Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

የ#አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው። ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ኝአንጋቶም ወረዳ ዐሻራችንን አሳርፈናል። በእንደዚህ ዓይነት አካባቢ የምናደርገው ጥረት የድርቅን ሥጋት ለመከላከል ያለመ ነው። እነዚህን ተግባራት በማስቀጠል ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል ፍሬያማ ውጤት ማግኘት እንችላለን።
የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል
-ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል
*********************************
(ኢ ፕ ድ)

የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚደንት ገለጹ፡፡

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የምዕራብ ፈጥኖ ደራሽ በአሶሳ ከተማ ያስገነባውን ካምፕ ዛሬ አስመርቋል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚደንት በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ፌዴራል ፖሊስ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ግዙፍ አቅም እየፈጠረ ነው።

የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በአሶሳ ከተማ ከተመረቀው በተጨማሪ በየክልሉ የሠራዊቱን አቅም የሚያጠናክሩ ካምፖች እየተገነቡ ነው ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በበኩላቸው፤ ክልሉ ወደ ተረጋጋ ሠላም እንዲመለስ የፌዴራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት በማዕድንና በሌሎች ዘርፎች የኢንቨስትመንት እንቅስቅሴዎች እንዳሉ ገልጸው፤ ኢንቨስትመንቱ እንዲጠናከር የፌዴራል ፖሊስ እገዛ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የዝግጅቱ ታዳሚዎች ችግኝ በመትከልም አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
የኢትዮጵያን የምርጫ ስርአት ለማጠናከር የሚውል ከ30 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ስርአት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋናንስ ድጋፍ ስምምነት ፕሮጀክት በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ድርጅት መካካል ተፈርሟል፡፡

ፕሮጀክቱ ሶስት ግቦች ያሉት ሲሆን አንድኛው የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን በማጠናከር ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ ፣ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር፣ ሁለተኛው ከሲቪክ ተቋማት ጋር በጋር በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ማሳደግ ሶስተኛው ደግሞ ነፃ ፍትሀዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ በሚቀጥሉት አራት አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የሀገሪቱን የምርጫ ስርአት በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲን ለማስፈን አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️

በእርከን ሥራ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በውኃ ማቆር እና በጥንታዊ የእጅ መሣሪያዎች በታወቀው የኮንሶ ሕዝብ መካከል በመገኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል።
👉 "ከወራቤ-ቦዥባር የመንገድ ግንባታ መዘግየት ምክንያት ለከፍተኛ መጉላላት ተዳርገናል" -አልቾ ውሪሮ ወረዳ ነዋሪዎች

👉 "በአጭር ጊዜ ሌላ የሥራ ተቋራጭ ከአስተዳደሩ ጋር ውል ተፈራርሞ ወደ ሥራ ይገባል" – የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የስልጤ ዞን መዲና ከሆነችው ከወራቤ ከተማ ተነስቶ አልቾ ውሪሮን አቋርጦ ቦዥባር ድረስ እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ግንባታ መዘግየት ለከፍተኛ እንግልትና መጉላላት እንደዳረጋቸው የዞኑ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በበኩሉ በአጭር ጊዜ ሌላ የሥራ ተቋራጭ ከአስተዳደሩ ጋር ውል ተፈራርሞ ወደ ሥራ ይገባል ብሏል።

የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሼክ መሐመድ ከማል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመንገዱ ግንባታ መዘግየት ምክንያት የሀገር ሽማግሌዎች ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104186
ኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ከስጋት ይልቅ የትብብርና የመልማት ጥያቄን እንዲመልሱ እየሠራች ነው
**********************
(ኢ ፕ ድ)

የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች የስጋትና ያለመተማመን መነሻ ከመሆን ይልቅ የትብብርና የዜጎችን የመልማት ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ለማድረግ ኢትዮጵያ ቁልፍ ሚና እየተጫወተች መሆኗን የስትራቴጃዊ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የስትራቴጃዊ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአፍሪካ ብዙ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አሉ። ኢትዮጵያ በየጊዜው በውሃ ዙሪያ ምክክሮችን በማዘጋጀት የጋራ ተጠቃሚነት እንዲሰፍን እየሠራች ነው። እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶች የስጋትና ያለመተማመን መነሻ ከመሆን ይልቅ የትብብርና የዜጎችን የመልማት ጥያቄዎች እንዲመልሱ ለማድረግ ጠንካራ ውይይቶችንና ምክክሮችን እያዘጋጀች ነው።

አፍሪካውያን ሀብታቸውን መጠቀም አለባቸው የሚለውን ሀሳብን በማንሳት ቁልፍ ሚና ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104197
የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ለሚዲያ ተባባሪና መረጃ ሰጪ በመሆን ሐሰተኛ መረጃን መመከት ያስፈልጋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ለሚዲያ ተባባሪና መረጃ ሰጪ በመሆን ሐሰተኛ መረጃን መመከት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገለጸ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እንድሪስ እንደገለጹት፤ ሁሉም የኮሙኒኬሽን መዋቅሮችና መረጃ በእጃቸው ያለ የመንግሥት አካላት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለሚዲያ ተባባሪና መረጃ ሰጪ በመሆን ሐሰተኛ መረጃን መመከት ያስፈልጋል።

እንደ አቶ መሐመድ ገለጻ፤ ከዲጂታል ሚዲያው ጋር ተያይዞ የመጣውን የሐሰተኛ መረጃ መመከት የሚቻለው ትክክለኛውን መረጃ ለማኅበረሰቡ ማቅረብ ሲቻል ነው።

ዘመኑ መረጃን ለሚዲያ ክፍት የሚደረግበትና ሕዝብ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104203
በአዲስ አበባ ከተማ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ182 የመፈተ ኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀመረ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው እለት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ዘንድሮ በከተማ አስተዳደር በ182 የፈተና ጣቢያዎች 75 ሺህ 090 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከምክትል ቢሮ ኃላፊው ከአቶ አሊ ከማል እና ከየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ፈይሳ ወዳጆ ጋር በክፍለከተማው በሚገኙ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የፈተናውን አጀማመር ተመልክተዋል።

የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዘንድሮ እንደመጀመሩና ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በእድሜ አነስተኛ እንደመሆናቸው ቢሮው ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሲሰራ ቆይቷል።

በከተማ አስተዳደሩ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እንከን ተጠናቋል።

የ6ኛ ክፍል ፈተናም በተመሳሳይ ሁኔታ ያልምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፈተና አስፈጻሚ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።