Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ጊቤ 3 የኃይል ማመንጨት ጣቢያ ከአምስት ሺህ 230 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ አመንጭቷል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የጊቤ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አምስት ሺህ 230 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ማምረት መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሰታወቀ።
የኃይል የማመንጨት አፈፃፀሙ ከዕቅድ በመቶ ብልጫ ያለው አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡
የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ሰሙ እንደገለፁት በ2014 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 4 ሺህ 900 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ለማመንጨት አቅዶ 5 ሺህ 230 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ በማምረት የዕቅዱን 4 በመቶ ብልጫ አስመዝግቧል፡፡
ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ19 በመቶ ብልጫ እንዳለው አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡
በመስከረም ወር የማመንጫ ዩኒቶችን ሊያስቆሙ የሚችሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችሉ የመለዋወጫ ዕቃዎች መገዛታቸው ጣቢያው ከዕቅዱ በላይ ኃይል እንዲያመነጭ አስችሏል ብለዋል።
የጣቢያው የጥገና ክፍል ኃላፊ አቶ ንጉሴ ማሙሻ በበኩላቸው ለዩኒቶቹ ተከታታይነት ያላቸው የጥገና ሥራዎች በወቅቱ መከናወናቸው የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ከዕቅዱ በላይ ኃይል እንዲያመርት እገዛ አድርጓል ብለዋል፡፡
ተቋሙ የኃይል ማመንጫ ጣቢያው የሚያቅዳቸውን ዕቅዶች ከግብ እንዲያደርስ የመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት ግዢ ሊፋጠንና የስታፍ ፕላኑን የሚመጥን የሰው ኃይል እንዲሟላ ኃላፊዎቹ ጠይቀዋል፡፡
የጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ከ40 እስከ 50 በመቶ እየሸፈነ የሚገኝና ኢኮኖሚውን በመደገፍ በኩል አስተዋፅኦው የጎላ እንደነበር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርተው በተገኙ ከ33 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ቢሮው አሰታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርተው በተገኙ ከ33 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደረዊ እርምጅ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለጹት 17 ሺህ 424 ማስጠንቀቂያ ፣14 ሺህ 285 የታሸጉ፣ 260 የተሰረዘ ንግድ ፈቃድ፣ 107 የታገደ ንግድ ፈቃድ ፣ 120 ከትስስር የወጡ ንግድ ድርጀቶች፣ አንድ 495 ከተፈቀደው የልኬት መጠን በታች በመለካት ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል።
በርካታ የንግድ ማህበረሰብ በቅንነት እያገለገሉ የህብረተሰቡን ችግር ለማቃለል መስራታቸውንና ከ12 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችም ሚዛኖቻቸውን ወደ ዲጅታል መቀየራቸውን ተናግረዋል።
የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የተለያዩ ህግ የማሰከበር ስራ እየሰራ በመሆኑ ህብረተሰብ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
ከንግዱና ከሸማቹ ማህበረሰብ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት ግንዛቤ በመፍጠርና ህገ-ወጥነትን የመከላከል ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የዓለም ባንክ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ከአምስት ሚሊዮን በላይ ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ የገንዘብ ድጋፍ ማጽደቁን አስታወቀ።
የዓለም ባንከ ትናንት ባወጣው መግለጫው ላይ እንዳስታወቀው፤ በጦርነቱ ምክንያት በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ሀብት ንብረታቸው ወድሟ፤ የህዝብ መገልገያ የሆኑ ተቋማትና ንብረቶችም በተመሳሳይ ወድመዋል፤ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሴቶችና ህጻናትም ለጾታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል።
ኢትዮጵያ ይህንን ችግር ለመቋቋም እያደረገች ያለውን ጥረት ለማገዝና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ባንኩ የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታውቋል።
