ ጊዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ ኣብ ውሽጢ ኽልተ ዓመት ናይ ጊዝያዊ ምምሕዳር ዕማማቱ አጻፊፉ ሓላፍነቱ ብህዝቢ ንዝተመረጸ መንግስቲ ከረክብ ይግባእ ነይሩ።

ይኹን እንበር ጊዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ ዝተውሃቦ ቁልፊ ዕማማት ኣብ ዝተወሰነሉ ጊዜ ከጻፍፍ ኣይከኣለን። ካብቶም ቁልፊ ዕማማት ሓድ ምርጫ ንምከያድ ዘኽእል ምቹእ ኩነታት ምፍጣር እዩ። እዙ ዕማም እዙይ ካብቶም ዘይተጻፈፉ ዕማማት ሓደ ብምዃኑ ዕድመ ጊዝያዊ መንግስቲ ሕጊ ብምምሕያሽ ብሓደ ዓመት ምንዋሕ ግድን ኰይኑ አሎ።

መንግስቲ ፈዴራል ኣብ መሬት ዘሎ ጭቡጥ ኩነታት ኣብ ግምት ብምእታው ዕደመ ጊዚያዊ መንግስቲ ንምንዋሕ፣ ፖለቲካዊ፣ ምምሕዳራውን ናይ ሕግን ስራሕቲ ኣብ ምክንዋን ዝርከብ ኰይኑ ምስእዙይ ተኣሳሲሩ ሓዱሽ ፕረዚደንት ጊዝያዊ ምምሕዳር ምሻም እውን ኣድላይ ኰይኑ አሎ።

ከም ዝፍለጥ በመሰረት ደንቢ ቁጽሪ 533/2015 አንቀጽ 3(2) ፕረዚደንት ጊዚያዊ ምምሕዳር ምሻም ናይ ቀደማይ ሚስትር ሓላፍነት እኳ እንተኮነ ህዝቢ ብዝተማለአ መገዲ ብምርጫ መራሕቱ ክሳብ ዝመርጽ ኣብ ጥቆማ ፕረዚደነት ጊዝያዊ ምምሕዳር ተሳትፎ ክህልዎ ኣድላይ ብምኳኑ፤ ንዕማማት ጊዝያዊ ምምሕዳር ብብቕዓት ክፍጽሙ ይከእሉ እዮም ፣ ሰላምን ድሕንነትን እቲ ክልል ከራጋግፁ ይከእሉ እዮም ትብልዎም ሕጹያት ኣብታሕቲ ናብ ዝተገለጸ ናይ ቀደማይ ሚነስትር ቢሮ ኢሜል አደራሻ ከብ ሎሚ ጀሚርኩም ጥቆማኹም ክትልእኹ ከምትኽእሉ ነፍልጥ።

መጠቆሚ ኢመይል info@pmo.gov.et
👍4
መላው የትግራይ ህዝብ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዕጩ ጥቆማ እንዲሰጡ ተጠየቀ
*******
(ኢ ፕ ድ)

መላው የትግራይ ህዝብ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጥቆማ እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

በደንብ ቁጥር 533/2015 አንቀፅ 3(2) መሰረት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን መሾም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊነት እንደሆነም ተገልጿል።

ጥቆማውንም በኢሜል info@pmo.gov.et መሰጠት እንደሚችሉም ተገልጿል።

በፌዴራል ሕገ መንግሥት አንቀጽ 62(9) እና አዋጅ ቁጥር 359/1995 የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ መግባት፣ በፕሪቶሪያ ስምምነትና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 533/2015 መሠረት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመታት ሲሠራ ቆይቷል።
6👍2
ጣልያን ከኢትዮጵያ ጋር በቡና ዘርፍ ያላትን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገለጸች
*******
(ኢ ፕ ድ)

የጣልያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ጋር በቡናው ዘርፍ ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት 400 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳለች።

የልማት ኤጀንሲው ከእ.አ.አ 2006 አንስቶ በኢትዮጵያ የቡና ልማት የእሴት ሰንሰለት መፍጠር ላይ እየሰራ ይገኛል።

የኤጀንሲው ዳይሬክተር ሚሼል ሞራና የቡናው ዘርፍ ጣልያን ከኢትዮጵያ ጋር ትብብሯን ማስፋት ከምትፈልግባቸው መስኮች አንዱ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ጣልያን የግሉ ዘርፍ በኢትዮጵያ የቡና ልማት ውስጥ ያለው ተሳትፎ እንዲያድግ ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልግ አመልክተዋል።

በዚህም የጣልያን የግሉ ዘርፍ ከሀገር በቀል አምራቾች ጋር በማስተሳሰር ለኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ ሙያዊ ድጋፍ የመስጠት ፍላጎት እንዳለም አንስተዋል።

በጣልያን መንግስት ድጋፍ እየየተገበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ የእሴት ሰንሰለትን የማጠናከር ፕሮጀክት ውጤቶች እየተገኙበት ነው ብለዋል።

ለኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ እድገት ጣልያን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅሰው የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ እንዲጠናከር ቁርጠኛ መሆኗንም አመልክተዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ በቡና ኤክስፖርት ከፍተኛ እምርታ አሳይታለች። በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ስምንት ወራት ወደ ተለያዩ ሀገራት ከላከችው ቡና ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓም
👍7👏2