EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተሳትፎ በዛሬው የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ
👍76👎1716👏4
በመላው ሀገሪቱ እስከ 5:30 ባለው ሰዓት 247 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
************

ከሁነቶች መከታተያ ክፍል (situation room) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ፤ በመላው ሀገሪቱ እስከ 5:30 ባለው ሰዓት 247 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ገልፀዋል፡፡

ከ9 ሺህ በላይ የችግኝ ጣቢያዎች አሁንም መረጃዎችን ወደ ማዕከሉ እየላኩ እንደሚገኝ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02pNNCEwDyy1AcDvajdcn94AyQn3UeZhb4hJJuQYkFMFWGqWUiufVxxAxg9eZCzHuXl
👍21👎178
በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በትግራይ ክልል እየተካሄደ ነው
*******************

በትግራይ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአፅቢ ወምበርታ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል።

በትግራይ ክልል በአንድ ጀምበር ሶስት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ነው መርሃ ግበሩ በይፋ የተጀመረው።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንደትግራይ ክልል በ64 የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች 10 ሚሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውንም የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

ዛሬ በክልሉ በአንድ ጀምበር 3 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተለያዩ የችግኝ አይነቶች የተዘጋጁ ሲሆን በ45 ወረዳዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ።

በአስማረ ብርሃኑ
👍5419👎12👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕለቱ ለሁለተኛ ጊዜ ባደረጉት ችግኝ ተከላ በየካ ተራራ ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጋር በመሆን የ500 ሚልዮን በአንድ ቀን የአረንጓዴ ዐሻራ ተከላ ላይ ተሳትፈዋል።
👍7632👎29👏6
ከማለዳው አንስቶ እስከ 8:45 ድረስ 372 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል
*****************

ከማለዳው አንስቶ እስከ 8:45 ድረስ 372 ሚሊየን 500 ችግኞች መተከላቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ከሁነቶች መከታተያ ክፍል ተጨማሪ መረጃዎች እስከመርሐ-ግብሩ ማጠናቀቂያ ድረስ መድረሱ ይቀጥላል።

በምሥክር ስናፍቅ
👍59👎2423👏1
የውጭ ሀገራት መገናኛ ብዙኃን በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐ-ግብርን ሽፋን ሰጥተው እየዘገቡ ይገኛሉ
********************

የቱርኩ ቲ.አር.ቲ-አፍሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከፍተኛ የችግኝ መትከል ዘመቻ ማካሄድ መጀመራቸውን በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል።

ኢትዮጵያ በቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር ላይ እያካሄደ እንዳለ ይህም በቀን ውስጥ በርካታ ችግኞችን በመትከል የዓለምን ሪከርድ የሚሰብር መሆኑን ነው የሚዲያው አውታሩ የዘገበው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መርሐ-ግብሩን ዛሬ ማለዳ የአፕል ችግኝ በመትከል እንዳስጀመሩትም ቲ.አር.ቲ አስነብቧል።

የቻይናው ሲጂቲኤን-አፍሪካ በበኩሉ፣ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በ12 ሰዓታት ውስጥ ለመትከል የሚያስችል ታላቅ መርሐ-ግብር መጀመሩን ገልጾ፣ ይህ ከተሳካ፣ የምሥራቅ አፍሪካን የደን ሽፋን ለማሻሻል ለታቀደው ዕቅድ ትልቅ ብሔራዊ አሻራ ይሆናል ሲል ዘግቧል።
👍15143👎28👏5