Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የግለሰብን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ቆርጠው ሃይል ያቋረጡ ሦስት ባለሙያዎች ጉቦ ሲቀበሉ መያዛቸውን ፖሊስ ገለፀ
**************
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ የግለሰብን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ቆርጠው ሃይል ያቋረጡ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ወንጀሉ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጨው በረንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይ አቶ ሳህሉ ሀኪም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የንግድ ፍቃድ አውጥተው እንጀራ እያስጋገሩ የሚያከፋፍሉ ግለሰብ ናቸው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመምጣት ቆጣሪ ልናነብና ልንመረምር ነው ካሉ በኋላ የኤሌክትሪክ ቆጣሪውን አይተው 33 ሺህ ብር እንደቆጠረ ለግል ተበዳይ ይነግሯቸዋል፡፡

የግል ተበዳይ አቶ ሳህሉ ሀኪም ያልተጠቀሙበትን ፍጆታ እንደቆጠረባቸውና ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ሲያሥረዷቸው ከተፈቀደልህ በላይ ሃይል ጨምረህ ተጠቅመሃል በማለት የሁለት ቆጣሪዎች ሃይል እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር እሱባለው ጌትነት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ባለሙያዎቹ 15 ሺህ ብር እጅ መንሻ ጉቦ ከሰጧቸው እንደሚያስተካክሉላቸው ለግል ተበዳይ ነግረው ገንዘብ መጠየቃቸውን የጠቀሱት ምክትል ኢንስፔክተር እሱባለው ጌትነት የግል ተበዳይም ይህን ያህል ገንዘብ እንደሌላቸው እና 10 ሺህ ብር እንዲያደርጉላቸው ተደራድረው ከጠየቋቸው ገንዘብ ውስጥ 5 ሺህ ብር ሲቀበሉ ቀደም ብለው ጉዳዩን ለፖሊስ አሳውቀው ስለነበር ከነ ገንዘቡ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ህዝብ እና መንግስት የጣሉባቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው ህብረተሰቡን የሚያማርሩ ግለሰቦችን ለህግ አጋልጦ በመስጠት ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉ የግል ተበዳይ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 200 ሰዎች ማዕድ አጋሩ
************
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለ200 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የማዕድ ማጋራት ስነስርዓት ላይ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባስተላፉት መልዕክት ችግር ሲያጋጥም ተካፍሎ መብላት የቆየ ልምዳችን ነው ብለዋል።

በዒድም ሆነ በፋሲካ በዓላት ማዕድ እያጋሩ አብሮ መብላት ባህላችን ነው፤ ይህንንም አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በማዕድ ማጋራቱ የጓሮ አትክልትን በአነስተኛ ቦታ መጠቀምን ለማስተማር ያለመ በፕላስቲክ ዕቃ የተዘጋጀ የአትክልት ችግኝ ከተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች ተለይተው በማዕድ ማጋራቱ ላይ ለተካፈሉ ዜጎች ተበርክቶላቸዋል።

በማዕድ ማጋራቱ የተካፈሉ ሰዎችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"የመስጠት ተግባራትን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ከበዓል ሰሞን ባሻገር የመስጠት ተግባራችንን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

“ያለንን ማካፈል የባህላችን አንድ አካል ሆኖ የዘለቀ ዕሴት ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ማካፈል ዐሥር እጥፍ መልሶ የሚያስሸልም ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

“ከበዓል ሰሞን ባሻገር በቀጣይነት የመስጠት ተግባራችንን ማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው” ብለዋል።

በተለያየ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሁሉ 'ማዕድ ማጋራት'ን እንዲያሰፉ አበረታታለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።