Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የህንድን አዲስ ታሪክ የከተቡት ታላቅ ሰው
+++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | እ.ኤ.አ በ1943 በቫድናጋር በምትገኝ አንዲት ጠባብ ቤት ውስጥ የተወለዱት ናሬንድራ ሞዲ፣ የዛሬው የፖለቲካ ቁመናቸው ትላንት ካለፉበት የሕይወት ውጣ ውረድ የተቀዳ ነው።

በቤተሰብ የሻይ መሸጫ ውስጥ እየረዱ፣ የሻይ ማፍያው እንፋሎትና የኑሮ ፈተና እያጠነከራቸው ያደጉት ሞዲ፣ ለድሆችና ለተገፉት ያላቸው ርኅራኄ መነሻው ይኸው ትሑት የቤተሰብ አስተዳደጋቸው ነው።

ገና በአፍላነታቸው ከመጻሕፍት ጋር የነበራቸው ጥብቅ ቁርኝትና በሂማላያ ተራሮችና ገዳማት ውስጥ ያሳለፉት መንፈሳዊ ሕይወት "ለሌላው መኖር" የሚለውን ትልቅ እውነት እንዲረዱ አድርጓቸዋል።

ሞዲ በፖለቲካው ዓለም ውስጥ ያሳዩት ብቃትና ጥንካሬ በሥራ የተገነባ ነው እየተባለም ይነገርላቸዋል።

በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከዴልሂና ከጉጂራት ዩኒቨርሲቲዎች ካገኙ በኋላ፣ በ1980ዎቹ የሕንድ ሕዝቦች ፓርቲን (BJP) ተቀላቅለዋል።


ከ2001 እስከ 2014 ድረስ በጉጃራት ግዛት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ያሳለፏቸው 13 ዓመታት፣ በግዛቲቱ ላይ ያመጡት ታላቅ ለውጥ ለሀገር መሪነታቸው እንደ ትልቅ ድልድይ ሆኖ አገልግሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ዲሲፕሊን የሚደነቅ ነው። ንጋት 11 ሰዓት ላይ ሥራቸውን በመጀመር እስከ እኩለ ሌሊት የሚዘልቁት ሞዲ፣ የሥራ መርሃቸው ብበዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።

ለእሳቸው መንግሥት በሰዎች ሕይወት ውስጥ እንቅፋት ሳይሆን የሥኬት ድልድይ መሆን አለበት።

ይህ በቢሮክራሲ ያልታጠረና ሕዝብን በቀጥታ የሚያገለግል አመራራቸው፣ ሕንድን ወደ ቀድሞ ክብሯ የመመለስ ራዕይ የሰነቀ ነው።

በዳግማዊት ግርማ
#ኢትዮጵያ #ህንድ #ጋዜጣ_ፕላስ #ወዳጅነት #ዲፕሎማሲ #ናሬንድራ_ሞዲ #ሕንድ
2
በውሃ ላይ የሚያርፉ አውሮፕላኖች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ነው
+++++++++++++++++++++++++

ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቱሪዝም አገልግሎት የሚውሉና በውሃ ላይ ማረፍ የሚችሉ አውሮፕላኖችን በቀጣይ ጥቂት ወራት ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለፁት፤ አየር መንገዱ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግና በቂ የአውሮፕላን ማረፊያ በሌላቸው የቱሪስት መዳረሻዎች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ በውሃ ላይ የሚያርፉ አውሮፕላኖችን በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባል።

አውሮፕላኖቹ በመጋቢትና ሰኔ ወራት ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡና የሙከራ አገልግሎት እንደሚጀምሩም ገልጸዋል።

እነዚህ አውሮፕላኖች በውሃም ሆነ በመሬት ላይ ማረፍ የሚችሉ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በቅርቡ የሚጀመረው የሙከራ አገልግሎት ስኬታማ ከሆነ ተጨማሪ አውሮፕላኖች እንደሚታዘዙ አስረድተዋል።

ይህም ወደ ቱሪዝም መዳረሻዎች በአውሮፕላን ለመጓዝ ለሚፈልጉ መንገደኞች ትልቅ አማራጭ እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #አየር_መንገድ #ቱሪዝም #አቪዬሽን
6👍3
ከአውድ ውጪ የተሰራጨ መረጃ
+++++++++++++
#የፕሬስ_መረጃ_ማጣሪያ- ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዲጂታል መታወቂያ ይዘው የሚታዩበት ፎቶግራፍ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር ተመልክተናል። ይሁን እንጂ ይህ ትክክለኛ ፎቶግራፍ አለመሆኑን የኢፕድ የመረጃ ማጣሪያ አረጋግጧል። https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0k5kskAzdQifV2J7McFNfY9WcxogXbS7U9vMDrJaVVgFctNSzXkt1QCZrnQFmT44fl&id=61550238885521&sfnsn=mo

#fakeimages  #fakeNewsAlert  #የፕሬስ_መረጃ_ማጣሪያ
የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ባለፈው አንድ አመት እየሰራንባቸው የቆየነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶች በመቀጠል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

የሃሳብ ልውውጣችን የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻችንን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጠናዊ መረጋጋትና ልማት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር።

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
9
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ መሐሙድን ያደረጉት አቀባበል #PMOEthiopia
5
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል። በዛሬው እለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ አስጀምረናል።

ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር፤ በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች ናቸው።

እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

#DigitalEthiopia2030
5