Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
302 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የዓለም ባንክ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ከአምስት ሚሊዮን በላይ ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ የገንዘብ ድጋፍ ማጽደቁን አስታወቀ።
የዓለም ባንከ ትናንት ባወጣው መግለጫው ላይ እንዳስታወቀው፤ በጦርነቱ ምክንያት በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ሀብት ንብረታቸው ወድሟ፤ የህዝብ መገልገያ የሆኑ ተቋማትና ንብረቶችም በተመሳሳይ ወድመዋል፤ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሴቶችና ህጻናትም ለጾታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል።
ኢትዮጵያ ይህንን ችግር ለመቋቋም እያደረገች ያለውን ጥረት ለማገዝና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ባንኩ የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታውቋል።
ድጋፉ ለማህበረሰቡ አስቸኳይ የእለት ደራሽ ፍላጎቶች፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና ለተያያዥ ማህበረሰብ አቀፍ ጉዳዮች የሚውል መሆኑንም ባንኩ ገልጿል።
የባንኩ ፕሮጀክት በመነሻነት ተግባራዊ የሚደረገውም በአፋር፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያና ትግራይ አካባቢዎች መሆኑም ተብራርቷል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በመጋቢት ወር ብቻ ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በመጋቢት ወር ብቻ ከ27 ነጥብ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ የገቢዎች ሚኒስቴር አሰታወቀ ።
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እንዳስታወቁት፣ የተሰበሰበው ገቢ የዕቅዱ 99 ነጥብ 67 በመቶ ማሳካት ተችሏል። ከ2ዐ13 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር 29 ነጥብ 11 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል።
ገቢው በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ የተሰበሰበ በመሆኑ ጥሩ አፈፃፀም ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህም ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ምንም ዓይነት ምክንያት ሳያሳብቡ በወቅቱ ግብራቸውን አስታውቀው በሚከፈሉ ግብር ከፋዮቻችን መልካምፈቀደኝነት በመኖሩ፤ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት በመቻላቸው እንዲሁም አጋር አካላትና ሕዝቡ እውነተኛ ድጋፍ በማድረጉ ነው።
በመሆኑም በ3ቱም የጋራ ጥረት የመጣ ውጤት በመሆኑ በራሴና በገቢዎች ሚኒስቴር ሥም ከልብ እያመሰገንኩ በቀሪ ሦስት ወራትም የመጋቢትን ወር አፈፃፀም እንድንደግመው ድጋፋችሁ እንዳይለየን የአክብሮት ጥሬዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ አስነሳላችኋላሁ በማለት ጉቦ ሲቀበል የነበረ መርማሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥባቸው በተደረጉ ንብረቶች ላይ ግለሰቦችን "እግድ አስነሳላችኋላሁ" በማለት ጉቦ ሲቀበል የነበረ መርማሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሙስና ወንጀል በተጀመረ ምርመራ ምክንያት ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በፍርድ ቤት የንብረት እግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥባቸው የተደረጉ ግለሰቦችን እግድ አስነሳላችኋላሁ በማለት ጉቦ ሲቀበል የነበረ መርማሪ በተቋሙ አመራሮችና በግለሰቦቹ ጥቆማ በፖለስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በግለሰቡ መኖሪያ ቤቱ በተደረገ ብርበራ 420 ሺህ የተገኘ ሲሆን በድርጊቱ ተሳታፊ በሆኑ ሌሎች ግለሰቦች ላይ ምርመራ ቀጥሏል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን በማጋለጥ የህግ የበላይነትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍና መብቱን በህጋዊ መንገድ ብቻ በማስከበር የወንጀለኞች መጠቀሚያ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ ሚኒስቴሩ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የእስራኤል የልዑካን ቡድን የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዱ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የእስራኤል የፓርላማ አባላት እና የጤና ባለሙያዎች ቡድን በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዱ፡፡
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት ትስስር ከዲፕሎማሲ ባለፈ ነው ያሉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የክልሉ ጤና ተቋማት የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ ነው።
ጉዳቱን መልሶ በመገንባት የተሟላ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከየአቅጣጫው ለሚደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የኢትዮጵያና የእስራኤል የፓርላማ አባላት፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ፣ የእስራኤል ቆንስላ ፅ/ቤት የጎንደር ቅርንጫፍ ዳይሬከረተር አቶ አዳነ ተድላ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ጉዳት የደረሰባቸው ዞኖች የጤና ተቋማት ኃላፊዎች በመድረኩ ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የኢትዮጵያ የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት የኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ ፖስኮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት ለተያዘው ዕቅድ የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ አሰታወቁ።

