FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) – Telegram
FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)
8.5K subscribers
1.28K photos
37 videos
3 files
172 links
ይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው
Download Telegram
ደመራ በአዲስ አበባ
በአሰግድ ሲሳይ
#etv #EBC #ደመራ
1
ዛሬ የሚመረቀው የኢቢሲ የጅማ ስቱዲዮ በምስል፦
ጂማ ስቱዲዮ - ተጨማሪ የይዘት ምንጭ
#etv #EBC #Jimma
😱2
ኢቢሲ ከአዲሱ የጅማ ስቱዲዩ ልዩ የምርቃት ስነ-ስርአት በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ ይገኛል
https://www.facebook.com/EBCzena/videos/427425130362005
ዛሬ የሚመረቀው የኢቢሲ የጅማ ስቱዲዮ በምስል፦
ጂማ ስቱዲዮ - ተጨማሪ የይዘት ምንጭ
#etv #EBC #Jimma
🔥5👍1
የፕሮግራም ጥቆማ ለሀገር ልጆች

ከቅኝት ስፖርት አዘጋጆች
አርሰናል ከ ፒኤስጂ

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ2024/25 የውድድር ዓመት የ2ኛ ሳምንት መርሐግብር በሰሜን ለንደን ኤምሬትስ ስቴዲየም ላይ ዛሬ ማክሰኞ ምሽት 4:00 የእንግሊዙ አርሰናል ከፈረንሳዩ ፓሪሰን ዠርሜ ጋር የሚያደርጉትን አጓጊ ጨዋታ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ቅኝት ስፖርቶች ወደናንተ ያደርሳሉ።

ጨዋታውን በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ በሬዲዮ፣ በሳተላይት ቴሌቪዥን፣በዩቲዩብና በፌስቡክ ገጾቻችን በፈለጉት አማራጭ መከታተል ይችላሉ!!

የጨዋታውን ትክክለኛ ግምት በማስቀመጥ የካርድ ሽልማቶችን ያግኙ!!

ፕሮግራሙን ቅኝት ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬሽን ጋር በመተባበር በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ያቀርቡታል።

ሙሉ ጨዋታን ቀጣዩን ሊንክ በመጫን በዩቱዮብ ገፃችን ይከታተሉ::

@FMADDIS97.1-qw6tj
6👍3👎1🔥1😁1
የአባገዳ ባንዲራ ቀለማት እና የቀለማቱ አቀማመጥ ትርጉም
*********************

የአባገዳ ባንዲራ ቀለማት አቀማመጥ ከላይ ወደ ታች
ጥቁር፣
ቀይ፣
ነጭ ነው።
ጥቁር መደብ፦ የፈጣሪ የበላይ መሆንን የሚገልጽ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ራሱ ጥቁር እንደሆነው ሁሉ ፈጣሪው /ዋቃ/ ጥቁር ነው ብሎ ያምናል። ጥቁር ቀለምም በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የቀዳሚነት መገለጫ ነው። ጥቁሩ ፈጣሪ ያለው ከላይ ነው፤ ዝናብ የሚዘንበው ከላይ ባለው ጥቁር ደመና ነው፣ ራሳችን ላይ ያለው ፀጉር እስኪሸብት ድረስ ጥቁር ነው፤ የዓይናችን ብሌን ጥቁር ነው - የሚገኘውም ከላይ ነው። እናም ጥቁር ቀዳሚ የመሆን መገለጫ ነው።

ቀይ መደብ፦ የብቃት፣ ብስል የመሆን፣ ሙሉ ሆኖ የመገኘት እና ለሕዝብ ነፃነት መሥዋዕት የመሆን መገለጫ ነው። ሁሉም ነገር በጊዜው ሙሉ ሆኖ የመገኘት ምሳሌ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ አንድ ነገር የብቃት ደረጃው ላይ መድረሱን ሲገልጽ “diimate” /ቀላ/ ብሎ ይገልጻል።

ነጭ መደብ፦ የነገሮች ፍፃሜ መገለጫ ነው። እንደ ምሳሌ፦ ጠቁሮ ዝናብ የሚሰጠን ደመና ነጭ ሲሆን አይዘንብም ማለት ነው፤ ጥቁር የነበረው የሰው ፀጉር እርጅና ሲደርስ ይሸብታል (ነጭ ይሆናል)፣ ነዶ ያለቀ እንጨት አመዱ ነጭ ነው … ስለዚህ ነጭ የፍፃሜ መገለጫ ነው ብሎ ያምናል - የኦሮሞ ሕዝብ።
#ኢሬቻ #etv #EBC
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0253oMPjoupdgwMWm1VF6ajSAWXxxfihs7dUixTcNezadBhVKL3vm4YhggLecPRtipl
👍6👎1😁1