Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ባሳለፍነው ሳምንት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም ሰልፍ በአራት ከተሞች ተካሂዷል
*******
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም በአራት የተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል።

በጣሊያን ሮም፣ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስአንጀለስ፣ በዋሺንግተን ዲሲ፣ በቤልጂየም ብራሰልስ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም ሰልፍ ከተሞች ናቸው

ሰልፈኞቹ ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪም ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በመሬት ላይ ያለውን እውነታ እንዲመለከቱ ጠይቀዋል።

ሕጎቹ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚጎዳ እንደሆነና የሁለቱ ሀገራት ጥቅም የማያስጠብቅ እንደሆነም ነው ሰልፈኞቹ የገለጹት።

የረቂቅ ሕጎቹን ይዘት መንግስትን ከመደገፍና ከመቃወም ጋር የሚያያዝ ሳይሆን በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ችግር የሚጋርጥና ሕዝብን የሚጎዳ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ረቂቅ ህጎቹ በህግ አውጭው አካል ሙሉ በሙሉ ውድቅ እስከሚሆኑ ድረስ የሚያደርጉትን ትግል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተሳካ ሮኬት አስወነጨፈ
*************
(ኢ ፕ ድ)
ከሦስተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአፄ ቴዎድሮስን የዕውቀት ጥያቄ የመመለስ ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የአፄ ቴዎድሮስን 154ኛ ዝክረ ሰማእት ምክንያት በማድረግ አሞራ ገደል በተባለ ሥፍራ የተሳካ የሮኬት ማስወንጨፍ ሙከራ አካሂዷል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያደረገው ሙከራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የቴክኖሎጅ ምርምሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚደንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ተናግረዋል።

ይህ ምርምር አድጎ ለሀገሪቷ የሕዋ ሳይንስ ምርምር አጋዥ እንዲሆን ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

እንደ አሚኮ ዘገባ በዝክረ ሰማእት መታሰቢያ ዕለቱ የአፄ ቴዎድሮስን የመድፍ ሥራ የሚያስታውስ ምስለ ሴባስቶፖል መድፍ ተሰርቶ በደብረ ታቦር ከተማ የመተኮስ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በታላቁ ቤተመንግስት የኢፍጣር ፕሮግራም እየተካሄደ ነው
*******
(ኢ ፕ ድ)
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በታላቁ ቤተመንግስት የኢፍጣር ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።

በታላቁ ቤተመንግስት በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የእስልምና እምነት ታላላቅ የኃይማኖት አባቶች ታድመዋል።

በዚህም የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ፣ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ጀይላኒ ከድር ጨምሮ ታላላቅ አባቶች፣ኢማሞች እና የእምነቱ ተከታዮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