የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር የምርምር ውጤቶች የገንዘብ ድጋፍ ውድድር እየተካሄደ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር የምርምር ውጤቶች ወደ ገበያ የሚገቡበት የገንዘብ ድጋፍ ውድድር እየተካሄደ ነው::
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና የእንግሊዝ ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የሚያደርጉለት ኢኖቬሽን ለልማት ፕሮግራም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ማዕቀፍ ውስጥ የኢንደስትሪውን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የምርምር ውጤቶችን ወደ ገበያ ለማስገባት የሚያስችላቸውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ያስችል ዘንድ የመጨረሻውን ውድድር እየተካሄደ ነው
በውድድሩ ከሀያ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡት አርባ ዘጠኝ ውጤታማ፣ የተጠናቀቁና ወደ ገበያ ሊገቡ የሚችሉ የምርምር ውጤቶች ቀርበዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ውድድር ያለፉ አስራ አንድ ፕሮጀክቶች የመጨረሽውን ውድድር እያካሄዱ ነው፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀገራዊ የምርምር ስራዎች ወደ ገበያ ገብተው የኢንዱስትሪውን ችግር በመፍታት ምርታማነትን የሚጨምሩ እንዲሆኑ ለማስቻል ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ነው ተብሏል። የምርምር ውጤቶችን ወደ ገበያ ማስገቢያ የድጋፍ ስርዓት አንዱ ነው።
በቀጣይም እንዲህ አይነት ድጋፎች በሌሎች ከፍተኛ የትምህርትና የምርምር ተቋማት ተጠናከሮ እንደሚቀጥል ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።

የጮቄ ተፋሰስ የማህብረሰብ ጥብቅ ስፍራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያስገኝ እየተሰራ ነው
*************
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኘው የጮቄ የማህብረሰብ ጥብቅ ስፍራን በማልማት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲያስገኝ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።
የጮቄ ተፋሰስ ማህብረሰብ ጥብቅ ስፍራን ወደ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማስገባት ከባለድርሻ አካለት ጋር በደብረ ማርቆስ ከተማ ምክክር ተካሂዷል።
የክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን አለምነህ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በጥብቅ ስፍራነት የተከለለው የጮቄ ተፋሰስ ከ6 ሺህ 24 ሄክታር በላይ ስፋት ያለውና ስድስት ወረዳዎችና 22 ቀበሌዎች ያዋስኑታል።
ተፋሰሱን በማልማት፣ በመንከባከብና በመጠበቅ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ማፋጠን እንደሚገባ ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።
በውስጡ ያሉ አገር በቀል ደኖች፣ ብርቅዬ የዱር አራዊት፣ አእዋፋትና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶችን በጥናት በማስደገፍ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
የውጭና የአገር ውስጥ ቱሪስቶችንና ተመራማሪዎችን ወደ አካባቢው በመምጣት የሚዝናኑበት የመስህብ ቦታ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ ጥብቅ ስፍራውን በማይነካ መልኩ የተሻሻሉ መኖዎችን በማልማት፣ በእንስሳት ማድለብ፣ በወተት ልማትና ከጎብኞች በሚገኝ ገቢ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
እንድ ኢዜአ ዘገባ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የጮቄ ተፋሰስ ምርምርና ልማት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶክተር መግባር ወንዴ በበኩላቸው ህብረተሰቡን በተለያዩ የኢኮኖሚ አማራጮች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሲቲው ለጮቄ ተራራ ልማት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ዲከረንስ የተሰኘ ችግኝ እያስፈላ መሆኑን ጠቁመው፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አንድ ሽህ የአካባቢው አርሶ አደሮችን በንብ ማነብ ማሰማራት መቻሉን አስታውቀዋል።