ድጋፉ ለማህበረሰቡ አስቸኳይ የእለት ደራሽ ፍላጎቶች፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና ለተያያዥ ማህበረሰብ አቀፍ ጉዳዮች የሚውል መሆኑንም ባንኩ ገልጿል።
የባንኩ ፕሮጀክት በመነሻነት ተግባራዊ የሚደረገውም በአፋር፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያና ትግራይ አካባቢዎች መሆኑም ተብራርቷል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በመጋቢት ወር ብቻ ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በመጋቢት ወር ብቻ ከ27 ነጥብ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ የገቢዎች ሚኒስቴር አሰታወቀ ።
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እንዳስታወቁት፣ የተሰበሰበው ገቢ የዕቅዱ 99 ነጥብ 67 በመቶ ማሳካት ተችሏል። ከ2ዐ13 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር 29 ነጥብ 11 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል።
ገቢው በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ የተሰበሰበ በመሆኑ ጥሩ አፈፃፀም ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህም ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ምንም ዓይነት ምክንያት ሳያሳብቡ በወቅቱ ግብራቸውን አስታውቀው በሚከፈሉ ግብር ከፋዮቻችን መልካምፈቀደኝነት በመኖሩ፤ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት በመቻላቸው እንዲሁም አጋር አካላትና ሕዝቡ እውነተኛ ድጋፍ በማድረጉ ነው።
በመሆኑም በ3ቱም የጋራ ጥረት የመጣ ውጤት በመሆኑ በራሴና በገቢዎች ሚኒስቴር ሥም ከልብ እያመሰገንኩ በቀሪ ሦስት ወራትም የመጋቢትን ወር አፈፃፀም እንድንደግመው ድጋፋችሁ እንዳይለየን የአክብሮት ጥሬዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ አስነሳላችኋላሁ በማለት ጉቦ ሲቀበል የነበረ መርማሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥባቸው በተደረጉ ንብረቶች ላይ ግለሰቦችን "እግድ አስነሳላችኋላሁ" በማለት ጉቦ ሲቀበል የነበረ መርማሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሙስና ወንጀል በተጀመረ ምርመራ ምክንያት ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በፍርድ ቤት የንብረት እግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥባቸው የተደረጉ ግለሰቦችን እግድ አስነሳላችኋላሁ በማለት ጉቦ ሲቀበል የነበረ መርማሪ በተቋሙ አመራሮችና በግለሰቦቹ ጥቆማ በፖለስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በግለሰቡ መኖሪያ ቤቱ በተደረገ ብርበራ 420 ሺህ የተገኘ ሲሆን በድርጊቱ ተሳታፊ በሆኑ ሌሎች ግለሰቦች ላይ ምርመራ ቀጥሏል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን በማጋለጥ የህግ የበላይነትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍና መብቱን በህጋዊ መንገድ ብቻ በማስከበር የወንጀለኞች መጠቀሚያ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ ሚኒስቴሩ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የእስራኤል የልዑካን ቡድን የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዱ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የእስራኤል የፓርላማ አባላት እና የጤና ባለሙያዎች ቡድን በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዱ፡፡
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት ትስስር ከዲፕሎማሲ ባለፈ ነው ያሉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የክልሉ ጤና ተቋማት የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ ነው።
ጉዳቱን መልሶ በመገንባት የተሟላ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከየአቅጣጫው ለሚደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የኢትዮጵያና የእስራኤል የፓርላማ አባላት፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ፣ የእስራኤል ቆንስላ ፅ/ቤት የጎንደር ቅርንጫፍ ዳይሬከረተር አቶ አዳነ ተድላ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ጉዳት የደረሰባቸው ዞኖች የጤና ተቋማት ኃላፊዎች በመድረኩ ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የኢትዮጵያ የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት የኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ ፖስኮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት ለተያዘው ዕቅድ የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ አሰታወቁ።

