Ashara Media - አሻራ ሚዲያ – Telegram
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
79.3K subscribers
24.7K photos
1.17K videos
24 files
9.65K links
ስልክ፥ +251984000629 / +251993111700
Download Telegram
ቀጥሏል . . . ተራ በተራ .. ቀጣዩ ማን ነው?

👉ጳጳሳት በተገኙበት እንዲታሰሩ  ማዘዣ ወጣባቸው ይሉናል የብል~ግና ካድሬዎች ፣

👉ይሁን እንጂ  ማዘዣ ወጣባቸው  የተባሉትም ሆነ ሀገር እንዳይገቡ ዲፖርት ተደረጉ የተባሉትም ጳጳሳት ግን እስካሁን ትንፍሽ የለም ግን ዝምታቸው እስከ መቼ ነው ?  ወይስ መንግሥት የሚፈልገውን ሰርቶ እስኪጨርስ እነሱም ተባባሪ ለመሆን ነው ?

👉 በእርግጠኝነት ለመናገር ዝምታችሁ ግን ብዙ ዋጋ ያስከፍላችኋል ፣ የመኖራችሁ ህልውና ቤተክርስቲያን ናት ከዚህ በላይ ምን እስኪሆን  ነው የምጠብቁት

👉 በሌላው ላይ የተደረገውን ወገኔ ብላችሁ ኖላዊነታችሁ ባትገልጹም  ፣ በእናንተ ላይ የሆነውን እንኳን መክራችሁ እና ዘክራችሁ በአንድ ልብ እና በአንድ መንፈስ ሆናችሁ ለምትመሩት ሕዝብ ባላችሁ ድምፃችሁን አሳሙ ። አልያ ግን በትብብር ለመስራት የተስማማቹህ ነው   የሚመስለው በተራ ።።
👍36🥰97😢2🤯1😱1
ሰበር ዜና-የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ
⨳⨳⨳
የማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው ቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ቋራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ። ክፍለጦሩ አዳሩን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ያደረ ሲሆን በመጨረሻም ሶስት ካፖችን መደምሰስ ችሏል።

አሶል አካባቢ የሚገኘ የሚሊሻ እና የፀረ ሽምቅ ካፕ፣ ሽመልእግር መውጫ የሚገኝ የአድማ ብተና ካፕ እና አለሙ በር አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ሐይል ካፕ ሙሉ በሙሉ የተመቱ ሲሆን አድማ ብተና፣ፀረሽምቅ እና ሚሊሻ እጅ የሰጠው እጅ ሰጥቶ የተረፈው ተረሽኖል ያለው የክፍለጦሩ አዛዥ እራሱን የመከላከያ ሐይል ብሎ የሚጠራው ገዳይ ቡድን ከተመታው እና ከተማረከው የተረፈው ካፑን ጥሎ በመፈርጠጥ ወደ ጎረቤት ሐገር ሱዳን ተጠግቷል ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ በኩል ያለው መስመሩ የተቋረጠበት ሲሆን አልጣሽ ፓርክ ከመግባት እና ወደ ጎረቤት ሐገር ከመሻገር የዘለለ አማራጭ የለውም ብሏል። የነብስ አውጭኙን በከባድ መሳሪያ ከርቀት እየተኮሰ እየፈረጠጠ እንደሚገኝ እና ፋኖም እየተከተለ እያሳደደው እንደሆነ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ለሚዲያችን ተናግሯል።
በተልዕኮው በቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦረ ስር የሚገኙ 100 አለቃ ደጀኔ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድ እየተሳተፋ ይጋኛል ሲል ሻለቃው ተናግሯል።
መረጃው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ነው!
ግንቦት 13/2016 ዓ/ም
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለአማራ ፋኖ!
ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍106😱5🥰1
34👍7
ዛሬ አዳሩን በደሴ ከተማ ከባድ ውጊያ መካሄዱ ተሰማ!

