EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የመንግስት አግልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎችን ገመገመ
*************

የመንግስት አግልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።

አብይ ኮሚቴው በስብሰባው የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎችን በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ ስምንት ተቋማት በተገኙበት መገምገሙን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

በቀጣይም መልካም ጅምሮች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት እና በሪፎርሙ የታቀፉ ተቋማትም ያላቸውን ልምድ የሚቀያየሩበት አውድ መፍጠር መቻሉን ጠቅሰዋል።

ተቋማት ያከናወኗቸውን ተግባራት በዝርዝር በመቃኘት እንዲሁም ጥንካሬዎችንና ውስንነቶችን በመለየት በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አብይ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡንም ገልፀዋል።

አብይ ኮሚቴ ከስብሰባው ጎን ለጎን በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችንም ጎብኝቷል።

በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት ሪፎርም መጀመሩ ይታወቃል።
👍10
ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥትን የእድሳት ሥራ ጎበኙ
***********

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ የተለያዩ ልማቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀምን እና የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት የእድሳት ሥራ ሂደትን ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን በተቋራጭነት ከሚሠራው ቢአይካ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ መወያየታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
👍17👏2
ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች መሆኑን የአፍሪካ ሕግ አውጪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች ገለጹ
**********

ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች ስለመሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአፍሪካ ወጣት የሕግ አውጭዎች ማኅበር አባል አቶ ከማል ሃሺ ገለጹ።

አቶ ከማል ይህን ያሉት የአፍሪካ ሕግ አውጪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው።

ጉባዔው በዋናነት በሙስና፣ ፊስካል ፍትህ እና ዲጂታል አስተዳደር ላይ ያተኮረ እንደነበር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

አቶ ከማል ከስብሰባው ጎን ለጎን በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ለጉባዔው ተሳታፊዎች አስጎብኝተዋል።

የአፍሪካ ወጣት ሕግ አውጪዎቹ በጉብኝታቸው በተመለከቱት የልማት እንቅስቃሴ ስለመደመማቸው አቶ ከማል ገልፀዋል።

እየተከናወነ ያለው ልማት ከፍተኛ በጀት የሚፈልግ ከመሆኑ አኳያ ኢንቨስትመንቱ ኢትዮጵያ በተሻለ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ እንዳለች የሚያመላክት ስለመሆኑም ጎብኚዎቹ ተናግረዋል።
👍222
"በደማችን ተከብሮ የቆየው ሉዓላዊነታችን በላባችን ፀንቶ ይቀጥላል" - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
***********************

በደማችን ተከብሮ የቆየው ሉዓላዊነታችን በላባችን ፀንቶ ይቀጥላል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡

የአገልግሎቱ መግለጫ እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች በውጭ ወራሪዎችና ጠላቶች የሚቃጡባትን ጥቃቶች በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ሉዓላዊነቷ ተከብሮ፣ የነፃነት ተምሳሌት ሆና ኖራለች፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የቀደምት ስልጣኔዎች ባለቤት፣ በተፈጥሮ ሀብቶች የበለጸገች፣ የሰው ልጅ እና የቡና መገኛ፣ በቅኝ ያልተገዛች የነፃነት ተምሳሌት ናት፡፡

ይሁን እንጂ ይህ አኩሪ ታሪካችንና ማንነታችን በተለያዩ ውስብስብ ምክንያቶች በኢኮኖሚያዊ እድገታችን ከዓለም ሀገራት ወደኋላ ቀርተናል፡፡ ይህ ሄኔታ ወደኋላ መቅረት ብቻም ሳይሆን በስንዴ ምፅዋት እንድንኖር አድርጎናል፡፡ በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተጠብቆና ተከብሮ የኖረው ሉዓላዊነታችን በላባችን ማፅናት ባለመቻላችን በስንዴ ልመና እና እርዳታ ነፃናታችን ተሸራርፏል፡፡ ሕዝቡን ለመመገብ የሌለውን እጅ የሚጠብቅ ነፃነቱና ሉዓላዊነቱ የተሟላ አይሆንምና፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0C6vWcEnd77A3hhhhFv1Gfyjt1z1NavLurVhYHjim3uSSgYHfeMeTBfMBQMdC5VjPl
👍39👎10👏52
ህብረተሰቡ ለሰላምና ለልማት ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ርዕስ መስተዳደር አረጋ ከበደ ገለፁ
*******************

የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አረጋ ከበደ ከጎንደር ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

አሁን እየተከናወነ ያለው ልማት የበለጠ እንዲስፋፋና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ከከተማ፣ ከክልልና ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።

ሰላም በመንግሥት ተፈጥራ በመንግሥት ተባርካ የምትቀርብ መና አይደለችም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ሰላም የሁሉን ትብብርና ቅንጅት ትፈልጋለች ብለዋል።

አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማፅናት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የጎንደርን ገፅታ ሊያሳምሩ የሚያስችሉ ትልልቅ ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን በመገንዘብ ልማቱ ለማስቀጠል ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በበኩላቸው፤ አሁን ያሉ የልማት እድሎችን ለመጠቀም ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከህዝቡ ጋር በመደጋገፍና በመመካከር በመስራት ከቻልን በአጭር ጊዜ ጎንደር ከተማን ሊመጥን የሚችል ልማት ማምጣት እንደሚቻል መናገራቸውን የጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽ ቢሮ መረጃ አመልክቷል።
👍255
በ8 ዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው የኦዳ ቡሉ ስርዓት እየተካሄደ ነው
*****************

የቦረና ኦሮሞ የገዳ ስርዓት አካል የሆነውና በ8 ዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው የኦዳ ቡሉ ስርዓት እየተካሄደ ነው።

71ኛው የቦረና አባገዳ ኩራ ጃርሶ የስልጣን ርክክብ ቅድመ ዝግጅት የሆነው የኦዳ ቡሉ ስርዓት ላለፉት 27 ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ቆይቷል።

በርካቶች ተሳታፊ የሆኑበት የመጨረሻዋ 27ኛ ቀን ላይ የተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተካሄዱ ይገኛል።

የምርቃትና የዕርድ ስነ ስርዓት ከተካሄዱ ስርዓቶች መካከል ነው።

የኦዳ ቡሉ ስርዓት በቦረና የገዳ ስርዓት 8ኛ የስልጣን መጠናቀቂያ የሚደረግ ሲሆን ይህም ፈጣሪ የሚለመንበት ስርዓት መሆኑ ተገልጿል።

በስነ ስርዓቱ መሰረት ከ3 ወር በኋላ ባሊ ወይም የስልጣን ርክክብ ይካሄዳል።

በሙሉ ግርማይ
👍278👎2
የበሰቃ ሐይቅ ምሥጢሮች፦ራዕይን መከተል የማያወላውል ቁርጠኝነት እና ዓላማ ያለው ርምጃ ይጠይቃል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍51👏112