Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 200 ሰዎች ማዕድ አጋሩ
************
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለ200 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የማዕድ ማጋራት ስነስርዓት ላይ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባስተላፉት መልዕክት ችግር ሲያጋጥም ተካፍሎ መብላት የቆየ ልምዳችን ነው ብለዋል።

በዒድም ሆነ በፋሲካ በዓላት ማዕድ እያጋሩ አብሮ መብላት ባህላችን ነው፤ ይህንንም አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በማዕድ ማጋራቱ የጓሮ አትክልትን በአነስተኛ ቦታ መጠቀምን ለማስተማር ያለመ በፕላስቲክ ዕቃ የተዘጋጀ የአትክልት ችግኝ ከተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች ተለይተው በማዕድ ማጋራቱ ላይ ለተካፈሉ ዜጎች ተበርክቶላቸዋል።

በማዕድ ማጋራቱ የተካፈሉ ሰዎችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"የመስጠት ተግባራትን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ከበዓል ሰሞን ባሻገር የመስጠት ተግባራችንን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

“ያለንን ማካፈል የባህላችን አንድ አካል ሆኖ የዘለቀ ዕሴት ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ማካፈል ዐሥር እጥፍ መልሶ የሚያስሸልም ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

“ከበዓል ሰሞን ባሻገር በቀጣይነት የመስጠት ተግባራችንን ማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው” ብለዋል።

በተለያየ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሁሉ 'ማዕድ ማጋራት'ን እንዲያሰፉ አበረታታለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።
የአምነስቲና የሂዩማንራይትስዎች ጥምር የምርመራ ሪፖርት አድሏዊና ችግር ያለበት መሆኑን አብን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስዎች ያወጡት ጥምር የምርመራ ሪፖርት የመረጃ አሰባሰብ፣ የመረጃ ትንተና፣ ድምዳሜውና በመፍትሄነት ያስቀመጡት ሃሳብ አድሏዊና ችግር ያለበት መሆኑን አብን (የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ) ገለጸ፡፡

የአብን ምክትል ሊቀመንበር አቶ መልካሙ ሹምዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ተቋማቱ ያወጡት ሪፖርት ዓለም አቀፍ የምርመራ ደረጃን አያሟላም፤ አድሏዊና ችግር ያለበትም ነው::

የተዛባና የአንድ ወገን ፍላጎትን ለማሳካት የተሰራ፣ ሕወሓት በኃይልና በጠመንጃ አፈሙዝ ሞክሮ ያላሳካውን በዲፕሎማሲና ዓለምአቀፍ ጫና ፈጥሮ ለማሳካት ታቅዶ የተተገበረ ፖለቲካዊ ዓላማን ለማሳካት የተሰራ ሪፖርት መሆኑንም አመልክተዋል::

በተለይም በሰብዓዊ መብት ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ከተባለ ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ መረጋገጥ ይኖርበታል:: ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን በስልክ በማነጋገር ተሰርቷል ያሉትም ቢሆን ተገቢውን የመረጃ አሰባሰብ ደረጃን አያሟላም ብለዋል::

ለሰብዓዊ መብት መከበርና መጠበቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንደግፋለን:: ደረጃቸውን የጠበቁና ገለልተኛ ምርመራዎችም እንዲካሄዱ እንፈልጋለን:: እነዚህ ተቋማት ግን የምዕራባውያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ መሳሪያ ሆነው የሚያገለግሉ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71180

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
"በወልቃይት ጠገዴ ያልተነገረ ካልሆነ በስተቀር ያልተፈጸመ የግፍ አይነት የለም" - ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
*******
(ኢ ፕ ድ)

አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ በተለይም በወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ ሕዝብ ላይ ሳይነገር የቆየ ካልሆነ በስተቀር የግፍና የጭካኔ አይነቶችን ሁሉ መፈፀሙን የወልቃይት ጠገዴና ሁመራ አካባቢ ምክትል አስተዳዳሪና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተናገሩ፡፡

ቡድኑ አንዱን ከፍ፤ ሌላውን ዝቅ በማድረግ የቅኝ ገዢዎችን የአገዛዝ ስርዓት ሲከተል እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

ኮሎኔል ደመቀ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃለምልልስ እንደገለፁት፣ ቡድኑ የውጭ ወራሪዎችን ተልዕኮና ማኒፌስቶ ይዞ ሲሰራ የመጣ ኃይል በመሆኑ ስልጣን ከያዘ በኋላ ህዝቡን በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት እና በአካባቢ እየከፋፈለ እርስ በእርሱ እንዲባላ ሲሰራ የኖረና አሁንም ያንኑ ካላስቀጠልኩ እያለ የሚዋጋ ኃይል ነው::

ሕወሓት ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅድሚያ አማራን ማጥፋት ነው የሚል ትርክት በመያዝም በተለይ በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ግፍና መከራ መፈጸሙንም ተናግረዋል::

ይህ ቡድን በይፋ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስም ቢሆን እንሄዳለን ያለ ኃይል ነው ያሉት ኮሎኔል ደመቀ፤ ይህ ደግሞ ትልቁ የጥፋት ኃይል መሆኑን ምስክር እንደሆነ ጠቁመዋል::

ሕወሓት የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት የሆኑት የውጭ ኃይሎች ታዛዥና ጉዳይ አስፈጻሚ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71170

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
“መሬት ነክ የሆነ አገልግሎት ለማግኘት ገንዘብ እየተጠየቅን ነው” የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች
**************
(ኢ ፕ ድ)

ለሕዝብ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች ምን መልክ አላቸው የሚለውን ለመመልከት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኛ በአዲስ አበባ ከተማ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ተገኝቶ ምልከታ አድርጓል:: በዚህም አገልግሎት ለማግኘት ነዋሪዎች ከሌሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ከቤታቸው ተነስተው ተራ ለመያዝ ክፍለ ከተማው በር መገኘታቸውን ነግረውታል::

የሥራ ሰዓት ደርሶ ሁሉም አገልግሎት ለማግኘት በየፊናው ይራወጣል። ይሁንና በክፍለ ከተማው ውስጥ አገልግሎት ፈላጊዎች እንዴትና የት አገልግሎት ማግኘት እንዳለባቸው መረጃ የሚሰጥ አካል የለም። በተለያዩ ጉዳዮች አገልግሎት ለማግኘት በር ላይ ቆመው የሚጠባበቁ ሰዎች እርስ በርሳቸው አገልግሎት ለማግኘት አሰልች እና አድካሚ መሆኑን ያወራሉ::

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አቶ በላይ አበራ (ስማቸው የተቀየረ) የተባሉ አዛውንት እንደነገሩን ፋይላቸው ከየካ ክፍለ ከተማ ወደ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ተዘዋውሮ የገዙት ቤት የካርታ ሥራው በየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት አልቆ ቤዚክ ማፕ ተረጋግጦ ሊሰጠኝ ሲል ፋይልህ ወደ ለሚ ኩራ ክፍለከተማ ስለተዛወረ እዚያ እንዲሄዱ ይነገራቸዋል:: በተነገራቸው መረጃ መሰረት ወደ ለሚኩራ ክፍለ ከተማው ቢሄዱም አገልግሎት ማግኘት ግን አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ገልጸዋል።

መሬት ነክ የሆነ አገልግሎት ለማግኘት እንዲህ በቀላሉ አትስተናገድም የሚሉት ተገልጋዩ፣ ፋይል ለመፈለግ የእጅ መንሻ የሚሆን ከሁለት ሺ እስከ 40 ሺ ብር ጉቦ የምንጠየቅበት ሁኔታም አለ ይላሉ።

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት እግዱ ከተነሳ በኋላ ባለፈው የካቲት ወር የጀመሩትን የቤት ስም ማዛወር አገልግሎት ሥራው ያለቀ ሆኖ እያለ አገልግሎቱን ሲጠይቁ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71195

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
በሚሌ - ኮምቦልቻ - ወረታ መስመር ኮንቴነሮችን ማስተናገድ መጀመሩን የወረታ ወደብና ተርሚናል ገለጸ
******************
(ኢ ፕ ድ )

በሚሌ - ኮምቦልቻ - ወረታ መስመር ኮንቴነሮችን ማስተናገድ መጀመሩን የወረታ ወደብና ተርሚናል ገለጸ፡፡

ወረታ ወደብና ተርሚናል በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ አስመጭና ላኪዎች የተቀላጠፈ የደረቅ ወደብ አገልግሎት እንዲያገኙ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡

የወደቡ ተጠቃሚዎች እንደገለጹት÷ ከጂቡቲ - ሞጆ - በአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳርና ሌሎች የሰሜን-ምዕራብ አካባቢዎች የሚጓጓዙ ቁሳቁስ አቋራጭ በሆነ መንገድ ከጂቡቲ -ሚሌ -ኮምቦልቻ -ወረታ ለማስገባት አስችሏል።

በተጨማሪም ይደርስ የነበረውን የጊዜና የገንዘብ ብክነት ቀንሷል።

የወረታ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ አያሌው ወደቡ ብዛት ያላቸው ኮንቴነሮች ማስተናገዱን ጠቅሰው፥ በ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግን በአሸባሪው ቡድን ወረራ ምክንያት መንድ በመዘጋቱ 1 ሺህ 520 ኮንቴነሮችን ብቻ እንዳስተናገደ ተናግረዋል።

በወጪ ደረጃ ሲታይ አንድ ትልቅ ኮንቴነር ከጅቡቲ - ኮምቦልቻ - ወረታ ሲመጣ እስከ 60 ሺህ ብር ወጪ ሲኖረው ከጅቡቲ በአዲስ አበባ ወረታ ሲገባ ግን እስከ 200 ሺህ ብር ወጪ እንዳለው ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል።

ሥራ አስኪያጁ በቅርቡ የተጠገነው የጨረቲ ወንዝ ድልድይ ለአገልግሎት ክፍት በመሆኑ ኮንቴነሮች በሚሌ - ኮምቦልቻ - ወረታ መምጣት መጀመሩን አመላክተዋል።

አሁን ላይ መንገዱ ክፍት መኾኑ ታውቆ አስመጭና ላኪዎች ወረታ ወደብና ተርሚናልን በመጠቀም የተለመደ ንግድና ኢንቨስትመንታቸውን ማስቀጠል እንደሚችሉ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