የደቡብ ወሎ ዞን መቀመጫ በሆነችው ደሴ ከተማ ጦሳ ተራራ ላይ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ መካሄዱን የአማራ ድምፅ ሚድያ በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የኮማንዶ አዛዡ ፋኖ ዮሴፍ አስማረን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።

በጦሳ ተራራ አቆራርጦ ወደ ከተማዋ ዘልቆ መግባት የቻለው አንድ የኮማንዶ ሻለቃ ፋኖ በርካታ የገዢው ቡድን ወታደሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን ኮማንዶ ዮሴፍ ጨምሮ ገልጿል።

አጥቢያ ለሊት ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ለሊቱ ስምንት ገደማ ድረስ በዘለቀው ውጊያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ታውቋል።

ፋኖዎች መስራት የሚፈልጉትን ስራ ፈፅመው ጦሳ ተራራን ለቀው መውጣታቸው ሲገለፅ፡ ነገር ግን አገዛዙ እስከ ንጋት ድረስ አከባቢውን በከባድ መሣሪያ ሲደበድብ ማደሩንም የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
👍105🤯53
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
#ሰበር_ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ከቱሉገና ከተማ ወጣ ብሎ ጫንጫ ተብሎ የሚጣራው አካባቢ የአገዛዙ ሊኮፍተር ዝቅ ብላ አሰሳ እያደረገች ባለችበት ስዓት ምን አደጋ እንደደረሰባት ለግዜው ባይታዎቅም ከአፈር ተቀላቅላለች ሲሉ የካባቢው ኗሪዎች ገልጸዋል። በኢራን ላይ የደረሰው የሂልኮቭተር መከስከስ በረከቱ በብልፅግናም እንደሚደርስ ጠቋሚ ነው። ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ…
የተከሰከሰውን የድሮን ቅሪተ አካል ለማንሳት መነሻውን ደብረዘይት ያደረገ ባለሞያዎችን ጭምር ያካተተ ቡድን ቱሉጋና ከተማ መግባቱን በቅድሙ ዜና እወጃችን ገልፀን ነበር።

የተጓዙባት ሄሊኮፍተር በርካታ የአማራ ተወላጆች በሚገኙባት ቱሉ ጋና ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ!
👍81🤯76
~ እጅግ አስቸኳይ አሁናዊ መረጃ!

በዚህ ሰዓት በ4 ካሶኒ የተጫነ አራ*ዊት ሰራዊት ከባህርዳር ከተማ ወደ ደቡባዊ ጎንደር ደራ ወረዳ በጎዞ ላይ ይገኛል።

መረጃው ለቀጠናው የወገን ኃይል በተለያዩ አማራጮች ሁሉ ይድረስ!
👍151
ሰበር ዜና!

ደቡብ ጎንደር አርብ ገበያ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷ ተሰማ!

የአማራ ፋኖ በጎንደር የሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ ክ/ጦር አርብ ገበያ ከተማን መቆጣጠሩን የአማራ ድምፅ ሚዲያ የጎንደር ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል።

ከተማዋ በፋኖ እጅ የገባችው ትናንት ግምቦት 14/2016 ዓ/ም ሲሆን፡ በውጊያው ከ20 በላይ ምርኮኛ የገዢው ቡድን ወታደሮችና በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሣሪያ በፋኖ መማረኩንም ነው የጎንደር ዘጋቢዎቻችን ያረጋገጡት።
74👍44🔥3🥰2👏2
🔥#ቲሊሊ_አዊ_አማራ‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም በአገው ምድር ክፍለጦር ዘንገና ብርጌድ ከጠዋት በመጀመር ከቲሊሊ ወደ ሰከላ በመንቀሳቀስ የነበረውን ሀይል አሽፋ መገንጠያ ላይ እያበራየው ይገኛል💪

ዝርዝር መረጃውን ውጊያው እንደተጠናቀቀ ይዘን እንመለሳለን‼️
👍666🔥3
ባህርዳር የውንብድና መነሐሪያ ሆናለች፦
=======///========
የባህርዳር ከተማ አገዛዙ በአሰማራቸው ወንበዴዎች በየእለቱ በሚፈጸም ውንብድና ነዋሪው ተማሯል።

በከተማዋ ውስጥ የፋኖ ኃይሎች ባለመኖራቸው የቡድን ዘራፊዎች ያለ አንዳች ከልካይ በጠራራ ጸሀይም ሆነ በጨለማ  ህዝቡን እየበዘበዙት ይገኛሉ። በየእለቱ እንዲህ አይነት ወሬ መስማት የተለመደ ድርጊት ሆኗል።

