EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በትግራይ ክልል እየተካሄደ ነው
*******************

በትግራይ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአፅቢ ወምበርታ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል።

በትግራይ ክልል በአንድ ጀምበር ሶስት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ነው መርሃ ግበሩ በይፋ የተጀመረው።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንደትግራይ ክልል በ64 የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች 10 ሚሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውንም የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

ዛሬ በክልሉ በአንድ ጀምበር 3 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተለያዩ የችግኝ አይነቶች የተዘጋጁ ሲሆን በ45 ወረዳዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ።

በአስማረ ብርሃኑ
👍5419👎12👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕለቱ ለሁለተኛ ጊዜ ባደረጉት ችግኝ ተከላ በየካ ተራራ ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጋር በመሆን የ500 ሚልዮን በአንድ ቀን የአረንጓዴ ዐሻራ ተከላ ላይ ተሳትፈዋል።
👍7632👎29👏6
ከማለዳው አንስቶ እስከ 8:45 ድረስ 372 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል
*****************

ከማለዳው አንስቶ እስከ 8:45 ድረስ 372 ሚሊየን 500 ችግኞች መተከላቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ከሁነቶች መከታተያ ክፍል ተጨማሪ መረጃዎች እስከመርሐ-ግብሩ ማጠናቀቂያ ድረስ መድረሱ ይቀጥላል።

በምሥክር ስናፍቅ
👍59👎2423👏1
የውጭ ሀገራት መገናኛ ብዙኃን በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐ-ግብርን ሽፋን ሰጥተው እየዘገቡ ይገኛሉ
********************

የቱርኩ ቲ.አር.ቲ-አፍሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከፍተኛ የችግኝ መትከል ዘመቻ ማካሄድ መጀመራቸውን በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል።

ኢትዮጵያ በቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር ላይ እያካሄደ እንዳለ ይህም በቀን ውስጥ በርካታ ችግኞችን በመትከል የዓለምን ሪከርድ የሚሰብር መሆኑን ነው የሚዲያው አውታሩ የዘገበው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መርሐ-ግብሩን ዛሬ ማለዳ የአፕል ችግኝ በመትከል እንዳስጀመሩትም ቲ.አር.ቲ አስነብቧል።

የቻይናው ሲጂቲኤን-አፍሪካ በበኩሉ፣ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በ12 ሰዓታት ውስጥ ለመትከል የሚያስችል ታላቅ መርሐ-ግብር መጀመሩን ገልጾ፣ ይህ ከተሳካ፣ የምሥራቅ አፍሪካን የደን ሽፋን ለማሻሻል ለታቀደው ዕቅድ ትልቅ ብሔራዊ አሻራ ይሆናል ሲል ዘግቧል።
👍15143👎28👏5
ኢትዮጵያ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ምን አሳካች? ምንጭ - ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
34👍29👎13👏5
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተካፋይ የነበሩ የትግራይ እግርኳስ ክለቦችን ከመክሰም ለመታደግ ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ሊካሄድ ነው
*********************

በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው መቀለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ስሁል ሽረ ከኢዋይ ፕሮዳክሽን ጋር በመሆን ለ60 ቀን የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ማዘጋጀታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ክለቦቹን ለመደገፍ በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ፕሮግራሞች ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገልጿል።

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብሩ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል አመራሮች በሚገኙበት መክፈቻውን አዲስ አበባ መዝጊያውን መቀሌ በማድረግ ይካሄዳል ተብሏል።

በፉአድ እድሪስ
👍34👏2411👎10
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ
*****************************

ኢትዮ ቴሌኮም የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀሙን በተመለከተ ለሚዲያዎች መግለጫ እየሰጠ ነው።

ተቋሙ በ2015 በጀት ዓመት 75.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።

ተቋሙ 18.7 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱም ተነስቷል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0E4zmQq9ju1SRKgH7YzFiB8ggcg15PKpErhccggqJCvk3ReeModN1tmmSHZKmxeCvl
👍56👏16👎145
በአውሮፓ የተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት መጠን አስጊ ደረጃ ደርሷል
***********************

በተለይ በደቡባዊ አውሮፓ በቀጣይ ሳምንታት የሙቀት መጠኑ 46 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ ዘግቧል።

የጣሊያኗ ደሴት ሳርዲኒያ እስከ 46 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የደረሰ ሲሆን፤ በቀጣይ 10 ቀናት ከፍተኛ ሙቀት ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ ነው።

ስፔን በተመሳሳይ ተከታታይ የሆነ የሙቀት ማዕበል የገጠማት ሲሆን፤ በተለይ በደቡባዊ የሀገሪቱ አካባቢ የሙቀት መጠኑ 44 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ደርሷል።

በተጨማሪ፥ በስፔኗ ደሴት ላፓልማ እና በግሪክ የሰደድ እሳት ተከስቷል።

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሙቀት መጠኑ 49 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መድረሱም ነው የተገለፀው።

የሙቀት መጠኑ መጨመር በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው ጠቋሚ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የሚቲዎሮሎጂ ማህበር አሳስቧል።
👍62👎8👏65
በሀገሪቱ በቂ የሆነ የስኳር መድሀኒት ስርጭት እና መጠባበቂያ አለ - የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት
**********************************************

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የስኳር ህሙማን መድሀኒት በተለይም “Humulin70/30” የተባለው የመድሃኒት ዓይነት በቀላሉ ለማግኘት መቸገራቸውን ሲገልጹ ተስተውሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢቢሲ ሳይበር የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ሰለሞን ንጉሴን አነጋግሯል።

አቶ ሰለሞን ተቋሙ በግዢ የሚያቀርባቸው ህይወት አድን እና መሰረታዊ መድሃኒቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከውጭ እንደሚያስገባ ገልጸው፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ መሰናክሎች የአቅርቦት መቆራረጥን እንደሚፈጥሩ ጠቁመዋል።

ነገር ግን ተቋሙ ዜጎች እድሜ ልክ የሚወስዷቸው መድሃኒቶችን ቅድሚያ በመስጠት የማቅረብ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ ባለፉት 2 ዓመታት ምንም አይነት የስኳር መድሃኒት አቅርቦት ችግር እንዳልገጠመ ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0t55HjqaAQpiAnZvgZYiv6gazoDWwfeatPQmxnPE5Pk8c263fBxZWNYdzNgcf4V5Fl
👍74👎1815
ከ20 በላይ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው
***********

በአገሪቱ የሚገኙ ከ20 በላይ ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አዲስ አበባ፣ ወለጋ፣ ደብረብርሃን፣ አርባምንጭ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ እና ሰመራ ዩኒቨርስቲዎች ይገኙበታል፡፡
👍8216👎8👏2