Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
301 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በህገወጥ መንገድ ሊጓጓዝ የነበረ አራት ሺህ 476 ሊትር በላይ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሸቀጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ልዩ ስሙ ሞቢል ማደያ አካባቢ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከአይሱዙ መኪና ላይ ወደ ኮንቴይነር ተሸካሚ 2 ሎቤድ ተሽከርካሪዎች ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በመጫን ላይ ሳለ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ሎቤድ መኪኖቹ ላይ በተደረገ ፍተሻም አራት ሺህ 476 ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት እንዲሁም 12 ኬሻ ቡና፣ 39 ካርቶን ፈሳሽ የምግብ ዘይት መገኘቱና ምርመራውም በሚመለከተው የህገ አካል እንደቀጠለ ጽ/ቤቱ አስታውቋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ሽፈራው አለሙ እንደገለፁት ህጋዊ ሂደታቸውን ያልተከተሉ ምርቶችን ከተለያዩ ህጋዊ ደረሰኝ ካላቸው ምርቶች ጋር በመቀላቀል ህጋዊ አስመስሎ ለማሳለፍ እየተደረገ የነበረውን ሂደት በአካባቢው የተመለከቱ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ መሰል ሕገወጥ ተግባራትን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኝ የህግ አካል ወይም በስልክ በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪው አቶ ሽፈራው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የአርባምንጭ ከተማን ጨምሮ በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች የወጣቶች የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ክልል ከ94ሺ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ በተለያዩ ከተሞች እየተካሔደ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ክልል አቀፍ የወጣቶች መድረክ በ157 ከተሞች ወጣቶችን ያሳተፈ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስመኘው አድነው በሆሳዕና ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደገለጹት በብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማሳደግ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ መቻሉን ተናግረዋል።
በፓርቲው የተቀመጡ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን በመፈጸም ሂደት ወጣቱ ግንባር ቀደም ተዋናይ ነው ያሉት ኃላፊው በውይይት መድረኮች ወጣቶች ገንቢ አስተያየት በማቅረብ በሀገሪቱ እየተካሔደ ያለውን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
በጉባኤው በኢኮኖሚያዊ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ የሚያደርጉ ውሳኔዎች መተላለፋቸውንም አብራርተዋል።
የዉይይት መድረኮች በቡታጅራ፣በሀላባ ቁሊቶ፣ በከምባታ ጠምባሮ ዞን እና በሌሎች ከተሞች እየተካሄደ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ባሳለፍነው ሳምንት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም ሰልፍ በአራት ከተሞች ተካሂዷል
*******
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም በአራት የተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል።

በጣሊያን ሮም፣ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስአንጀለስ፣ በዋሺንግተን ዲሲ፣ በቤልጂየም ብራሰልስ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም ሰልፍ ከተሞች ናቸው

ሰልፈኞቹ ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪም ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በመሬት ላይ ያለውን እውነታ እንዲመለከቱ ጠይቀዋል።

ሕጎቹ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚጎዳ እንደሆነና የሁለቱ ሀገራት ጥቅም የማያስጠብቅ እንደሆነም ነው ሰልፈኞቹ የገለጹት።

የረቂቅ ሕጎቹን ይዘት መንግስትን ከመደገፍና ከመቃወም ጋር የሚያያዝ ሳይሆን በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ችግር የሚጋርጥና ሕዝብን የሚጎዳ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ረቂቅ ህጎቹ በህግ አውጭው አካል ሙሉ በሙሉ ውድቅ እስከሚሆኑ ድረስ የሚያደርጉትን ትግል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተሳካ ሮኬት አስወነጨፈ
*************
(ኢ ፕ ድ)
ከሦስተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአፄ ቴዎድሮስን የዕውቀት ጥያቄ የመመለስ ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የአፄ ቴዎድሮስን 154ኛ ዝክረ ሰማእት ምክንያት በማድረግ አሞራ ገደል በተባለ ሥፍራ የተሳካ የሮኬት ማስወንጨፍ ሙከራ አካሂዷል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያደረገው ሙከራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የቴክኖሎጅ ምርምሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚደንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ተናግረዋል።

ይህ ምርምር አድጎ ለሀገሪቷ የሕዋ ሳይንስ ምርምር አጋዥ እንዲሆን ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

እንደ አሚኮ ዘገባ በዝክረ ሰማእት መታሰቢያ ዕለቱ የአፄ ቴዎድሮስን የመድፍ ሥራ የሚያስታውስ ምስለ ሴባስቶፖል መድፍ ተሰርቶ በደብረ ታቦር ከተማ የመተኮስ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