Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በገበታ ለትውልድ በመገንባት ላይ ያሉና የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ሰፊ ዕድል ይፈጥራሉ‼️

በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ የተገነቡ፣ በመገንባት ላይ ያሉና የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ሰፊ ዕድሎች እየፈጠሩለት ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በያዝነው የፈረንጆች አመት በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት የዓለም ቱሪዝምን በመሳብ 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የዓለም አቀፉ ቱሪዝም ተቋም አስታወቀ፡፡ ተቋሙ 2023 ከጥር እስከ ሐምሌ ያለውን የሀገራትን የቱሪዝም ፍሰት ከ2019 ጋር በማነጻጸር ይፋ አድርጓል፡፡

ኢትዩጵያ በያዝነው 2016 ዓ.ም መጀመሪያ ሁለት ቅርሶቿን በዩኔስኮ መዝገብ አካትታለች።

በተያዘው 2016 በጀት ዓመት አንድ ሚሊዮን የውጭ ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ከሚመጡ የውጭ ሀገራት ዜጎች ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ኢፕድ መዘገቡ ይታወሳል።

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
161 የፌዴራል ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ አቅርበዋል
****
(ኢ ፕ ድ)

ከ169 የፌዴራል ተቋማት 161 ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ አቅርበዋል።

የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ኤሌክትሮኒክስ ግዢ ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት እያደረገ ይገኛል።

በዉይይቱ ላይ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንደገለጹት በተያዘዉ በጀት ዓመት 161 ተቋማት ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ያቀርባሉ።

በ2016 ዓ.ም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ግዢ ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም ጠቁመዋል።

በግዢ ስርዓቱ ሲያጋጥም የነበረዉን ሌብነት ከማስቀረቱም በተጨማሪ ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ ነዉ ብለዋል።

በመጀመሪያወዉ ሩብ ዓመትም 2802 ጨረታዎች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ መዉጣታቸዉ ተጠቁሟል። 3,800 የሚጠጉ የንግዱ ማህበረሰብም በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግዢ እየፈጸመ እንደሆነም ተገልጿል።

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
ጥቅምት 27 ቀን 2016  ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
ኢትዮጵያ እና ቻይና አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ
****
(ኢ ፕ ድ)

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ኢትዮጵያ እና ቻይና በአስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም በጥናትና ምርምር ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

ከቻይና ብሄራዊ የአስተዳደር አካዳሚ የልዑካን ጋር የሁለቱን ሀገራት አጋርነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።

ኢትዮጵያ እና ቻይና በተለያዩ መስኮች አብሮ በመስራት የቆየ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቁመው፤ በአሁኑ ጊዜ የቻይና ብሄራዊ የአስተዳደር አካዳሚ በአስተዳደር ስልጠና እንዲሁም በጥናትና ምርምር ያለውን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ያለውን ዝግጅት አድንቀዋል፡፡

አካዳሚው በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አቅም ያለውና የበርካታ ምሁራን ስብስብ በመሆኑ፤ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተዛማጅ የሆነ ልምድ በማጋራት የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር እንደሚገባ አፈጉባኤው ተናግረዋል፡፡

የቻይና ብሄራዊ የአስተዳደር አካዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ጎንግ ዌቢን ቻይና ከኢትዮጵያም ሆነ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸው፤ አካዳሚው በስልጠናም ሆነ በጥናትና ምርምር ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የቻይና ብሄራዊ የአስተዳደር አካዳሚ እና የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ በቅርቡ የሚፈራረሙት የትብብር ስምምነት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንደሚያጠናክርም የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
በ16 ሚሊየን ዶላር በጀት የአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም ተጀምሯል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በ16 ሚሊየን ዶላር በጀት 624 ኪሎዋት ሀይል በማመንጨት 32ሺ ግለሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም ተጀምሯል።

ግሎባል ኢንቫሮመንት ፋሲሊቲ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም አስጀመረ

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ እንደገለጹት ብሔራዊ ኤሌክትርፍኬሽን ፕሮግራም ተቀርፆ በመንቀሳቀስ በ2030 ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

ብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም 35 በመቶ ከመስመር ውጭ (off grid) ለመሸፈን የታለመ በመሆኑ፤ መሰል ፕሮጀክቶች ፕሮግራሙን ለማሳካት ጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ሚኒግሪድ ፕሮጀክት 16 ሚሊየን ዶላር የተመደበለት፤ ሲሆን 624 ኪሎዋት ሀይል በማመንጨትና 32ሺ ግለሰቦችን ተጠቃሚ በማድረግ፤ 120 ሰዎች የስራ እድልን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የአየር ንብረትን ለመከላከል ሚና እንዳለው ጠቅሰው፤ በዚህ ስራ ከ16ሺ ቶን በላይ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እንደሚረዳና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
*******
(ኢ ፕ ድ)

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከጥቅምት 28ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ቀደም ሲል በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ::