Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ባሳለፍነው ሳምንት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም ሰልፍ በአራት ከተሞች ተካሂዷል
*******
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም በአራት የተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል።

በጣሊያን ሮም፣ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስአንጀለስ፣ በዋሺንግተን ዲሲ፣ በቤልጂየም ብራሰልስ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን የሚቃወም ሰልፍ ከተሞች ናቸው

ሰልፈኞቹ ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪም ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በመሬት ላይ ያለውን እውነታ እንዲመለከቱ ጠይቀዋል።

ሕጎቹ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚጎዳ እንደሆነና የሁለቱ ሀገራት ጥቅም የማያስጠብቅ እንደሆነም ነው ሰልፈኞቹ የገለጹት።

የረቂቅ ሕጎቹን ይዘት መንግስትን ከመደገፍና ከመቃወም ጋር የሚያያዝ ሳይሆን በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ችግር የሚጋርጥና ሕዝብን የሚጎዳ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ረቂቅ ህጎቹ በህግ አውጭው አካል ሙሉ በሙሉ ውድቅ እስከሚሆኑ ድረስ የሚያደርጉትን ትግል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተሳካ ሮኬት አስወነጨፈ
*************
(ኢ ፕ ድ)
ከሦስተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአፄ ቴዎድሮስን የዕውቀት ጥያቄ የመመለስ ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የአፄ ቴዎድሮስን 154ኛ ዝክረ ሰማእት ምክንያት በማድረግ አሞራ ገደል በተባለ ሥፍራ የተሳካ የሮኬት ማስወንጨፍ ሙከራ አካሂዷል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያደረገው ሙከራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የቴክኖሎጅ ምርምሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚደንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ተናግረዋል።

ይህ ምርምር አድጎ ለሀገሪቷ የሕዋ ሳይንስ ምርምር አጋዥ እንዲሆን ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

እንደ አሚኮ ዘገባ በዝክረ ሰማእት መታሰቢያ ዕለቱ የአፄ ቴዎድሮስን የመድፍ ሥራ የሚያስታውስ ምስለ ሴባስቶፖል መድፍ ተሰርቶ በደብረ ታቦር ከተማ የመተኮስ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በታላቁ ቤተመንግስት የኢፍጣር ፕሮግራም እየተካሄደ ነው
*******
(ኢ ፕ ድ)
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በታላቁ ቤተመንግስት የኢፍጣር ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።

በታላቁ ቤተመንግስት በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የእስልምና እምነት ታላላቅ የኃይማኖት አባቶች ታድመዋል።