ሚኒስትሩ ከኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባቀረቡለት ግብዣ መሰረት በብረት ምርትና ፋብሪካ ግንባታ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፋቸውን ለመስጠት ከመጡት ታዋቂው የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ፖስኮ የጥናት ቡድን አካል የሚሆን ሲሆን ኩባንያው በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል።

በቅርብ ጊዜያትም የአዋጭነት ጥናት፣ የፋብሪካ ተከላና የሰው ሀብት ልማት ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ከማዕድን ሚኒስቴር ሙያተኞች ጋር ይፋዊ ስራ መጀመሩ የማዕድን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ለመጪው የፋሲካ በዓል የዘይት አቅርቦትና ስርጭት በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ንግድ ቢሮ አስታወቀ
******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የዘይት አቅርቦትና ስርጭት በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ከዘይት አቅራቢ ድርጅቶችና ባለ ድረሻ አካላትጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የግብይት ሰንሰለቱን በጠበቀና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲሚሰራጭም ተገልጸዋል።

የንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ፣ የዘይት አቅራቢዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸውና የዘይትን ምርት ስርጭት ከወዲሁ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ማቅረብ እንዳለባቸው ፤የአቅርቦትና የስርጭት ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ስርጭቱ በተስተካከለ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑንም አክለው አስረድተዋል፡፡

የዘይት አቅራቢዎችም በበኩላቸው በቢሮው በተቀመጠላቸው አቅጣጫ ለመስራትና ከወዲሁ ከፋሲካ በዓል በፊት በሸማች ህብረትስራ ማህበራት በኩል ምርቱን ለማሰራጨት የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱ ተጠናቋል ።

ንግድ ቢሮ የሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት በተለይም ስኳርና ዱቄት ለፋሲካ በዓል በተገቢው መንገድ ለማህበረሰቡ እንዲደርሱ እየሰራ መሆኑም ተመላክቶዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ሁሉም ወገን ለአገሪቱ ሰላምና ለዜጎች ደህንነት በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀስ ተጠየቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል የሚደረገው እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲቆምና ሁሉም ወገን ለአገሪቱ ሰላምና ለዜጎች ደህንነት መጠበቅ በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀስ የገዳ አባቶች ህብረት ጸሐፊና የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ጥሪ አቀረቡ።

አባ ገዳ ጎበና ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ በአገሪቱ በየቦታው የሚስተዋለው የሰላም እጦትና ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ መፍትሄ ካልተሰጠው አገር ከማፍረስ አልፎ የዜጎችን የመኖር ህልውና አጠያያቂ ያደርጋል።

በሰላም እጦት ምክንያት ከኢትዮጵያ በእድገታቸው የሚበልጡ አገራት ትላላቅ ከተሞቻቸው መወደማቸውን አይተናል። ስለሆነም ስለአገራችን የሰላም ጉዳይ ሁላችንም ልንጨነቅ ይገባልም ብለዋል።

በሚፈጠረው ችግር ከሁሉም በላይ ንጹሃን ዜጎች ኢላማ ስለሚሆኑ የትኛውንም አለመግባባት በጠረጴዛ ዙሪያ እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ የመንግሥት ድርብ ኃላፊነት ነው ያሉት አባገዳ ጎበና፤ አንዳንድ ምሁራንና ፖለቲከኞች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በሚያስተላልፉት ከፋፋይ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70816

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
የሰዎችን ሕይወት በማጥፋትና ዜጎችን በማፈናቀል የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት እንደማይቻል ተጠቆመ
****************
(ኢ ፕ ድ)

