Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በኮሪደር ልማቱ በአራት ኪሎና ፒያሳ የተጠናቀቁና ለህዝብ ክፍት የሆኑ መንገዶች‼️

👉 ከአራት ኪሎ ራስ መኮንን ድልድይ፣

👉 ከደጎ አደባባይ በቀይባህር አብርሆት ቤተ መፃህፍት፣

👉 ከማህሙድ- በቴድሮስ አደባባይ ወዳጅንት አደባባይ፣

ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት ‼️

ዛሬ ጠዋት የዘንድሮው የበጀት አመት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ የሆነውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀናት ግምገማ ጀምረናል።
እንደሁልጊዜው የየሴክተሮችን አፈፃፀም እንገመግማለን። ክፍተቶችን እናጤናለን፤ በጥንካሬዎች ላይ ለቀጣይ ስራዎች እንነሳለን።

ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ስትራቴጅያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር በሁለትዮሽ እና ክልላዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለቱ ሀገራት መካከል ከወራት በፊት የተፈረመው ስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ውይይቱ በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
ሆስፒታሉ በዓመት ለ60ሺህ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጣል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ስር የሚገኘው አቤት ሆስፒታል በዓመት ለ60 ሺ ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አናኒያ ጃንባይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ ከተቋቋመ 9 ዓመታትን ያስቆጠረው አቤት ሆስፒታል እየሰጠ ያለው አገልግሎትና የተገልጋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ከሌሎች ሆስፒታሎች በተለየ ሁኔታ ከድንገተኛ አደጋና ከቃጠሎ ጋር የተያያዙ ህክምናዎችን እንዲሰጥ ታስቦ የተቋቋመው ሆስፒታሉ፣ ከአጥንት ስብራት፣ ከዲስክ መንሸራተት፣ ከነርቭ ጋር የተያያዙና ሌሎችንም ትልልቅ ቀዶ ህክምናዎችን እየሰጠ ነው፡፡

ዶ/ር አናኒያ እንደተናገሩት፣ በሆስፒታሉ ብቻ የሚሰጡ ህክምናዎች ያሉ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በሀገር ውስጥ ባሉ ጥቂት የመንግሥት የህክምና ተቋማት የሚሰጡ ናቸው፡፡

ከህክምና አገልግሎት በተጨማሪ ከትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ የኢንሹራንስ ግንኙነቶችና የካሳ ክፍያ ጥያቄዎች ሲኖሩ የጉዳት መጠን ማብራራትን የመሳሰሉ ትልልቅ ሥራዎችን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129710