በዚህም የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ፣ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ጀይላኒ ከድር ጨምሮ ታላላቅ አባቶች፣ኢማሞች እና የእምነቱ ተከታዮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"የኢቢሲ - ንግድ ባንክ 4ኛ የስፖርት ሽልማት ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ። በመካከላችን ያሉትን በርካታ ጀግኖች መዘንጋት የለብንም። ነባሮቹን በማድነቅና ተምሳሌት በማድረግ አዳዲሶችን በመንከባከብ ብዙ ጀግኖችን ለመፍጠር መትጋት አለብን። ስፖርት ለሀገራችን ያለውን አራት ፋይዳዎች ማሰብ ተገቢ ነው። 1) ስፖርት የግል ክህሎት ይፈልጋል እንዲሁም የቡድን ጥረት ይጠይቃል:: የሀገር ግንባታም እንዲሁ ነው። 2) ስፖርት የግል ጥቅምን ከማስፈን ባሻገር የሀገር ገጽታ ግንባታን ይደግፋል። 3) ስፖርት እንደ አንድ ሀገር የማያቋርጥ እና ተጨማሪ ጥረት እና ጠንክሮ መሥራትን ይፈልጋሉ። 4) ስፖርት ዲሲፕሊንን እና ደንቦችን ማክበርን ይጠይቃል። ሀገርም የተጻፋና ያልተጻፋ ሕጎችን ይሻል:: የስፖርት ጀግኖቻችንን ስኬት፣ ታታሪነት እና ውጤታቸውን ስናከብር እንደ ሀገር ስፖርቱ የሚያሳየንን ትምህርት እናስተውል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የቀይ መስቀል ማኅበር ለሰባት ሚሊዮን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በተያዘው በጀት ዓመት በሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለችግር ለተዳረጉ ሰባት ሚሊዮን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ።
የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን አሊ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት፣ በድርቅና በሌሎችም ተያያዥ ችግሮች ምክንያት መጠነሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ ተፈጥሯል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በተያዘው በጀት ዓመት በሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለችግር ለተዳረጉ ሰባት ሚሊዮን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉንና ከዚህ ውስጥ ሦስት ሚሊዮን የሚሆኑት በግጭትና ድርቅ ለችግር የተዳረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በሚቀጥሉት ሰባት ወራትም ከአምስት መቶ ሺ እስከ ስድስት መቶ ሺ የሚደርሱ ሰዎችን ለማገዝ መታቀዱን ገልጸው፤ ለዚህ ደግሞ እስከ ሰባት መቶ ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል። ይህን ሀብት ለማሰባሰብም በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ በኩል ጥሪ የቀረበ ሲሆን በአገር ውስጥም ከበጎ አድራጊዎች የሀብት ማሰባሰብ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ከግጭት፣ ድርቅና ሌሎችም ችግሮች ጋር በተገናኘ 20 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች ቀጥታ እርዳታና መልሶ ማቋቋም ይፈልጋሉ ያሉት ዶክተር ሰለሞን፤ ማኅበሩም በሚሰበስበው....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71037
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
”የአካባቢ ስያሜን መቀየር የኢትዮጵያን መቦጫጨቅ የሚፈልጉ አካላት የሚያሰራጩት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ነው‘ – አምባሳደር ተፈራ ሻዎል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ሰሜን ጎንደርን ሌላ ስያሜ በማላበስ አንዱን ምዕራብ ሌላውን ምስራቅ ክፍል ነው የሚለው አገላለጽ የኢትዮጵያን መቦጫጨቅ የሚፈልጉ ሰዎችና ድርጅቶች የሚያሰራጩት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ አካል መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባ አምባሳደር ተፈራ ሻዎል ገለጹ።
አምባሳደር ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ወልቃይትና ጠገዴ የሚገኙበት ሰሜን ጎንደር የኢትዮጵያ ክፍል ነው። ስሙን እየለወጡ ሌላ ስያሜ መስጠት ተገቢነት የለውም። ድርጊቱ ምዕራባውያን የሚያካሂዱት የተለመደ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ አካል መሆኑን መገንዘብ ይገባል።
የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋሙ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች ሰሞኑን በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ ጉዳይ ሪፖርት ማውጣታቸው ይታወሳል።
እነዚህ ተቋማት የሰሜን ጎንደርን ስያሜ በመቀየር ሌላ ስም መስጠታቸው ተገቢነት የለውም ብለዋል። ሰሜን ጎንደርን ቀደም ሲል ወርረው ይዘውት፣ ስሙንም ለውጠው፣ በካርታም አቀማመጡን አበላሽተው ቆይተዋል ሲሉም አስታውሰዋል።
አሁን ደግሞ አካባቢውን በሪፖርት ሌላ ስያሜ ማላበስ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71038
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላቀ አገልግሎት ተሸላሚ ሆነ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2013/14 ዓ.ም ባስመዘገበው አፈፃፀም የላቀ አገልግሎት ተሸላሚ ሆነ፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አሸናፊ ታዘበው እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ሽልማቱን ማዘጋጀቱን አድንቀዋል።
ሽልማቱ ተቋሙ ለሠራቸው በርካታ ሥራዎች ዕውቅና የሚሰጥና ባለሙያዎችንም ለተሻለ ውጤት የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅትም ሆነ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ላይ ከሕክምና ባለሙያዎቹ በተጨማሪ የአስተዳደር ሠራተኞችና የአካባቢው ወጣቶች እንዲሁም ከማኅበራት ጋር ተቀናጅቶ ሲሠራ እንደቆየ ገልፀዋል፡፡
እንደ ዶክተር አሸናፊ ገለፃ፤ ባለሙያዎች ወደ ጦርነት ሄደው ሙያዊ እገዛ እንዲሰጡ ከመደረጋቸው በፊት በሥነ ልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71052
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ የመረጃ ተቋማት ሽብርተኝነትን ለመከላከል በትብብር እንደሚሠሩ ገለጹ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ የመረጃ ተቋማት ሽብርተኝነትን ለመከላከልና የቀጣናውን ዘላቂ ሠላም ለማስጠበቅ በትብብር እንደሚሠሩ ገለጹ።
የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ወታደራዊ መረጃ መድረክ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ትናንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል ብርሀኑ በቀለ፤ ምሥራቅ አፍሪካ የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ አሸባሪዎች፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እንዲሁም ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ያለበት መሆኑን ጠቅሰዋል። እነዚህ ሁሉ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ የጸጥታና የደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል አገራት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ቀጣናውን እየፈተኑ ያሉ እንደ አልሻበብ፣ አይ ኤስ አይ ኤስና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሽብርተኞችን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71036
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️