ድርጊቱ በተለይም በርካታ ነዋሪ በሚገኝባቸው የዳግማዊ ምኒሊክ ክ/ከ፣ ጣና ክ/ከ፣ ሽንብጥ ክ/ከተማ በህግ የተሰጠ መብት እስኪመስል ድረስ ወንጀሉ በከፍተኛ ደረጃ የሚፈጸምባቸው ናቸው።
ጥንቃቄ፦
፨ አዞል አካዳሚ ጀርባ
፨ ከኖክ ወደ አኮቴት መስመር
፨ ከባለእግዚአብሔራ እስከ ተባበሩት ወዘተ የወንበዴዎች ዋና ምሽግ መሆናቸውን ደርሰንበታል።
👍645🤯4🥰3
መረጃ
ፋሽስታዊ አገዛዙ ሲኖዶሱን የማፈራረስ አሻጥራዊ ተልዕኮውን ገፍቶበታል።
  👉 ዛሬ በአትላንታ ኤርፖርት ምን ተፈጠረ

✍️ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጅያና አካባቢው ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የትኛውም የመንግሥት ሚዲያዎች ሳይዘግቡ  በካድሬው ናትናኤል በኩል ብቻ  መንግሥት እንደከሰሳቸው እና በተገኙበት ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ማዘዣ እንደወጣባቸው  (Creditional Document ) የአሜሪካ ፓስፖርታቸውን ጭምር በገጹ ለጥፎ  መዘገቡ ይታወቃል ፦

✍️ብፁዕነታቸው ይህንን መረጃ ካሉበት ስቴት የሚያውቋቸው እንዲህ ተብለዋል ቢባሉም ፣ እኔ ምን አድርጌ ፣ የሰረሁት ወንጀል የለም በማለት መልስ በመስጠት ስለሁኔታው ነገሩን ለማጣራት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤንባሲ አባሳደር ጋር  በቀጥታ ስልክ ቢደውሉም ወጣ ስለተባለው መረጃ አምባሳደሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በስልክ ያሳወቋቸው ሲሆን ፦

✍️ይህ በእንዲህ እንዳለ ቀደም ሲል ለግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ቲኬት ቆርጠው ከአትላንታ ወደ ኢትዮጵያ በረራቸው ዛሬ 11:00Am EST ላይ ነበር ፦

✍️ኤርፖርት ሲደርሱ የገጠማቸው ግን እጅግ አስገራሚ ነው ፣ ቲኬት የቆረጡት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመሆኑ  ቦርዲንግ ፓስ( Boarding pass )  ለመውሰድ ፓስፓርታቸውን ሰጥተው ሲጠባበቁ ቲኬቱ (Cancelled) እንደተሰረዘ ፣ ቢጫ (Yellow Card) ካርዳቸውም (Deactivate) እንደማይሰራ  ( ቢጫ ካርድ አዲስ ከተሰጣቸው ሁለት ወር እንዳልሆነ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል) በዚህ ምክንያትም ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ እንደማይችሉ በኢትዮጵያ አየር መንገዱ ሠራተኛ  ይነገራቸዋል ፦

✍️ በሁኔታው የተገረሙት ብፁዕነታቸውም ለምን እንዲህ እንደሆነ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ሰራተኞቹን ብሎም ኃላፊዎቹን ቢጠይቁ  ትዕዛዙ ከላይ እንደሆነ የተፈጠረውንም ምንም እንደማያቁት ቢነገራቸውም በድጋሚ አምባሳደሩ ጋር  ደውለው ቢጠይቁም የአምባሳደሩ ምላሽ በድጋሚ አሁንም ምንም እንደማያውቁ እና አጣርተው ለብፁዕነታቸው በስልክ እንደሚያሳውቁ  ምላሽ ቢሰጡም እስካሁን ማንም ምላሽ ሳይሰጣቸው ዛሬ ኤርፓርት ተጉላልተው ወደ ቤታቸው ለመመለስ መገደዳቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ከትላንታ አርሰውኗል 
👍646😢3
https://youtu.be/dQC0lp_mZsI?si=Lfl5kuDZxSUQQhWn

ሰብስክራይብ እያደረግን እናበርታው ወንድማችን ሀብታሙን
👍9212🔥5🥰1
በጎንደር ግዛት ሳምንት በሞላው መጠነ ሰፊ ውጊያ የአማራ ፋኖ በጎንደር ሰራዊት በከፍተኛ ድል መገስገሱን ቀጥሏል
በጎንደር ግዛት የተለያዩ ግንባሮች ላለፉት ሰባት ቀናት ገደማ በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ ባለው ውጊያ በፋኖ ሰራዊት ላይ ጥቃት ለመክፈት ልዩ ዝግጅት ሲያደርግ የከረመው የብልፅግና ቡድን ሰራዊት ያልተጠበቀውና ያልገመተው ሽንፈት ገጥሞታል።
በጎንደር ግዛት የቀጠለውን ውጊያ ጨለማ ብቻ የሚከልለው የሙሉ ቀን ጦርነት መሆኑንም ሮሃ ከፋኖ አመራሮች አረጋግጣለች።
ውጊያውንና የፋኖን ከፍተኛ ድል አስመልክቶ ለሮሃ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጠው የአማራ ፋኖ በጎንደር የህዝብ ፋኖ ኢያሱ አባተ እጅግ የሚያስደንቁ ጀብዱዎች በፋኖ ሰራዊት እየተፈፀሙ መሆኑን በስልክ ነግሮናል።
ከፍተኛ ድል የተገኘበትና ሰባተኛ ቀኑን የያዘው ተጋድሎ የአማራ ፋኖ በጎንደር በጉና ክፍለ ጦር እንዲሁም በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦርን ጨምሮ በተለያየ አደረጃጀት ስር ባሉ የፋኖ ተዋጊዎች ከባድ ትንቅንቅ መካሄዱን ቀጥሏል።
በገላውዲዮዎስ ከተማና አዋሳኝ አካባቢው በናሁሰናይ ብርጌድና ተስፋየነው ቢራራ ብርጌድ እንዲሁም ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ የተሰዋበት ውባንተ ተራራ ላይ የተፈፀመው ገድል ታሪካዊ የሚባል እንደሆነ ፋኖ ኢያሱ ይገልፃል።
የአገዛዙ ጦር በተወሰደበት እርምጃ ገላውዲዮስ ከተማን ለቆ ሲወጣ  አርብ ገበያም መግባት እንዳልቻለና ወደ ማህደረ ማርያም አቅጣጫ በየተራራው መበታተኑንም ፋኖ ኢያሱ ገልፆልናል።
ቡድኑ ከተበተነ በኋላ መምሸቱንና መተያየት እንዳልተቻለ የገለፀው ኃላፊው በመምሸቱ የአገዛዙን ጦር ሙትና ቁስለኛ ቁጥር በትክክል ማወቅ እንዳልተቻለና ገበሬውን የተወሰነውን እየቀበረ እንደነበር አስረድቷል።
የምርኮኛ አያያዝንና የምህረት አዋጅን በተመለከተ የአማራ ፋኖ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ፋኖ ኢያሱ አባተ በሰጠው ምላሽ ምርኮኞችን ወደ ቤተሰቦቻቸው መላክና ፋኖን መቀላቀል የፈለጉትን የመቀበል ሂደቱ መቀጠሉን ተናግሯል።
መከላከያ በሚል ስም በሶስት ወር ደካማ ስልጠና ወደ ውጊያ የሚላኩ የአገዛዙ ወታደሮችን አዛዦቻቸው እጅ ከሰጣችሁ በአሰቃቂ ሁኔታ ትገደላላችሁ ስለሚሏቸው በተሳሳተ አረዳድ በውጊያው እንደሚሞቱ አስረድቷል።
ይህንንም ከምርኮኞች ማረጋገጥ እንደተቻለ እና ፋኖ ግን ከሚባለው በተቃራኒ ቁስለኛ ምርኮኞችን በእኩል ደረጃ በማሳከም ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ወደ ቤተሰቦቻቸው እስከመሸኘት መድረሱን ፋኖ ኢያሱ አረጋግጧል።
ለምርኮኞች ደህንነት ሲባል በቪዲዮ ይፋ የማይሆኑ ነገሮች በመረጃ ፍሰቱ ላይ ስለፈጠሩት እንቅፋትም ኃላፊው ያስረዳል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍562🤬1
የአማራ ፋኖ በጎጃም ያስተላለፈውን ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፈው በተገኙ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ
****
የአማራ ፋኖ በጎጃም በትላንትናው ዕለት ማለትም ግንቦት 14/2016 ዓ.ም ከዛሬ ግንቦት 15/2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል ያስተላለፈውን ጥብቅ ትዕዛዝ ተከትሎ ትዕዛዙን ተላልፈው ተግባራዊ ባላደረጉ ተሽከርካሪዎች ላይ በዛሬው ዕለት እርምጃ መውሰዱን ለመረጃ ቲቪ በላከው መልዕክት ገልጿል።

