መገናኛ ብዙሃን ለአገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
****
(ኢ ፕ ድ)
መገናኛ ብዙሃን ለአካታች አገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ሰፊ ሽፋን ከመስጠት ጀምሮ ሙያዊ ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ትላንት ውይይት አካሂዷል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በመድረኩ ባደረጉት ገለጻ፤ መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛውን የውይይት ጽንሰ ሀሳብ፣ የአጀንዳ ቀረጻ አካሄድ፣ የውይይት ሂደትና ትግበራ፣ በየቋንቋዎቻቸው ለሕዝቡ በየወቅቱ ተደራሽ በማድረግ የኮሚሽኑ አጋር እንዲሆኑና ለምክክሩ ስኬታማነት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
ኮሚሽነሩ፤ ሚዲያ እውቀትን፣ እውነትን፣ ፍቅርን፣ ሠላምን፣ እድገትንና መተባበርን በቀላሉ በአፍ መፍቻ ቋንቋው በተዓማኒነት ለህዝብ የሚያደርስ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአካታች አገራዊ ምክክሩ ላይም ይህንኑ ኃላፊነት ለመወጣት ከኮሚሽኑ ጋር በአጋርነት እንዲሰራ ጠይቀዋል።
ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅን፣ የምክክርን ጽንሰ ሀሳብና አስፈላጊነት በህትመት፣ በቴሌቪዥን፣ በራዲዮና በማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ መገናኛ ብዙሃን ሲሰሩ እንደነበር ጠቅሰው፤ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይ ሚዲያው ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ የማስተማር ሚናቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በአዋጅ ለኮሚሽኑ ተቆጥሮ የተሰጡ ኃላፊነትና ተግባር በአይነቱ ለአገሪቱ አዲስ ሲሆን፤ ለውጭውም ተምሳሌታዊ ነው ብለዋል።
አገራዊ ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት የሚዲያ አጋርነት ሚና አይተኬ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ለሕዝቡ ተደራሽ እንዲሆን እያንዳንዱ የሚዲያ ተቋም ከምክክር ኮሚሽኑ የሚዲያና ተግባቦት ዘርፍ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71362
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ክልሉ የዜጎችን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት ማጠናከር እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የዜጎችን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳሰበ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ፣ በባቱ እና በአዳማ ከተሞች የመስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ሲሆን ምልከታ ባደረገባቸው ከተሞች የሴቶች ተጠቃሚነት፣ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ፣ ለአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች የሚደረገውን ድጋፍ የተሻለ ውጤት የታየባቸው መሆኑን ኮሚቴው አመላክተዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወርቅሰሙ ማሞ በአዳማ ከተማ የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ያለበት የመዋቅርና የበጀት ችግር መፈታት እንዳለበት ጠቁመው፤ በበጎ አድራጎት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች መንግስትና ህዝብን በማሳተፍ አረጋውያንን እና ጎዳና ተዳዳሪ ህጻናትን በማንሳት በቋሚነት እየረዱ መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
ጉብኝት በተደረገባቸው ከተሞች፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረትና አመራሩም የተሻለ የህዝብ አገልጋይ ለመሆን ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡
በሌላ በኩል በአዳማ የሚገኘው የአካል ተሀድሶ ማምረቻ ማዕከል፤ ለአካል ጉዳተኛ ዜጎች የሚያገለግሉ መሳሪዎችን እያመረተ ቢሆንም የበጀት፣ የሰው ሀይል፣ የማሽን እና የጥሬ እቃ ግብዓት ችግሮች እንዳሉበት የገለጹት የቋሚ ኮሚቴው አባላት፤ እነዚህ ችግሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ምክትል አፈ-ጉባኤ ኤሊያስ ኡመታ፤ በክልሉ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብልሹ አሰራሮች ተለይተው እንዲቀረፉ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዉ ፤ የቋሚ ኮሚቴው ግብረ- መልስ እንደ ግብዓት የሚወሰድ ነው ማለታቸዉ ተመልክቷል፡፡
የክልሉ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ሠሚራ ፋሪስ በበኩላቸው እንደ ክልል ለህዝቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ እስከ ወረዳ ድረስ መዋቅር የተዘረጋ መሆኑን መግለጻቸዉን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

ማህበረሰቡ ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ከሚሸጡ ህገወጦች እንዲጠነቀቅ ፖሊስ አሳሰበ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በዓላት ተከትሎ የምግብ ምርቶችን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ከሚሸጡ ህገወጦች ማኀበረሰቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።
ከስቅለትና ፋሲካ በዓላት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎችና የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መጪው የስቅለትና የፋሲካ በዓልን ተንተርሶ በርከት ያለው የማኀበረሰብ ክፍል የተለያዩ የምግብ ምርቶችንና ቁሳቁሶች ሲገበያይ ከሕገወጦች መጠንቀቅ አለበት።
በሕገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖች አጋጣሚዎችን በመጠቀም የተለያዩ የማታለል ተግባራቶችን ሊፈጽሙ ይችላሉ ያሉት ኮማንደሩ፤ በምግብ ውስጥ በተለይም በዘይት፣ ቅቤ፣ በርበሬና ሌሎች ምርቶች ውስጥ ባዕድ ነገሮችን ቀላቅሎ የሚሸጥ አጭበርባሪ ይኖራል ብለዋል።
እንዲህ ያሉ ወንጀሎች ከመፈጠራቸው በፊት ፖሊስ አስፈላጊውን የቅድመ መከላከል...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71391

ህዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመደገፍ ሊሆን ይገባል-ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
******
(ኢ ፕ ድ)
ህዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከበር የተቸገሩትን በመርዳትና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል አሳሰቡ።
የጋምቤላ ፣የቤንሻንጉል፣ የምዕራብ ወለጋ፣የቄለም ወለጋና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የትንሳኤን በዓል በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝበ ክርስቲያኑ አብሮነቱንና አንድነቱን በማጠናከር እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመረዳዳት በዓለ ትንሳኤውን ሊያከበር ይገባል።
በዓለ ትንሳኤ ክርስቶስ የአዳም ዘርን ነፃ ያወጣበት ክብረ በዓል በመሆኑ ህዝበ ክርስቲያኑ የዘረኝነትና የጎሰኝነት አስተሳሰቦችን በማስወገድ በዓለ ትንሳኤውን በአንድነትና በመደጋገፍ እንዲያሳልፈው አሳስበዋል።
እንደ ኢዜ ዘገባ በጋምቤላና በቤሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ህዝበ ክርስቲያን በዓሉን በፍቅርና እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲያከብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በሀገሪቱ ለተጀመረው የሰላም ግንባታና የለውጥ ጉዞ ስኬታማነት ምዕመኑ የበኩሉን እንዲያበረክት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ጥሪ አቅርበዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ213 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ስድስት ስምምነቶችን ተፈራረመ
****
(ኢ ፕ ድ)
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ213 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሰድስት ስምምነቶችን ተፈራረመ፡፡
ከ41 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው በጦርነቱ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን እያስተናገዱ ላሉትና በዚህ ሳቢያ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ላይ ተግዳሮት ለገጠማቸው 4 ከተሞች ጎንደር ፣ባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃናና ሰመራ- ሎጊያ የሚውል ነው፡፡
ከስድስቱ ሁለቱ ስምምነቶች ለአራቱ ከተሞቹ 11 የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ መሳቢያ ፓምፖችና 9 ጀኔረተሮች ለማቅረብ ነው።
ቀሪ አራት ስምምነቶች፤ ሦስቱ ለ22 ከተሞች 44 ሞተር ሳይክሎችን፣ ማጓጓዝን ጨምሮ 10 ሰርፌስ ፖምፖቹን፣ ለ22 ከተሞች ቧንቧዎችና የባንቧ መገጣጠሚያዎችን ለማቅረብ የተደረጉ ናቸው፡፡
ቀሪው አንድ ስምምነት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የመጠጥ ውሃ ችግር ባለባቸው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጠምባሮና ዛላ ወረዳዎች የውሃ ምንጭ ፍለጋ፣ የአዋጭነት ጥናት ፣ ዝርዝር ዲዛይን ሥራና በጉድጓድ ቁፋሮ ወቅት የፕሮጀክት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥራን ለማከናወን የተደረገ ነው፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ለአራቱ ከተሞች የሚቀርቡት ጠላቂ ፓምፖች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉ ዜጎች ውሃ በማቅረብ ረገድ በየከተሞቹ ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ይቀርባሉ።
ቀሪዎቹም ኮንትራቶች በስምምነቶቹ መሠረት ተግባራዊ እንዲደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ለተዋዋዮቹ ወገኖች አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር እንደሚደርግ አመልክተዋል፡፡
ስምምነቶቹ ከሁለት እስከ 9 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የኢሙ ጠቅላላ አስመጪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የድዛሚል ጀነራል ትሬዲንግ፣ ፀሜክስ ግሎባል ኢንተርፕራይዝና መታፈሪያ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ተወካዮችም በስምምነታቸው መሠረት በጊዜ ግዴታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡
በስምምነቶቹ የተመለከተው ክፍያ ለሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራምና ለሁለተኛው የአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ከተያዘውን በብድር ከተገኘው ገንዘብ የሚሸፈን ነው፡፡

በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች‼️
👉 በለውጥ ጎዳና ላይ በመጓዝ ዴሞክራሲን የሚገነቡ ሀገራት በሁለት ጫፍ መካከል የሚቆም ፈተና ይገጥማቸዋል፤
👉 በአንዱ ዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባት ሲሆን ሌላ የሀገርንና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በጥብቅ ርምጃዎች ማስከበር ነው፣
👉 ዴሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት ስንነሣ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ ጥብቅ ዕርምጃዎች በነጻነትና በመብት ስም እንዳይላሉ በሚዛን መንቀሳቀስ ይገባል፣
👉 ሁለቱን በሚዛን ለማከናወን ደግሞ የእያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ ፓርቲ፣ ቡድን፣ ወገን፣ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት፤ የህግና የጸጥታ ተቋማትም ሕገ መንግሥታዊና ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፣
👉 ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሕዝብና ሀገርን ሰላም የሚነሡ አካላትን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሕዝብን ሰላም የሚነሡና በተላላኪነት የሚያገለግሉ ቡድኖችን በጥናትና በመረጃ በመለየት አስፈላጊው ሁሉ ሕግ የማስከበር ርምጃ እንዲወሰድ የደኅንነት ምክር ቤቱ ወስኗል፣
👉 የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥመንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል፣
👉 ወላጆች ልጆቻችሁን፣ ሽማግሌዎች ወጣቶቻችሁን፣ የሃይማኖት አባቶች ምእመኖቻችሁን፣ የፓርቲ መሪዎች አባሎቻችሁን፣ የጎሳ መሪዎች ወገኖቻችሁን በመምከር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከግጭትና ከሽብር ራሱን አርቆ፣ ለሰላምና ለሀገር ደኅንነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ተጠይቋል፣