ሚኒስትሩ ከኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባቀረቡለት ግብዣ መሰረት በብረት ምርትና ፋብሪካ ግንባታ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፋቸውን ለመስጠት ከመጡት ታዋቂው የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ፖስኮ የጥናት ቡድን አካል የሚሆን ሲሆን ኩባንያው በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል።

በቅርብ ጊዜያትም የአዋጭነት ጥናት፣ የፋብሪካ ተከላና የሰው ሀብት ልማት ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ከማዕድን ሚኒስቴር ሙያተኞች ጋር ይፋዊ ስራ መጀመሩ የማዕድን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ለመጪው የፋሲካ በዓል የዘይት አቅርቦትና ስርጭት በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ንግድ ቢሮ አስታወቀ
******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የዘይት አቅርቦትና ስርጭት በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ከዘይት አቅራቢ ድርጅቶችና ባለ ድረሻ አካላትጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የግብይት ሰንሰለቱን በጠበቀና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲሚሰራጭም ተገልጸዋል።

የንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ፣ የዘይት አቅራቢዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸውና የዘይትን ምርት ስርጭት ከወዲሁ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ማቅረብ እንዳለባቸው ፤የአቅርቦትና የስርጭት ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ስርጭቱ በተስተካከለ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑንም አክለው አስረድተዋል፡፡

የዘይት አቅራቢዎችም በበኩላቸው በቢሮው በተቀመጠላቸው አቅጣጫ ለመስራትና ከወዲሁ ከፋሲካ በዓል በፊት በሸማች ህብረትስራ ማህበራት በኩል ምርቱን ለማሰራጨት የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱ ተጠናቋል ።

ንግድ ቢሮ የሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት በተለይም ስኳርና ዱቄት ለፋሲካ በዓል በተገቢው መንገድ ለማህበረሰቡ እንዲደርሱ እየሰራ መሆኑም ተመላክቶዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ሁሉም ወገን ለአገሪቱ ሰላምና ለዜጎች ደህንነት በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀስ ተጠየቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል የሚደረገው እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲቆምና ሁሉም ወገን ለአገሪቱ ሰላምና ለዜጎች ደህንነት መጠበቅ በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀስ የገዳ አባቶች ህብረት ጸሐፊና የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ጥሪ አቀረቡ።

አባ ገዳ ጎበና ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ በአገሪቱ በየቦታው የሚስተዋለው የሰላም እጦትና ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ መፍትሄ ካልተሰጠው አገር ከማፍረስ አልፎ የዜጎችን የመኖር ህልውና አጠያያቂ ያደርጋል።

በሰላም እጦት ምክንያት ከኢትዮጵያ በእድገታቸው የሚበልጡ አገራት ትላላቅ ከተሞቻቸው መወደማቸውን አይተናል። ስለሆነም ስለአገራችን የሰላም ጉዳይ ሁላችንም ልንጨነቅ ይገባልም ብለዋል።

በሚፈጠረው ችግር ከሁሉም በላይ ንጹሃን ዜጎች ኢላማ ስለሚሆኑ የትኛውንም አለመግባባት በጠረጴዛ ዙሪያ እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ የመንግሥት ድርብ ኃላፊነት ነው ያሉት አባገዳ ጎበና፤ አንዳንድ ምሁራንና ፖለቲከኞች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በሚያስተላልፉት ከፋፋይ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70816

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
የሰዎችን ሕይወት በማጥፋትና ዜጎችን በማፈናቀል የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት እንደማይቻል ተጠቆመ
****************
(ኢ ፕ ድ)

የንጹሃን ሰዎችን ሕይወት በማጥፋትና ዜጎችን ከቀያቸው በማፈናቀል የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት እንደማይቻል ተጠቆመ። ሰላም በየአካባቢው ለማረጋገጥ ትልቁን ድርሻ የሚጫወተው መንግሥት ቢሆንም ኅብረተሰቡም ጽንፈኞችንና ሽብርተኞችን በመታገልና በማጋለጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ሰላም ልማት መምህር አቶ ሮባ ጴጥሮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ግጭቶች በፖለቲካ ልዩነት፣ በጎሳ፣ በሃይማኖትና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ሊከሰቱ ቢችሉም አገር ያለ ሰላም፤ ሰላም ደግሞ ያለ ውይይት ሊኖር አይችልም።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚስተዋለው ግጭትና የሰላም መደፍረስ መንስኤዎቹ በርካታ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የሽብር ቡድኖችና ፅንፈኛ ኃይሎች የማኅበረሰቡን ሕይወት አደጋ ውስጥ በመጣልና ከቀዬው በማፈናቀል በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ ፈተና መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአገር ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት መንግሥት በአገር ደህንነት ላይ የተጋረጡ ስጋቶችን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70817

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