Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረጉ ሂደት በውስን የውጭ ባንኮች ይጀመራል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረጉ ሂደት ውስን ቁጥር ባላቸው የውጭ ባንኮች ብቻ የሚጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ እንደገለጹት÷ የውጭ ባንኮች ይዘውት የሚመጡት ካፒታል በኢትዮጵያ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በማቃለል ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ከዚህ መነሻነት የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የማድረጉ ሂደት በውስን የውጭ ባንኮች ብቻ ይጀመራል።
መንግሥት በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ ለመሳተፍ የሚመጡ የውጭ ባንኮችን በሙሉ ተቀብሎ ፈቃድ እንደማይሰጥ ጠቁመው÷ ለመነሻነት ውስን የውጭ ባንኮችን ብቻ እንደሚያስተናግድ ተናግረዋል። ለዚህም አራት ቅድመ ሁኔታዎች....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85638
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ከንቲባ አዳነች አቤቤ‼️
የከተማ አስተዳደራችን በተለያዩ አካባቢዎች በ 2.78 ቢሊዮን ብር እየገነባቸው ካሉ 6 ዘመናዊ የመሸጋገርያ ድልድዮች መሃከል የኢምፔርያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ጉብኝተናል።
ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው ቀድሞ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በማስቀረት የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ እና ለከተማዋም አድገት የራሱን የሆነ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው፡፡ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ይደረጋል፡፡
አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና አበባ የማድረግ ጉዟችን በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በናይሮቢ የሰላም ስምምነቱን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ሲያደርግ የነበረው የልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

በመንግሥትና ህወሓት መካከል የተፈረመውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ በናይሮቢ የሰላም ስምምነቱን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ሲያደርግ የነበረው የልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተደረገውን ውይይት አጠናቀውና ተፈራርመው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሠዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናትና ባለወታደራዊ ማዕረጎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በውብሸት ሰንደቁ