Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
302 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የእስራኤል የልዑካን ቡድን የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዱ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የእስራኤል የፓርላማ አባላት እና የጤና ባለሙያዎች ቡድን በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዱ፡፡
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት ትስስር ከዲፕሎማሲ ባለፈ ነው ያሉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የክልሉ ጤና ተቋማት የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ ነው።
ጉዳቱን መልሶ በመገንባት የተሟላ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከየአቅጣጫው ለሚደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የኢትዮጵያና የእስራኤል የፓርላማ አባላት፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ፣ የእስራኤል ቆንስላ ፅ/ቤት የጎንደር ቅርንጫፍ ዳይሬከረተር አቶ አዳነ ተድላ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ጉዳት የደረሰባቸው ዞኖች የጤና ተቋማት ኃላፊዎች በመድረኩ ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የኢትዮጵያ የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት የኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ ፖስኮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት ለተያዘው ዕቅድ የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ አሰታወቁ።

ሚኒስትሩ ከኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባቀረቡለት ግብዣ መሰረት በብረት ምርትና ፋብሪካ ግንባታ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፋቸውን ለመስጠት ከመጡት ታዋቂው የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ፖስኮ የጥናት ቡድን አካል የሚሆን ሲሆን ኩባንያው በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል።

በቅርብ ጊዜያትም የአዋጭነት ጥናት፣ የፋብሪካ ተከላና የሰው ሀብት ልማት ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ከማዕድን ሚኒስቴር ሙያተኞች ጋር ይፋዊ ስራ መጀመሩ የማዕድን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ለመጪው የፋሲካ በዓል የዘይት አቅርቦትና ስርጭት በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ንግድ ቢሮ አስታወቀ
******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የዘይት አቅርቦትና ስርጭት በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ከዘይት አቅራቢ ድርጅቶችና ባለ ድረሻ አካላትጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የግብይት ሰንሰለቱን በጠበቀና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲሚሰራጭም ተገልጸዋል።

የንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ፣ የዘይት አቅራቢዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸውና የዘይትን ምርት ስርጭት ከወዲሁ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ማቅረብ እንዳለባቸው ፤የአቅርቦትና የስርጭት ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ስርጭቱ በተስተካከለ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑንም አክለው አስረድተዋል፡፡

የዘይት አቅራቢዎችም በበኩላቸው በቢሮው በተቀመጠላቸው አቅጣጫ ለመስራትና ከወዲሁ ከፋሲካ በዓል በፊት በሸማች ህብረትስራ ማህበራት በኩል ምርቱን ለማሰራጨት የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱ ተጠናቋል ።

ንግድ ቢሮ የሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት በተለይም ስኳርና ዱቄት ለፋሲካ በዓል በተገቢው መንገድ ለማህበረሰቡ እንዲደርሱ እየሰራ መሆኑም ተመላክቶዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ሁሉም ወገን ለአገሪቱ ሰላምና ለዜጎች ደህንነት በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀስ ተጠየቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል የሚደረገው እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲቆምና ሁሉም ወገን ለአገሪቱ ሰላምና ለዜጎች ደህንነት መጠበቅ በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀስ የገዳ አባቶች ህብረት ጸሐፊና የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ጥሪ አቀረቡ።

አባ ገዳ ጎበና ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ በአገሪቱ በየቦታው የሚስተዋለው የሰላም እጦትና ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ መፍትሄ ካልተሰጠው አገር ከማፍረስ አልፎ የዜጎችን የመኖር ህልውና አጠያያቂ ያደርጋል።

በሰላም እጦት ምክንያት ከኢትዮጵያ በእድገታቸው የሚበልጡ አገራት ትላላቅ ከተሞቻቸው መወደማቸውን አይተናል። ስለሆነም ስለአገራችን የሰላም ጉዳይ ሁላችንም ልንጨነቅ ይገባልም ብለዋል።

በሚፈጠረው ችግር ከሁሉም በላይ ንጹሃን ዜጎች ኢላማ ስለሚሆኑ የትኛውንም አለመግባባት በጠረጴዛ ዙሪያ እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ የመንግሥት ድርብ ኃላፊነት ነው ያሉት አባገዳ ጎበና፤ አንዳንድ ምሁራንና ፖለቲከኞች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በሚያስተላልፉት ከፋፋይ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70816

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
የሰዎችን ሕይወት በማጥፋትና ዜጎችን በማፈናቀል የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት እንደማይቻል ተጠቆመ
****************
(ኢ ፕ ድ)

የንጹሃን ሰዎችን ሕይወት በማጥፋትና ዜጎችን ከቀያቸው በማፈናቀል የፖለቲካ ዓላማን ማሳካት እንደማይቻል ተጠቆመ። ሰላም በየአካባቢው ለማረጋገጥ ትልቁን ድርሻ የሚጫወተው መንግሥት ቢሆንም ኅብረተሰቡም ጽንፈኞችንና ሽብርተኞችን በመታገልና በማጋለጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ሰላም ልማት መምህር አቶ ሮባ ጴጥሮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ግጭቶች በፖለቲካ ልዩነት፣ በጎሳ፣ በሃይማኖትና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ሊከሰቱ ቢችሉም አገር ያለ ሰላም፤ ሰላም ደግሞ ያለ ውይይት ሊኖር አይችልም።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚስተዋለው ግጭትና የሰላም መደፍረስ መንስኤዎቹ በርካታ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የሽብር ቡድኖችና ፅንፈኛ ኃይሎች የማኅበረሰቡን ሕይወት አደጋ ውስጥ በመጣልና ከቀዬው በማፈናቀል በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ ፈተና መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአገር ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት መንግሥት በአገር ደህንነት ላይ የተጋረጡ ስጋቶችን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70817

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
“ጂፒኤስ ያስገጠሙ የሕዝብ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ይደረግላቸዋል” -የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ከ12 ሰዎች በላይ የመጫን አቅም ያላቸውና ጂፒኤስ ያስገጠሙ የሕዝብ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ባወጡባቸው አካባቢ በሚመጣው የመረጃ ቋት (ዳታ ቤዝ) መሠረት የነዳጅ ድጎማው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የነዳጅ ድጎማውን ለማግኘት እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ጂፒኤስ ማስገጠም እንደሚኖርበት ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የነዳጅ ድጎማው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ያስችላል። ድጎማውም ከሐምሌ አንድ 2014ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።
በድጎማ ሥርዓቱ ተሽከርካሪዎች ጂፒኤስ ማስገጠም የመጀመሪያው መስፈርት መሆኑን የገለጹት አቶ አረጋዊ፤ ይህም የትራንስፖርት ስምሪቱን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ቁጥጥሩን ለማሳለጥ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
እንደ አቶ አረጋዊ ገለጻ፤ በአዲስ አበባ ነባራዊ ሁኔታ የሰሌዳ ቁጥር ያላቸው፤ 12 ሰዎችንና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያላቸው ኮድ አንድ ብዙኃን ትራንስፖርት የነዳጅ ድጎማው ተጠቃሚዎች ናቸው። እንዲሁም ኮድ ሦስት የሆኑና ጂፒኤስ የተገጠመላቸው ከ12 ሰዎች በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማው በቀጥታ ይመለከታቸዋል።
ከሌሎች ክልሎች ሰሌዳ አውጥተው በከተማዋ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70839
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የኑሮ ውድነትን እያባባሱ ባሉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ። የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጫናው ከፍተኛ በመሆኑ ወቅቱን የዋጀ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራ ሊሠራ ይገባል።
የፖለቲካና የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ወሰንሰገድ አሰፋ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሁን እየታየ ያለው የምርቶች የዋጋ ንረት አገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ጉዳይ ሆኖ እየታየ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጠር ማንኛውም ኢኮኖሚ እድገት ሲመጣ በራሱ የሚፈጠር የዋጋ ግሽበት መኖሩን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የዋጋ ግሽበት እያደገ መምጣት ደግሞ ከሰዎች የመሥራት አቅም ማደግ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ገልጸዋል። ለአብነት የኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበት የፍላጎትና የአቅርቦት መጠን አለመመጣጠን መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጠቁመዋል።
በምንዛሬ እጥረት የሚፈጠር የዋጋ ንረት ቢኖርም በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወጪ የግብርና ምርት ግብዓት ማሟያ የሚውለው በጀት ለጦርነት የሚመደብ ከሆነ፣ የመሠረታዊ ፍላጎት እጥረት እንዲኖር ያደርጋል። በዚህ ወቅት የዋጋ ንረቱ እያሻቀበ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ ያደርጋል።
የዋጋ ንረቱ ክፍተት አገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መሆኑን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70824
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በአፋር ክልል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዕለት ደራሽ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
በአፋር ክልል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የዕለት ደራሽ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ከሚገኙ 21 ወረዳዎች ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የዕለት ደራሽ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ወረራ ምክንያት ከ645 ሺህ በላይ ዜጎች ከትውልድ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል።
በክልሉ ለጉዳት ከተጋለጡት አንዱ በሆነው ኪልባቲ ዞን ሁለት ሥር የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች አባአላ፣ መጋሌ፣ ኮነቫ፣ ዳሎል፣ ኢረብቲ እና በርሃሌ በወረራው ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ኃላፊው በተለይም አባአላ እና ኢረብቲ ወረዳዎች አልፎ አልፎ የሚነሱ ግጭቶች ለተፈናቃይ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70824
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በኩላሊትና ካንሰር ሕክምና ላይ አተኩሮ እየሠራ መሆኑን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ በኩላሊትና ካንሰር ሕክምና ላይ በማተኮር ውጤት ለማስመዝገብ እየሠራ መሆኑን ገለጸ።
ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው በጤና ዘርፍ የኩላሊት ሕክምናና ካንሰር ላይ ለመሥራት በትኩረት አቅጣጫ ለይቷል። በእነዚህ የሕክምና ዘርፎች ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ ይገኛል።
ለኩላሊት እጥበት ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ ታካሚዎች የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፤ ይህንን አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
በካንሰር ሕክምናም በተሻለ መልኩ አገልግሎቱን ለመስጠት እየሠራ እንደሚገኘ ገልጸው፤ በተለይ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የሕክምና ዓይነቶች ኅብረተሰቡን ለማገልግል ራሱን ዘመኑ በአፈራቸው ቤተ ሙከራዎችና የሕክምና መሣሪያዎች ራሱን የማዘመን ሥራ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70823
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ሦስት ወረዳዎች የአቮካዶ ምርትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ውጤታማነታቸው መረጋገጡን ማኅበሩ አስታወቀ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ሦስት አካባቢዎች ውጤታማነታቸው በተግባር መረጋገጡን የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማኅበር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማኅበር የፕሮጀክት ማናጀር አቶ ዋለ ጌታነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ቡታጂራ አካባቢና በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ውጤታማነታቸው በተግባር ተረጋግጧል።
እስካሁን በተከናወኑ ሥራዎች በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ለወጪ ንግድ የሚውሉ ጥራት ያላቸው የአቮካዶ ምርቶችን ማዘጋጀት ቢቻልም በኢትዮጵያ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም መኖሩን ጠቁመዋል።
የአካባቢዎቹን ተሞክሮም ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማስፋፋት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዋለ፤ ይህን አቅም በአግባቡ ለመጠቀምና ዘርፉን ለማሳደግ የግብዓት አቅራቢዎችና አምራቹን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70826
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ከ13 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከውጭ ሀገር ገበያ ማግኘት ችለዋል
******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ2014 በጀት ዓመት 9 ወራት 216 የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻችን ወደውጭ ሀገር በመላክ 13 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘታቸውን አሰታወቀ።
የተቋሙ የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ መለሰ፣ ባለፉት 9 ወራት 216 የሚሆኑ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የምርት ናሙናዎችን በማስተዋወቅና በቀጥታም ከላኪዎች ጋር የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ በማድረግ 13 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
በእነዚህ ኢንተርፕራይዞች 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ምርት ወደውጭ ሀገር ተልኳል። ወደ ውጭ ከተላኩ ዋና ዋና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች መካከል የአግሮፕሮሰሲንግ፣ የዕደ-ጥበብ፣ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች እና የኬሚካልና ማዕድን ምርቶች ይገኙበታል ብለዋል፡፡
በሀገሪቱም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት ወራት በርካታ ችግሮች ቢከሰቱም የሀገሪቱ ምርቶች በውጪ ሀገር ገበያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተወዳዳሪነታቸውንናጥራታቸው እየጨመረ በመምጣቱ የሽያጭ ዋጋቸውም በዚያው ልክ መጨመሩን አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር 2 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በአገር ውስጥ በማምረትና በመተካት የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉንም ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ባለፉት በዘጠኝ ወራት ከቀረቡት 531 ቅሬታዎች ለ529ኙ ውሳኔ መስጠቱን ኮሚሽኑ አስታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ ባለፉት በዘጠኝ ወራት ከተቀረበለት 531 የይግባኝ መዛግብት ለ529ኙ ውሳኔ መስጠቱን አሰታወቀ።
ኮሚሽኑ የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው እንደተናገሩት፣ በንግድና በጉምሩክ ከታክስ ተጨማሪ አሴት ተመን ጋር ተያይዞ ለኮሚሽኑ ቅሬታ ሲቀርብለት ከውሳኔ በፊት ገለልተኛ የሆነ የግራ ቀኝ ክርክር በዳኞቹ አማካኝነት ስለሚያደርግ የሚሰጠው ውሳኔው ፍትሃዊ ነው።
ለኮሚሽኑ የሚቀርቡለት ቅሬታዎች ሲፈተሹ አብዛኞቹ ያልተሟሉና ግልጽነት የጎደላቸው መረጃዎች መሆናቸው የገለጹት አቶ ሙሉጌታ የተሟላና እውነተኛ መረጃ ይዞ የሚቀርቡ ቅሬታ አቅራቢዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
በዋቅሹም ፍቃዱ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️