EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች የተከናወነው የመስቀል ደመራ መዝሙር የመጨረሻው ጥናትና ልምምድ
*********

በ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ከሚቀርቡ ኃይማኖታዊ ሥርዓቶች አንዱ ለበዓሉ የሚስማማ መዝሙር ነው።

ይህ መዝሙር የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ጊዜ ወስደው የሚዘጋጁበት ነው።

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ለ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ሲያደርገው የነበረውን የመዝሙር ጥናት ያጠናቀቀውም ዛሬ ነው።

በዛሬው ዕለትም ነገ በሚከናወነው የመስቀል ደመራ የሚቀርብ መዝሙር የመጨረሻ ጥናትና ልምምድ ተከናውኗል።

ዕለቱን የሚያወድሱ እና ሌሎች የምስጋና መዝሙራትን ጨምሮ የማዕከሉ ዘማሪያን ከ80 በላይ መዝሙራትን ሲያጠኑ ቆይተዋል።

የመዝሙር ጥናቱ በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በግዕዝ፣ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ፣ በወላይትኛ፣ በጉራግኛ እና በክስታንኛ ተከናውኗል።

ማዕከሉ የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል በደመቀ እና ኃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ለማሳለፍ እንደተዘጋጀም ተገልጿል።

በአሰግድ ሲሳይ
👍5515👎10👏2
ቅኝት ስፖርት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከትዌንቴ የዩሮፓ ሊግ

https://www.facebook.com/share/v/YBKyx6SqqbdSmnv6/?mibextid=oFDknk
👍86
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎቹን በኮትዲቯር ያደርጋል
*************

ዋልያዎቹ ከጊኒ ጋር የሚያደርጓቸው እነዚህ የደርሶ መልስ መረሐ ግብሮች በኮትዲቯር እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።

የሁለቱ ሀገራት የመጀመሪያ ጨዋታ ጊኒ የሜዳዋ ጨዋታዋን ለማድረግ ባስመዘገበችውና በያሞሱክሩ በሚገኘው ስታድ ኮናን ባኒ ስታዲየም ጥቅምት 1/2017 ከምሽቱ 1፡00 ላይ ይከናወናል።

ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ባስመዘገበችውና አቢጃን በሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ስታዲየም ጥቅምት 4/2017 ምሸት 4፡00 ላይ ይደረጋል።

ሞሮኮ በ2025 ለምታሰናዳው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ እስካሁን ሁለት ጨዋታዎችን ያደረጉት ዋልያዎቹ አንድ ነጥብ በመያዝ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ጊኒ በአንጻሩ እስካሁን ምንም ነጥብ አላስመዘገበችም።

በዮሴፍ ሹምዬ
👍313👎3
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የተ.መ.ድ. ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴቴን አሰናበቱ
**************

ፕሬዚዳንቷ በዚሁ ወቅት ልዩ መልዕክተኛዋ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ላበረከቱት ከፍተኛ ድጋፍ ማመስገናቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
👍4412
ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ላስመዘገበችዉ አመርቂ ዉጤት እዉቅና አገኘች
********************

በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው የተመድ 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሽልማት አበርክቷል።

እውቅናው የተሰጠው ኢትዮጵያ የተቀናጀ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በማከናወን እና ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት መስጠት በመቻሏ በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰርን በመከላከል ላስመዘገበችው ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሽልማቱን መቀበላቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍292
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በተገለጸው ክፍት የሥራ መደብ ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በፍሪላንስ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች ለተገለጸው ክፍት የስራ መደብ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይሄ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የስራ ቀናት ሸጎሌ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዲቪዥን ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
👍96👎1
የዘንድሮው ኢሬቻ መስከረም 25 እና 26 እንደሚከበር ተገለፀ
****************

የዘንድሮው ኢሬቻ መስከረም 25 እና 26 እንደሚከበር የአባገዳዎች ሕብረት አስታውቋል፡፡

የኢሬቻ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የአባገዳዎች ሕብረት መግለጫ የሰጠ ሲሆን፤ በዚህም በዓሉ በመስከረም 25 ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ፤ በመስከረም 26 ደግሞ ኢሬቻ ሆረ አርሰዴ እንደሚከበር ተገልጿል።

መግለጫውን የሰጡት አባ ገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች ኢሬቻ የእርቅና የሰላም በዓል በመሆኑ ዘንድሮም አንድነትንና ሕብረትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር ገልጸዋል።

የኦሮሚያ አባገዳዎች ህብረት ሰብሳቢ አባገዳ ወርነህ ተሬሳ፤ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት እሴትን በጠበቀ መልኩ ለማክበር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid021ZRuaKAiqMGKJGKjjN37SX6sy5oJRPoSdXmWewqYwJyHZ6pz6enKvoCeAPFK5NcNl
👏149👍8👎8
የመስቀል ደመራ በዓል ድባብ በደብረ ማርቆስ ከተማ
14👍13👎1