ትዕዛዙን ተላልፈው እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ አራት(4) ተሳቢ ተሽከርካሪዎች በማንኩሳ እና በቡሬ መካከል ዛባ ተብላ በምትጠራ ቦታ ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም (5ኛ ክ/ጦር )ደጃች አስቦ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ፣የአሳምነው ፅጌ ሻለቃ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ነው የተገለጸው።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ጨምሮ እንደገለጸው በትላንትናው ዕለት ያስተላለፈውን ትዕዛዝ ከተወሰኑት ውጪ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ምንም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ባለማድረግ ትዕዛዙን ተቀብለው ተግባራዊ ያደረጉ በርካቶች መሆናቸውንም አያይዞ ገልጿል።

በተጨማሪም በቀጣይ የአማራ ፋኖ በጎጃም ያስተላለፈውን ጥሪ ተላልፈው በሚገኙ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ሲል አስታውቋል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍12233
ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ የሚቀላቀሉ የአድማ ብተና አባላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ ..‼️‼️

በሰሜና በደቡብ ወሎ ዞን ተሰማርተው ከነበሩ የአድማ ብተና አባላት መካከል ግፍን በመቃወም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ከአሃዳቸው እየከዱ ወደ ፋኖ የሚቀላቀሉ የአድማ ብተና አባላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ለማረጋገጥ ተችሏል ።

ትናንት ግምቦት 14/2016 ዓ/ም ብቻ በሐይቅና በውጫሌ እንዲሁም በአምባሰል ከ30 በላይ የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ መቀላቀላቸው ተረገጋግጧል።

በሁለቱ ዞኖች ብቻ ካለፉት ሦስትና አራት ቀናት ወዲህ ፋኖን የተቀላቀሉ የአድማ ብተና አባላት ቁጥር 200 ይደርሳል ነው የተባለው።

ግንቦት ዘጠኝና አስር/2016 ዓ/ም በደቡብ ወሎ ዞን በሐይቅ፣ በቢስቲማ፣ በወረባቦ፣ በውጫሌ ዙሪያና በአምባሰል እንዲሁም በሰሜን ወሎ ደግሞ በመርሳ፣ በውርጌሳ፣ በወልድያ ዙሪያ፣ በቆቦ፣ በላስታ እና በሙጃ ዙሪያ በቁጥር ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ታውቋል ።

በራያ የአማራ ክልል መዋቅር እንዲፈርስ ከተደረገ ወዲህ ከአሃዳቸው እየከዱ ወደ ፋኖ የሚቀላቀሉ የአድማ ብተናና ፖሊስ አባላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ነው የተመላከተው።

ግምቦት 09/2016 ዓ/ም እና ግምቦት10 ብቻ በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ 24 የአድማ ብተና አባላት ፣ በወልድያ ዙሪያ 13 ፣ በመርሣ 12 ፣ በኒኒ በር 5 ፣ የአድማ ብተና አባላት እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ደግሞ በሐይቅ 17 ፣ በቦቀቅሳ 22 ፣ በውጫሌ 9 ፣ በወረባቦ 5 (አንድ መቶ አለቃ ከነ አጃቢዎቹ) በአምባሰል 22፣ በፀሀይ መውጫ 4፣ በወግዲና በሌሎች ምዕራብ ወረዳዎች በቁጥር 19 የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በአቅራቢያቸው የሚገኙ የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ክፍለጦሮችን መቀላቀላቸውን ነው  ለማረጋገጥ የተቻለው ።

በተመሣሣይ በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ባሉ አከባቢዎች ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የአድማ ብተና እንዲሁም የሚሊሻና የፖሊስ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል።

ከሦስት ሳምንታት በፊት ከ970 በላይ የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአሁኑ የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ አንድ አካል የሆነውን የቀድሞው የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝን መቀላቀላቸውን በወቅቱ ዕዙ በሰጠው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም።

በሁለቱ ዞኖች ያለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ተከትሎ በክልሉ ፀጥታ ቢሮ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መፈጠሩም ተሰምቷል።

ተሰማርተው ከነበሩበት የሐይቅ ከተማ አከባቢ ከድተው ወደ ፋኖ የተቀላቀሉት በቁጥር 17ቱ የአድማ ብተና አባላት ተናግረዋል ።

በተጨማሪም "በርካታ ጓዶቻችንን ገብረን፣ ስጋና አጥንታችን ከስክሰን ያስመለስነውን እርስታችን በድጋሚ ተመልሶ ለሕወሓት ተሰቶብናል ፣ ለምን ብለው የጠየቁ አባሎቻችንም ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን አናውቅም። በዛላይ ከወንድሞቻችን ጋር እንድንገዳደል ተገደናል።