የመዲናዋ የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን ለመመለስ በቅርበት የሚከታተል ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለፀ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማን ህዝብ የሰላምና ፀጥታ ችግር ጥያቄዎች ለመመለስ በቅርበት የሚከታተል ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለፀ።
መንግሥት የህዝቡን ችግሮች ለመፍታት ከህዝብ ጋር ውይይት እንዲደረግ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የከተማዋ ህዝብ በውይይቱ ወቅት በሰላምና ፀጥታ ችግሮች ዙሪያ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል የጋራ ግብረሃይል ማቋቋም ማስፈለጉ ተገልጿል።
ግብረ ሃይሉ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ ሲሆን የጋራ ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል የቢሮ ኃላፊና የፀጥታና መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር ፍሰሐ ጋረደው ገልፀዋል።
ኮሚሽነሩ በማዕከል ደረጃ የተቋቋመው ግብረ-ሃይል በየጊዜው የከተማዋን የሰላምና የፀጥታ ችግሮች እየገመገመ አፈፃፀሙን ሪፖርት የሚያደርግና ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ምክረ ሃሳብ በማቅረብ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት ተግባራዊ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
የጋራ ግብረ ኃይሉ ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የአፈፃፀም ዝርዝር መርሃ ግብር ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የግለሰብን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ቆርጠው ሃይል ያቋረጡ ሦስት ባለሙያዎች ጉቦ ሲቀበሉ መያዛቸውን ፖሊስ ገለፀ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ የግለሰብን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ቆርጠው ሃይል ያቋረጡ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
ወንጀሉ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጨው በረንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይ አቶ ሳህሉ ሀኪም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የንግድ ፍቃድ አውጥተው እንጀራ እያስጋገሩ የሚያከፋፍሉ ግለሰብ ናቸው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመምጣት ቆጣሪ ልናነብና ልንመረምር ነው ካሉ በኋላ የኤሌክትሪክ ቆጣሪውን አይተው 33 ሺህ ብር እንደቆጠረ ለግል ተበዳይ ይነግሯቸዋል፡፡
የግል ተበዳይ አቶ ሳህሉ ሀኪም ያልተጠቀሙበትን ፍጆታ እንደቆጠረባቸውና ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ሲያሥረዷቸው ከተፈቀደልህ በላይ ሃይል ጨምረህ ተጠቅመሃል በማለት የሁለት ቆጣሪዎች ሃይል እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር እሱባለው ጌትነት ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ባለሙያዎቹ 15 ሺህ ብር እጅ መንሻ ጉቦ ከሰጧቸው እንደሚያስተካክሉላቸው ለግል ተበዳይ ነግረው ገንዘብ መጠየቃቸውን የጠቀሱት ምክትል ኢንስፔክተር እሱባለው ጌትነት የግል ተበዳይም ይህን ያህል ገንዘብ እንደሌላቸው እና 10 ሺህ ብር እንዲያደርጉላቸው ተደራድረው ከጠየቋቸው ገንዘብ ውስጥ 5 ሺህ ብር ሲቀበሉ ቀደም ብለው ጉዳዩን ለፖሊስ አሳውቀው ስለነበር ከነ ገንዘቡ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ህዝብ እና መንግስት የጣሉባቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው ህብረተሰቡን የሚያማርሩ ግለሰቦችን ለህግ አጋልጦ በመስጠት ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉ የግል ተበዳይ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 200 ሰዎች ማዕድ አጋሩ
************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለ200 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የማዕድ ማጋራት ስነስርዓት ላይ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባስተላፉት መልዕክት ችግር ሲያጋጥም ተካፍሎ መብላት የቆየ ልምዳችን ነው ብለዋል።
በዒድም ሆነ በፋሲካ በዓላት ማዕድ እያጋሩ አብሮ መብላት ባህላችን ነው፤ ይህንንም አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በማዕድ ማጋራቱ የጓሮ አትክልትን በአነስተኛ ቦታ መጠቀምን ለማስተማር ያለመ በፕላስቲክ ዕቃ የተዘጋጀ የአትክልት ችግኝ ከተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች ተለይተው በማዕድ ማጋራቱ ላይ ለተካፈሉ ዜጎች ተበርክቶላቸዋል።
በማዕድ ማጋራቱ የተካፈሉ ሰዎችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

"የመስጠት ተግባራትን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ከበዓል ሰሞን ባሻገር የመስጠት ተግባራችንን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
“ያለንን ማካፈል የባህላችን አንድ አካል ሆኖ የዘለቀ ዕሴት ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ማካፈል ዐሥር እጥፍ መልሶ የሚያስሸልም ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
“ከበዓል ሰሞን ባሻገር በቀጣይነት የመስጠት ተግባራችንን ማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው” ብለዋል።
በተለያየ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሁሉ 'ማዕድ ማጋራት'ን እንዲያሰፉ አበረታታለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።