Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኦሮሚያ ክልል አንድ ሺህ 402 የግብርና ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ
****
(ኢ ፕ ድ)

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አንድ ሺህ 402 የግብርና ትራክተሮችን ከነመለዋወጫው ለአርሶ አደሮች፣ ለህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ አስረክቧል።

ርክክቡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሰራ ኃላፊዎች በተገኙበት መከናወኑን ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ሀላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ናቸው።

የክልሉ መንግስት ምርትና ምርታማነትን ለማሳድግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ትራክተሮቹ የክልሉ መንግስት የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት ለያዘው ውጥን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል።

መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓም
5👍2👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍32
"ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ያላትን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
*****
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል ከወንድሜ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይዘውት የመጡትን መልእክት ተቀብያለሁ ብለዋል።

ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በደቡብ ሱዳን ወቅታዊውን የጸጥታና የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት፣ ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም ገልጸዋል።

መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓም
👍81
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

በኢፌዴሪ ህገመንግስት 62 (9)፣ በአዋጅ 359/1995 አንቀጽ 15(3) እና ደንብ ቁጥር 533/2015 እና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ላበረከቱት፣ በተለይ የተገኘውን ሰላም ለማፅናት ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቄቄና አመራር የፌዴራል መንግስት እውቅና እንዳለውና በቀጣይ ስራዎችም ተቀራርበን እንደምንሰራ እያረጋገጥኩ ለነበራቸው ቆይታ አመሰግናለሁ።

መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓም
👍17😁75
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የአማራጭ ሳይሆን ምርጫ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የባሕር በር ተጠቃሚነቷን ቀደም ሲል በተፈጠረ የፖለቲካ ችግርና የዲፕሎማሲ አያያዝ ምክንያት ብታጣም
አሁን ላይ የቀረበው ጥያቄ የአማራጭ ሳይሆን ምርጫ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ሌተናል ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀል ተናገሩ።

ሌተናል ጀነራል ዮሐንስ ለኢፕድ እንደገለፁት፣ ትውልዱ የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ መስራት ይገባል።

የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ሁሉም ወገን በበጎ መልኩና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ሊመለከተው ይገባል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ተጠቃሚ ብትሆን ጥቅሙ ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር እንደሆነ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ሳትጠቀም ከ30 ዓመታት በላይ አሳልፋች። ይህ በዝምታ የሚታለፍ ጉዳይ እንዳልሆነ ገልጸው፤ በተለይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባት ተናግረዋል።

ሁሉም የባሕር በር ተጠቃሚ ሀገራት በፍትሃዊ መንገድ ቢጠቀሙ ሁሉንም አትራፊ ያደርጋል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፤ የባሕር በር ጉዳይ ገበያ የሚፈጥር፣ ደህንነትን የሚያረጋግጥና ለኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት በመሆኑ የትውልዱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው ብለዋል።

የባሕር በር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሰላማዊ መንገድ እስከ መጨረሻው ድረስ መሄድ እንዳለበት ጠቁመው፤ ይህ  ጥያቄ  ምላሽ እንዲያገኝ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል... https://press.et/?p=149038
👍11
“የዓባይ ግድብ የዘመናት ሕልም የተፈታበት የትውልድ ኩራት ነው”
– አቶ ዛሂድ ዘይዳን ኣል-ሐረሪ የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ
******
(ኢ ፕ ድ)

የሕዳሴ ግድብ ያለፉት ትውልዶች የዘመናት ሕልም የተፈታበት፤ የትውልዱ ኩራት እንደሆነ የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ መሥራችና ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዛሂድ ዘይዳን ኣል-ሐረሪ አስታወቁ።

በግድቡ ላይ የተያዘውን አንድ ዓይነት አቋም በሌሎች ሀገራዊ ልማቶች ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ መሥራችና ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዛሂድ ዘይዳን ኣል-ሐረሪ ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ ግድቡ ያለፉት ትውልዶች የዘመናት ሕልም የተፈታበት የትውልድ ኩራት ነው። የውሃ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሕይወት አጀንዳም ነው።

ኢትዮጵያውያን ስለወንዙ ያላቸውን የቁጭት ቃል በዘፈን በሥነቃልና በሌሎችም ኪነጥበባዊ ሥራዎች ሲገልጹ መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ ዛይድ፤ አሁን ላይ ወደ ተግባር ተገብቶ ግድቡ ከፍጻሜ ጫፍ መድረሱ የሕዝባችንን ጽናት የሚያመላክት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

በወንዙ ላይ ስለሚገነባ ግድብ ሲወራ የነበረው በዚህ ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤ የአሁኗ፣ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ሳትፈጠር በፊትም እንደነበር ጠቁመዋል። በወንዙ ላይ ግድብ ለመገንባት የሚጓጉ፣ ምኞት የነበራቸው ትውልዶች እንደነበሩም ገልጸዋል፡፡

ግንባታው ከየትኛውም ፖለቲካዊ አቋምና አመለካከት በላይ የሆነ የውሃ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሕይወትም ጭምር ነው ያሉት አቶ ዛሂድ፤ የትኛውንም ዓይነት የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው አካላት የሀገር ጉዳይ በሆነው በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ የተያዘውን አንድ ዓይነት አቋም አስጠብቀው ማስቀጠል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡https://press.et/?p=149110
👍121
"ዛሬ ጠዋት ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተገናኝተን በቁልፍ ቀጠናዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
7
ጣና ነሽ ጀልባ ከ3 ወራት በኋላ ጎርጎራ ትደርሳለች
*****
(ኢ ፕ ድ)

ጣና ነሽ ጀልባ ከጂቡቲ ዶራሌ ፈርጀ-ብዙ ወደብ ወደ አገር ቤት ዛሬ ጠዋት ጉዞ ጀምራለች። በአማካኝ ከ3 ወራት በኋላ ጎርጎራ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።

የጣና ነሽ ጀልባ 150 ሜትሪክ ቶን ክብደት የምትመዝን፣ 38 ሜትር ርዝመት ያላት እና 200 ተሳፋሪ የመያዝ አቅም ያላት ሲሆን ለመዝናኛ አገልግሎት በመጠቀም እያደገ ያለው የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትልቅ አስተዋጾ የምታበረክት ይሆናል።

ጀልባዋ ከጅቡቲ ተነስታ በዲኪል-ካላፊ መንገድ የምትንቀሳቀስ ሲሆን፣ በአማካይ ከ7 ቀናት በኋላ ኮሪደሩን ታቋርጣለች ተብሎ ይጠበቃል። ለጉዞ የሚሆን የዝቅተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የሃይል ተሸካሚ መስመሮች በኮሪደሩ የሚቋረጡና ተለዋጭ መንገድ የተዘጋጀላቸው ሲሆን፣ ሁለት ተጨማሪ ጎታች ተሽከርካሪዎችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ተመድቦ ከጀልባዋ ጋር ጉዞ ጀምሯል።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍64
ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ተረከቡ
**
ሌ/ጄኔራል ታደ
ሰ ወረደ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን በዛሬው ዕለት ተረከቡ።

ሌ/ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

ዛሬ በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግርና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራምም ተከናውኗል።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍8👏1
ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ሲረከቡ የፈረሙት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር የተልዕኮ አፈጻጸም የቃል ኪዳን ሰነድ‼️

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍6
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶርያን ስምምነትና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል። የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ጊዜያዊ መንግሥቱ መቀጠለ አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል።

ዛሬ በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩንና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል።

ሌ/ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናችው። ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችንና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው።

አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምንት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላምና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍12