Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ፖስት አገልግሎት ድርጅትን ጎበኙ‼️
"ኢትዮጵያ በትዕግስት እና በጥንቃቄ የምታደርገው ውሳኔ ለሁሉም ልጆቿ ጥቅም ስትል ነው" - ዶክተር ለገሰ ቱሉ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በትዕግስት እና በጥንቃቄ የምታደርገው ውሳኔ ለሁሉም ልጆቿ ጥቅም ስትል መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ "ከታሪክና ተግባራዊ ልምምድ አንጻር ነገሮችን ከተመለከትን ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላም የሚደረግ ሽግግር በሰጥቶ መቀበል መርህ፣ በትዕግስትና በብልሃት የሚመሩ መሆኑን ያመለክተናል" ብለዋል።
ለዘላቂ ሰላም ጥቅሞችን ማጣጣም የግድ እንደሆነም ነው ያመለከቱት።
ይህ ጉዳይ ውስጣዊ ከሆነ ደግሞ የተለየ ትኩረት እና ማስተዋልን እንደሚጠይቅ ዶክተር ለገሰ ገልፀዋል።
"ኢትዮጵያ በትዕግስት እና በጥንቃቄ የምታደርገው ውሳኔ ለሁሉም ልጆቿ ጥቅም ስትል ነው" ብለዋል።
"ጉዳቶቻችንና ሃዘናችንን የምንረሳው ይቅር ስንባባል ነው" ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለዚህ መሳካት ልጆቿም ይተባበራሉ ብላ ኢትዮጵያ በእኛ ላይ እምነት ጥላለች ያሉት ሚኒስትሩ፥ "ከዚህ አኳያ የጀመርነው መንገድ መልካም ይመስላል፤ ልጆቿ ከተባበሩ ይሳካል" ብለዋል።
የሰላም ስምምነቱ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሻሻል ያደርጋል
******************
(ኢ ፕ ድ)
“በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሻሻል ያደርጋል” ሲሉ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ እንዳለ ንጉሴ አስታወቁ።
መምህር እንዳለ ንጉሴ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረገው ስምምነት ለኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
ኢትዮጵያ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲደረግባት የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በአሸናፊነት የተወጣች በመሆኑ ምዕራባውያን ያላቸውን ግንኙነት እንዲፈትሹ ይገደዳሉ ነው ያሉት።
እንደ አቶ እንዳለ ገለፃ፤ምዕራባውያን የጥቅምና የአመለካከት ጉዳይ በመኖሩ ከዚህ በኋላ ባለው ሂደት አርፈው ይቀመጣሉ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን በቀጥታ ጫና የሚያደርጉበት መንገድ ይቀንሳል፤ኢትዮጵያን ለማፍረስ ይጠቀሙበት የነበረው ግጭት ወደ ስምምነት በመምጣቱ የጸጥታው ምክር ቤትና የአውሮፓ ኅብረት በየጊዜው ስብሰባ ማድረግ አይችሉም። ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሚዲያዎቻቸውን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85655
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረጉ ሂደት በውስን የውጭ ባንኮች ይጀመራል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረጉ ሂደት ውስን ቁጥር ባላቸው የውጭ ባንኮች ብቻ የሚጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ እንደገለጹት÷ የውጭ ባንኮች ይዘውት የሚመጡት ካፒታል በኢትዮጵያ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በማቃለል ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ከዚህ መነሻነት የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረጉ ሂደት በውስን የውጭ ባንኮች ብቻ ይጀመራል።
መንግሥት በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ ለመሳተፍ የሚመጡ የውጭ ባንኮችን በሙሉ ተቀብሎ ፈቃድ እንደማይሰጥ ጠቁመው÷ ለመነሻነት ውስን የውጭ ባንኮችን ብቻ እንደሚያስተናግድ ተናግረዋል። ለዚህም አራት ቅድመ ሁኔታዎች....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85638
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ከንቲባ አዳነች አቤቤ‼️
የከተማ አስተዳደራችን በተለያዩ አካባቢዎች በ 2.78 ቢሊዮን ብር እየገነባቸው ካሉ 6 ዘመናዊ የመሸጋገርያ ድልድዮች መሃከል የኢምፔርያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ጉብኝተናል።
ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው ቀድሞ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በማስቀረት የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ እና ለከተማዋም አድገት የራሱን የሆነ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው፡፡ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ይደረጋል፡፡
አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና አበባ የማድረግ ጉዟችን በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