እስከ ዛሬ ክህደት የፈፀምንባቸውን ፋኖ ወንድሞቻችን ይቅርታ ጠይቀን ያሳዘነውን ህዝባችንን ልንክስ ከአዴንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ክድተን ወጥተናል ብለዋል።

ያለፉት ሁለት ቀናት በሁለቱ ዞኖች ፋኖን ከተቀላቀሉት ከ150 በላይ የአድማ ብተና አባላት መካከል አብዛኻኞቹ ልዩ ኃይሉ ሳይፈርስ በፊት 2ኛና 3ኛ ዙር ሰልጥነው የመክት ብርጌድ፣ የጣና፣ የበላይ እና የመቅደላ ብርጌድ አባላት እንደነበሩ ለማረጋገጥ ችለዋል።

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
👍6712😱2🤯1
62👍29
💚💛 ውባንተ ተራራ ታሪክ ተሰራ!

ገላውዲዎስ ከተማ ዳር ላይ የሚገኘው ተራራ እዛው ቦታው ላይ በጀግንነት በተሰዋው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ስም "ውባንተ ተራራ" ተብሎ መሰየሙ ይታወቃል። በትናንትናው እለት የውባንተ የትግል ልጆቹ ታሪክ ሰርተውበታል። "ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር" የሚከተለውን ግዙፍ ድል ተጎናፅፏል።

ከጠላት ጦር የተደመሰሱ:-
#ሻለቃ ጌታቸው ሰኢድ መሐመድ
#አስር አለቃ ፀጋየ ሃይላይ ታረቀ
#ምክትል አስር አለቃ ጣሂር ኢሌም ገመዳ
#ከሰማንያ በላይ እግረኛ የአገዛዙ ጦ*ር
ምርኮኞች:-
አንድ መቶ አለቃ እና አንድ ሻምበል መሪ ጨምሮ 30 በላይ ምርኮኛ

የውባንተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የደመሰሰው የአገዛዙ ሰራዊት "ሰሜን ምእራብ እዝ፣ 503 ኮር፣ 78ኛ ክፍለ ጦር፣ አምስተኛ ሬጅመንት መሆኑ ታውቋል። ይህ የአገዛዙ ሃይል ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።

አንድ ልዩ " የሳምሪ" ሰላይ ኦፒ በቁጥጥር ስር ውሏል። በተደረገበት ምርመራ ትግረኛን ጨምሮ አራት ቋንቋ የሚናገር እብድ መስሎ የኦፒ( አቅጣጫ ጠቋሚ አስተኳሽ) አገልግሎት ሲሰጥ ነው በንስር አይናማ ገበሬ ወገን ቁጥጥር ስር የዋለ።

የፋኖ አመራሮች እንደገለፁልን፤ ቁስለኛ ምርኮኞችን ለህክምና ስናበቃቸው ከተባልነው በተቃራኒ አግኝተናቹሃል፣ በፋኖ ምርኮ አያያዝ በጣም ተገርመናል እያሉ ምስጋናቸውን ደስታቸውን በእ*ንባ ጭምር መግለፃቸውን አብራርተዋል።

በትናንትናው ዘገባ እንደተገለፀው ይህ ትልቅ ድል የተመዘገበው በጎጃም መስመር ተጨማሪ የአገዛዙ ጦር ወደ ገላውዲዎስ አቅጣጫ እንዳይመጣ በማንችሎት የሚመራው የወገን የጎጃም አማራ ፋኖ በአርብ ገብያ በኩል ትልቅ ገድል በመፈፀም በር በመዝጋቱ ነው። የፋኖ ትግል ቅንጅት እመርታ የተመዘገበት ድል ነው።
ማሸነፍ ብቸኛው መዳኛችን ነው!

ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

ፌስቡክ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/asharamedia24

የትዊተር 👇👇👇👇 https://x.com/AsharaMedia?t=-smOVxBgjnktAOJ6_3203Q&s=09

#YOUTUBE 👇👇👇👇 #SUBSCRIBE
https://www.youtube.com/@ashara-995
40👍39🔥4😢3🤯2🥰1