የንጹሃን ሰዎችን ሕይወት በማጥፋትና ዜጎችን ከቀያቸው በማፈናቀል የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት እንደማይቻል ተጠቆመ። ሰላም በየአካባቢው ለማረጋገጥ ትልቁን ድርሻ የሚጫወተው መንግሥት ቢሆንም ኅብረተሰቡም ጽንፈኞችንና ሽብርተኞችን በመታገልና በማጋለጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ሰላም ልማት መምህር አቶ ሮባ ጴጥሮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ግጭቶች በፖለቲካ ልዩነት፣ በጎሳ፣ በሃይማኖትና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ሊከሰቱ ቢችሉም አገር ያለ ሰላም፤ ሰላም ደግሞ ያለ ውይይት ሊኖር አይችልም።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚስተዋለው ግጭትና የሰላም መደፍረስ መንስኤዎቹ በርካታ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የሽብር ቡድኖችና ፅንፈኛ ኃይሎች የማኅበረሰቡን ሕይወት አደጋ ውስጥ በመጣልና ከቀዬው በማፈናቀል በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ ፈተና መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአገር ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት መንግሥት በአገር ደህንነት ላይ የተጋረጡ ስጋቶችን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70817

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
“ጂፒኤስ ያስገጠሙ የሕዝብ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ይደረግላቸዋል” -የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ከ12 ሰዎች በላይ የመጫን አቅም ያላቸውና ጂፒኤስ ያስገጠሙ የሕዝብ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ባወጡባቸው አካባቢ በሚመጣው የመረጃ ቋት (ዳታ ቤዝ) መሠረት የነዳጅ ድጎማው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የነዳጅ ድጎማውን ለማግኘት እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ጂፒኤስ ማስገጠም እንደሚኖርበት ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የነዳጅ ድጎማው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ያስችላል። ድጎማውም ከሐምሌ አንድ 2014ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።
በድጎማ ሥርዓቱ ተሽከርካሪዎች ጂፒኤስ ማስገጠም የመጀመሪያው መስፈርት መሆኑን የገለጹት አቶ አረጋዊ፤ ይህም የትራንስፖርት ስምሪቱን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ቁጥጥሩን ለማሳለጥ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
እንደ አቶ አረጋዊ ገለጻ፤ በአዲስ አበባ ነባራዊ ሁኔታ የሰሌዳ ቁጥር ያላቸው፤ 12 ሰዎችንና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያላቸው ኮድ አንድ ብዙኃን ትራንስፖርት የነዳጅ ድጎማው ተጠቃሚዎች ናቸው። እንዲሁም ኮድ ሦስት የሆኑና ጂፒኤስ የተገጠመላቸው ከ12 ሰዎች በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማው በቀጥታ ይመለከታቸዋል።
ከሌሎች ክልሎች ሰሌዳ አውጥተው በከተማዋ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70839
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የኑሮ ውድነትን እያባባሱ ባሉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ። የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጫናው ከፍተኛ በመሆኑ ወቅቱን የዋጀ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራ ሊሠራ ይገባል።
የፖለቲካና የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ወሰንሰገድ አሰፋ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሁን እየታየ ያለው የምርቶች የዋጋ ንረት አገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ጉዳይ ሆኖ እየታየ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጠር ማንኛውም ኢኮኖሚ እድገት ሲመጣ በራሱ የሚፈጠር የዋጋ ግሽበት መኖሩን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የዋጋ ግሽበት እያደገ መምጣት ደግሞ ከሰዎች የመሥራት አቅም ማደግ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ገልጸዋል። ለአብነት የኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበት የፍላጎትና የአቅርቦት መጠን አለመመጣጠን መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጠቁመዋል።
በምንዛሬ እጥረት የሚፈጠር የዋጋ ንረት ቢኖርም በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወጪ የግብርና ምርት ግብዓት ማሟያ የሚውለው በጀት ለጦርነት የሚመደብ ከሆነ፣ የመሠረታዊ ፍላጎት እጥረት እንዲኖር ያደርጋል። በዚህ ወቅት የዋጋ ንረቱ እያሻቀበ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ ያደርጋል።
የዋጋ ንረቱ ክፍተት አገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መሆኑን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70824
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️